TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ ለሚገነቡ 10 ሺህ ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በምዕራፍ 1 ፕሮጀክት የሚገነቡ የ5 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳናች አቤቤ አስጀምረዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በአንድ አመት ዉስጥ ተገንብተዉ ለነዋሪዎች የሚተላለፉ መሆኑ ተገልጿል።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአሁን በፊት በከተማዋ ሲገነቡ የነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ጥራት ችግርና የሃብት ብክነትን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩን ለ54 ቢሊዮን ብር ዕዳ መዳረጉን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ እነዚህንና መሰል ችግሮችን ከመቅረፍ ጎን ለጎን የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ነዉ ብለዋል።

ተገጣጣሚ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በተቀመጠላቸዉ ጊዜ ዉስጥ ተጠናቀዉ ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።

በከንቲባዋ የተመራ ቡድንም የተገጣጣሚ ቤቶቹን ግብአት ማምረቻ ፋብሪካና እየተመረቱ ያሉትን ልዩ ልዩ ግብአቶች ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል።

የሚገነቡት ቤቶች ባለ 4 እና ባለ 10 ወለል ሕንጻዎች ሲሆኑ ቤቶቹን የሚገነባዉ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ነዉ።

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
አርቲስት ኑሆ ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አርቲስት ኑሆ ጎበና ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት ኑሆ ጎበና በአፋን ኦሮሞና በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ ዜማዎችን ለአድማጭ አበርክቷል፡፡

አርቲስት ኑሆ ፤ ከአባቱ አቶ መሃመድ ጎበና እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ አደም በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡

#ኤፍቢሲ/#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
#Oromia

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ውሳኔዎቹ ምድናቸው ?

ውሳኔዎቹ ከከተሞች አደረጃጀት ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለትና ከዛ በላይ ከተሞችን አንድ ላይ እንዲደራጁ ተወስኗል።

1. ቢሾፍ ከተማ ፦ የቢሾፍቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እንዲሁም የመዘጋጃ ቤት ከተሞች ሂዲ፣ ኡዴ ደንካካ እና ድሬ በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ10 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

2. ሻሸመኔ ከተማ፦ የሻሸመኔ ከተማ እና የብሻን ጉራቻ ከተማ በመቀላቀል በ4 ክ/ከተሞች እና በ12 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

3. አዳማ ከተማ፦ የአዳማ ከተማ እና የወንጂ ከተማን በመቀላቀል በ6 ክ/ከተሞች እና በ19 ወረዳዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

4. ሮቤ ከተማ፦ የሮቤ ከተማ እና የጎባ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

5. ማያ ከተማ፦ የሀረማያ ከተማ፣ የአወዳይ ከተማ እና የአዴሌ ከተማን በመቀላቀል በ3 ክ/ከተሞች እና በ12 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

6. ባቱ ከተማ፦ የባቱ ከተማ እና የአዳሚ ቱሉ ከተማን በመቀላቀል በ7 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ሆኗል፤

ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሚከተሉት ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡

1. መቱ ከተማ
2. አጋሮ ከተማ
3. ቡሌ ሆራ ከተማ
4. ነጆ ከተማ
5. ሰንዳፋ በኬ ከተማ
6. ሸኖ ከተማ
7. ሞያሌ ከተማ
8. ዶዶላ ከተማ
9. ሻክሶ ከተማ

ከዚህ ባለፈ የሚከተሉት ከተሞ ደረጃ እንደሚከተለው እንዲሻሻል ተወስኗል።

1. አዳማ፣ ሻሻመኔና ቢሾፍቱ ከተሞች፡- የሬጂዮ-ፖሊስ ከተማ

2. የሮቤ ከተማና የማያ ከተማ፡- ዋና ከተማ

3. የመቱ፣ አጋሮ፣ ቡሌ ሆራ፣ ነጆ፣ ሰንዳፋ በኬ፣ ሞያሌና ሻክሶ ከተማ፣- ወደ ከፍተኛ ከተማነት እንዲያድጉ ተወስኗል።

በሌላ በኩል የምስራቅ ቦረና ዞን አዲስ ዞን ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል፡፡

በአዲስ መልክ 21ኛ ዞን ሆኖ የተደራጀው የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና ከተማው ነጌሌ ቦረና ሆኖ፡-
• ከቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ፣ ሞያሌ ከተማ፣ ጉቺ ወረዳ እና ዋችሌ ወረዳ፣
• ከጉጂ ዞን ሊበን ወረዳ፣ ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ፣ ነጌሌ ቦረና ከተማ፣
• እንዲሁም ከባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ፣ ኦቦርሶ ወረዳ እና ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በመጨመር እንደ ዞን 10 ወረዳዎችን በመያዝ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጂ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል።

የመደ ወላቡ ወረዳ ደግሞ በሁለት ቦታ ማለትም የመደ ወላቡ ወረዳና ኦቦርሶ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅና የጭናክሰን ወረዳ የነበረው በሁለት ወረዳ የጭናክሰን ወረዳና የመከኒሳ ኦሮሞ ወረዳ ሆኖ እንዲደራጅ ተወስኗል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/OBN-02-27

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
#ቦረና

" በቡድንም ሆነ በተናጠል ድጋፍ መሰብሰብ አይቻልም " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ድጋፍ ለማድረግ በቡድንም ሆነ በተናጠል መሰብሰብ እንደማይፈቀድ የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሳሰበ።

የክልሉ መንግስት ፤ በክልሉ አንዳንድ ዞኖች በተለይ በቦረና ዞን በተከታታይ አምስት የዝናብ ወቅት ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ ድርቅ መከሰቱ አስታውሷል።

በተከሰተዉ ድርቅ ምክንያትም መንግስት ባቀረበዉ ጥሪ መሠረት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች በተለያዩ መንገዶች በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እየተሰበሰበ ይገኛል ብሏል።

ከዚህ በኋላ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ወይም ከኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ እዉቅና ዉጭ #በቡድንም ሆነ #በተናጠል ድጋፍ ማድረግ የማይፈቀድ መሆኑን አሳስቧል።

ይህም የሚሰበሰበዉን ድጋፍ በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ፍትሓዊ በሆነና ግልፅነት ባለዉ መንገድ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ውሳኔ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
አንጋፋዋ አርቲስት ሀሎ ዳዌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

አርቲስት ሀሎ ዳዌ በኦሮሞ የኪነጥበብና የትግል ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑ አርቲስቶች አንዷ ናት።

አርቲስት ሀሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ብትቆይም ማገገም ባለመቻሏ ዛሬ በአዳማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ከ #ኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia