TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ / ቪድዮ ፦ የቀድሞው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ስብሃት ነጋ አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።

አቶ ስብሃት ወደ አሜሪካ ያቀኑት ለህክምና መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አቶ ስብሐት ነጋ ለፍ/ቤት በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ገልፀው ህክምናቸውን አድርገው ለመመለስ ወደ ውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸው ክስ መስርተው እንደነበር ይታወሳል።

በህዳር 23 ቀን 2015 በነበረ ቀጠሮ ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ የፍትሃብሔር ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት አቶ ስብሃት ነጋ ወደ ውጪ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ #ተገቢ_አይደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ነበር።

ይኸው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመፈጸሙን ተከትሎ አቶ ስብሃት በጠበቃቸው አማካኝነት ውሳኔው እንዳልተፈፀመላቸው ገለጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል።

በዚህም በቀረበው አቤቱታ መነሻ ለምን የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳልተፈጸመ ከፌደራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች  ቀርበው  እንዲያብራሩ ከተደረገ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔው እንዲፈጸም በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

አቶ ስብሃት ነጋ በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻ  ከብዙ መጉላላት በኋላ ለህክምና ከኢትዮጲያ ወደ ውጭ ሀገር መውጣት ችለዋል።

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ
Video / Photo : Social Media

@tikvahethiopia