TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዛሬው የክልል መንግስታት መግለጫ !

ዛሬ የክልል መንግስታት #ተመሳሳይ_አይነት ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አውጥተዋል።

እስካሁን ድረስ መግለጫቸውን ለህዝብ ያሰራጩት ፦

- የሶማሌ ክልል
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል
- የደቡብ ክልል
- የሐረሪ ክልል
- የጋምቤላ ክልል መንግስታት ሲሆኑ በመግለጫቸው " በተገቢው አካል ያልተፈቀደ እና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ሰላማዊ ሰልፍ " የተከለከለ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫ ፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ችግር የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና መሰረት ባደረገ ውስጠ ደንብ / ውስጣዊ አሰራር ሊፈታ ይገባል የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል።

" በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከሃይማኖት ጉዳይነት አልፎ እየተወሳሰበና በርካታ እኩይ ዓላማ ያላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ የፓለቲካ ኃይሎች ተቀናጅተው ኢትዮጵያን ለማዳከም ርብርብ እያደረጉ ናቸው " ያሉት የየክልሉ መንግስታት " ይህንንም በመረጃና በማስረጃ አረጋግጠናል ብለዋል።

በዚህም " ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሀገርና የህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውንም እንቅሳቃሴ እንቃወማለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በተገቢው አካል ያልተፈቀደና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግም ተገቢነት ያለው ጉዳይ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫቸው ፤ ህገ መንግስቱንና የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ውሳኔን መሰረት በማድረግ ማንኛውንም ሕገወጥ እንቅስቃሴ በመከላከልና በመቆጣጠር ህግ የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ አስገንዝበዋል።

(መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሰበር_መረጃ

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አስቸኳይ ሰበር መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች 72 ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት ፤ ቀኖናና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ይፋዊ ጥሪ ማስተላለፏን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዳሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል።

ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ላልተጋባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ለሕዝቡ የሚያመጣው መፍትሔ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አሳውቋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_መረጃ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አስቸኳይ ሰበር መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች 72 ሰዓታት…
#በትዕግስት_ተጠባበቁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማሳስቢያ !

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፤ ሕዝበ ክርስቲያኑ አባቶች #የደረሱበትን_ውጤት_እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት ይጠባበቅ ዘንድ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰሞኑን ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በተለያዩ ቦታዎች እየተፈጠሩ ያሉ ክስተቶች እና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን በቅርበት በመከታተል እንዲሁም ሁሉንም ወገኖች እና የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ለችግሩ እልባት ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው ባደረገው ክትትልና ምርመራ አዲስ "ቤተ ክህነት" አቋቁመናል በማለት ያሳወቁት ቅዱስ ሲኖዶስ ማዕረጋቸውን ያነሳባቸው ጳጳሳት በአንዳንድ ቦታዎች በኃላፊዎች ድጋፍ ጭምር በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን መያዛቸውን ገልጿል።

ጥር 27/2015 የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ለመያዝ ያደረጉትን እንቅስቃሴ ተከትሎ እርምጃውን ለመቃወም የወጡ ሰዎችን ለመበተን በመንግሥት ጸጥታ አባላት በተወሰደ #ተመጣጣኝ_ያልሆነይል እርምጃና ከጸጥታ አባሎቹ ጋር ሲተባበሩ በነበሩ ሰዎች ቢያንስ 8 ሰዎች በጥይትና በድብደባ መገደላቻውን ኮሚሽኑ ማረጋገጡ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ኃላፊዎች በሻሸመኔ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 13 መሆኑን እንደገለፁለት አስረድቶ ይህን የማጣራት ሂደቱ እንደቀጠለ ነው ብሏል።  

ቁጥራቸው ገና በትክክል ያልታወቀ ሰዎች ለተለያየ ዓይነትና መጠን የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን እንዲሁም በርካታ ሰዎች ለተለያየ ጊዜ መጠን መታሰራቸውን አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በተለያዩ ቦታዎች አዲስ " ቤተ ክህነት " አቋቁመናል በማለት ያሳወቁትን ጳጳሳት በተቃወሙ ሰዎችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ ከቤተ ክርስቲያናት ማባረር፣ የመንቀሳቀስ መብትን በኃይል መገደብ እና ከሕግ ውጭ እስራት እንደተፈጸመ ገልጿል።

(ከኢሰመኮ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሰሞኑን ከኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በተለያዩ ቦታዎች እየተፈጠሩ ያሉ ክስተቶች እና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችን በቅርበት በመከታተል እንዲሁም ሁሉንም ወገኖች እና የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ለችግሩ እልባት ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ዛሬ በላከልን መግለጫ አሳውቋል። ኮሚሽኑ በመግለጫው ባደረገው ክትትልና ምርመራ አዲስ …
ከኢሰመኮ መግለጫ ፦

" ... በመንግሥት የጸጥታ አባሎች ተመጣጣኝ ባልሆነ ኃይል አጠቃቀም በጥይት እና በድብደባ የተፈጸሙ ግድያዎች፣ ከሕግ ውጭ የተፈጸሙ እስሮችና የእንቅስቃሴ ገደቦች፣ እንዲሁም ሲኖዶሱ ያቀረበውን የጥቁር መልበስ ጥሪ የተቀበሉ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ እስሮች፣ ከአገልግሎት እና ከሥራ ቦታ ማግለልና ማንገላታት ፍጹም ተገቢ ያልሆኑ እና የዜጎችን በሕይወት የመኖር፣ በነጻነት ሃይማኖታቸውን እና ሐሳባቸውን የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን የሚፃረሩ #የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶች ናቸው፡፡

ስለሆነም መንግሥት የተሟላና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ እና የተጎዱትንም ሊክስ ይገባል፡፡

በተጨማሪም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ተቃውሞ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ኃይል ከመጠቀም፣ ከማንገላታት፣ ከሕገ ወጥ እስር እና የሰዎችን እንቅስቃሴ ያለበቂ ምክንያት ከመገደብ መቆጠብ ይኖርባቸዋል፡፡

በተጨማሪ #በማኅበራዊ_ሚዲያና በሌሎችም መገናኛ ብዙኃን የሚሰራጩ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ሥጋቱን የሚጨምሩ በመሆናቸው በሁሉም አካላት ኃላፊነት የተሞላው የሚዲያ አጠቃቀም ያስፈልጋል። "

(ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/76425?single

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

የኢትዮጵያ መንግስት " ኢትዮ ቴሌኮም " ን በከፊል ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር በድጋሚ ዓለም አቀፍ ጨረታ አወጣ።

አሁን የወጣው ጨረታ የኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ለዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ለማቅረብ ያለመ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ኩባንያዎች የማይመለስ 20 ሺህ ዶላር እና መተማመኛ በ13 ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንደሚችሉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት #የዕግድ ትዕዛዝ መስጠቱ ተገለፀ።

ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ አውግዛ በለየቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በዚህ ጉዳይ የቤተክርስቲያኗ የህግ ክፍል ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#በትዕግስት_ተጠባበቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማሳስቢያ ! ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፤ ሕዝበ ክርስቲያኑ አባቶች #የደረሱበትን_ውጤት_እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት ይጠባበቅ…
#Update

የኢ/ኦ/ተ/ቤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ይህን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ይሰጣል።

@tikvahethiopia