ፎቶ / ቪድዮ ፦ የቀድሞው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ስብሃት ነጋ አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።
አቶ ስብሃት ወደ አሜሪካ ያቀኑት ለህክምና መሆኑ ተነግሯል።
ከዚህ ቀደም አቶ ስብሐት ነጋ ለፍ/ቤት በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ገልፀው ህክምናቸውን አድርገው ለመመለስ ወደ ውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸው ክስ መስርተው እንደነበር ይታወሳል።
በህዳር 23 ቀን 2015 በነበረ ቀጠሮ ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ የፍትሃብሔር ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት አቶ ስብሃት ነጋ ወደ ውጪ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ #ተገቢ_አይደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ነበር።
ይኸው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመፈጸሙን ተከትሎ አቶ ስብሃት በጠበቃቸው አማካኝነት ውሳኔው እንዳልተፈፀመላቸው ገለጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል።
በዚህም በቀረበው አቤቱታ መነሻ ለምን የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳልተፈጸመ ከፌደራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ቀርበው እንዲያብራሩ ከተደረገ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔው እንዲፈጸም በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
አቶ ስብሃት ነጋ በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻ ከብዙ መጉላላት በኋላ ለህክምና ከኢትዮጲያ ወደ ውጭ ሀገር መውጣት ችለዋል።
Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
Video / Photo : Social Media
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) መግለፃቸውን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ለረጅም ጊዜ በሀገር ውስጥ እና በውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ትላንት…
ፎቶ፦ ዛሬ የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።
ስርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፤ የመንግስት ኃላፊዎች፤ ከኖርዌይና ከተለያየ አካባቢ የመጡ የውጪ ሀገር ወዳጆቻቸው እና በበርካታ ምዕመናን በተገኙበት ነው።
Photo Credit : EOTC TV
@tikvahethiopia
ስርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፤ የመንግስት ኃላፊዎች፤ ከኖርዌይና ከተለያየ አካባቢ የመጡ የውጪ ሀገር ወዳጆቻቸው እና በበርካታ ምዕመናን በተገኙበት ነው።
Photo Credit : EOTC TV
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ በትላንትናው ዕለት የተደረገውን ጥሪ በመቀበል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተደረሰውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመቀበል በዛሬው ዕለት ወደ እናት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን የሚገልዕ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በማቅረብ በይፋ መመለሳቸውን አሳወቀች።
ቤተክርስቲያኗ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፦
- ወደ ሥራ እንደምትመልሳቸው
- ደመወዛቸውን እንደምትከፍል
- የታሸገውን ቤታቸውን በመክፈት እንደምታስረክባቸው ገልጻለች።

#ጫሞ
በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች፤ ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ።
" ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው።
ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ማዕበል የመስጠም አደጋው ያጋጠመው።
በአደጋው የጀልባውን ሹፌር ጨምሮ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
አደጋው መከሰቱ እንደታወቀ የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ጥረት ቢደረግም በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት አልተሳካም።
ከአደጋው መድረስ በኋላ ከአርባ ምንጭ ከተማ በመጡ ዋናተኞች ጭምር ሕይወት ለማዳን ቢሞከርም በሰዓቱ የነበረው ማዕበል አላስቻለም ተብሏል።
በጫሞ ሐይቅ ላይ የነበረው ማዕበል ዛሬ ጠዋት ጋብ ማለቱን ተከትሎም ፤ የሟቾችን አስክሬን ለማግኘት ፍለጋው መቀጠሉን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
(እስካሁን የተገኘ አስክሬን የለም)
Credit : Ethiopia Insider

#ጫሞ በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች፤ ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ። " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው። ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው…
" ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው ተሟጧል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ
የደቡብ ፖሊስ ትላንትና በ #ጫሞ_ሐይቅ ላይ ለሰመጠችው ጀልባ መንስኤው ከመጠን በላይ መጫን እና ባልተለመደ ሁኔታ የተከሰተ ማዕበል ነው ብሏል።
የዞን ፖሊስ በበኩሉ ጀልባዋ ከሥምንቱ ሰዎች በተጨማሪ #ሙዝ እና #ዕቃ መጫኗን አሳውቋል።
የሕይወት አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያለው ፖሊስ ለዚህም የተለያዩ ጀልባዎችና ዋናተኞች ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
በተከናወነው የፍለጋ ሥራ ከጫማዎች እና የተለያዩ አልባሳት ባለፈ የተገኘ ነገር እንደሌለ ተገልጿል።
የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል እስካሁን ድረስ በሕይወት የተገኘ አለመኖሩን ጠቁመዋል።
ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው መሟጠጡንም ቢሮው ገልጿል።
(ኤፍቢሲ)

ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#መግለጫ
በኢትዮጵያ ኦርቶኮስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ መንግስት የቄስ ዓባይ መለሰን ገዳዮች ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ አለ።
ሀገረ ስብከቱ በሰጠው መግለጫ ፤ " መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐባይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ " ብሏል።
አክሎም ፤ " ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር " ሲል ጠይቋል።
ከዚህ ባለፈ በሸገር ከተማ አስተዳደር አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
እስካሁን የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ ሀገረ ስብከቱ ጠይቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ፎቶ / ቪድዮ ፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ የሆነው ቼልሲ ትላንት እሁድ እለት በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ክፍት የሆነ የ " ኢፍጣር " ስነሥርዓት በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም አስተናግዷል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በምዕራብ ለንደኑ ግፉዝ ስታዲየም ተሰብስበው የኢፍጣር ስነስርዓቱን ያከናወኑ ሲሆን ስነስርዓቱ የተዘጋጀው በቼልሲ ፋውንዴሽን እና በ " ረመዷን ቴንት ፕሮጀክት " ነው።
Video Credit : Bein Sport