TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

ዛሬ ማምሻውን የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከምርጫ በኋላ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያን የወደፊት አካሔድ ለመወሰን እና የአገሪቱን ዴሞክራሲ እና ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ የሚመሩት መንግሥት እና መላ ኢትዮጵያውያን ከምርጫ በኋላ ለሚካሔድ አካታች የፖለቲካ ብሔራዊ ውይይት ቁርጠኛ እንዲሆኑ ነው የባይደን አስተሳደር ጥሪ ያቀረበው።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሚመሩት የአሜሪካ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሠራተኞቹ ጥረቶች እውቅና ቢሰጥም ፤ 6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚካሔድበት ከባቢ “አሳሳቢ ነው” ብሏል። 

የአሜሪካ መንግስትን አቋም የሚያንጸባርቀው መግለጫ ዛሬ ማምሻውን አንቶኒ ብሊንከን በሚመሩት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኩል ነው የወጣው።

የባይደን አስተዳደር የኢትዮጵያ ምርጫ አሉበት ያላቸው ፈተናዎች ፦
- የተቃዋሚ ፖለቲከኞች እስር፣
- የገለልተኛ ሚዲያ መዋከብ፣
- የአካባቢያዊ እና ክልላዊ መንግሥታት ወገንተኝነት እንዲሁም በመላ ኢትዮጵያ በብሔሮች እና በማህበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሱ ግጭቶች ለነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንቅፋት ናቸው ብሏል።

"በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች በክልሎች እና ብሔሮች መካከል ያለው ልዩነት መካረር የአገሪቱን አንድነት እና የግዛት ሉዓላዊነት ያሰጋል” ያለው የአሜሪካ መንግስት #ከምርጫው_በኋላ መፍትሔ ሊፈለግ እንደሚገባ አሳስቧል።

የአሜሪካ መንግስት ፥ “ከምርጫው በኋላ ያለው ጊዜ #ኢትዮጵያውያን ተባብረው እነዚህን ልዩነቶች ለመጋፈጥ ኹነኛ ወቅት ነው” ብሏል።

የአሜሪካ መግለጫ : www.state.gov/elections-in-ethiopia/

#EthiopiaInsider #SpokespersonNedPrice #Ethiopia

@tikvahethiopia