TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቱርክ #ሶሪያ በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ከተሞች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል። በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት…
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ መሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ7,300 አልፈዋል።

በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7,300 ማለፉን ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የኢትዮጽያ የሚድያ ህግ ከሴቶችና ህጻናት መብቶች አንጻር በሚል ርዕስ ከሚድያ አካላት እና ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ የኢትዮጵያ የሚድያ አዋጅና ድንጋጌዎቻቸው ከሴቶች እና ህጻናት ጥበቃ አንጻር የተቀመጡት ድንጋጌዎች የቀረቡ ሲሆን ቢሮው የሰራቸውንና በመስራት ላይ ያለው ስራ ቀርቧል።

ቢሮው ፦
👉 ለዓመታት ስትደፈር ስለቆየች ሴት፤

👉 በአባታቸው ስለተደፈሩ ልጆች፤

👉 ተገለው በመንገድ ስለተጣሉ ልጆች እና  ሌሎችም በመዲናዋ (አዲስ አበባ) የተከሰቱ ዘግናኝ ኬዞችን እየተከታተለ እንዳለ አሳውቋል።

#አንዳንድ ሀኪሞች፣ መምህራን፣ መንገደኞች ፣ ሚድያዎች እና ሌሎችም በሴቶችና ህጻናት ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ መካከል እንደሚመደቡም ተነግሯል።

በመድረኩ በሀገሪቱ የሚሰሩ ፊልሞችና ማስታወቂያዎች ለአብነትም የዳይፐር፣ የሳሙና፣ የማድ ቤት እቃዎችና ሌሎች ማስታወቂያዎች ላይ የሚሰሩት ሴቶች መሆናቸውን በመጠቆም የማስታወቂያዎቹ አሰራርም የሴቶችን አቅም የሚያዳክምና መሰል ኃላፊነቶች የእነሱ ብቻ መሆናቸውን አመልካች በመሆኑ ሊስተካከል እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም የኪነጥበብ ስራዎች የሴቶችና ህጻናትን መብቶች የሚያከብሩ እና ክብራቸውን የሚጠብቁ ሊሆኑ እንደሚገባና ሚድያውም የራሱን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#ኢንሹራንስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርግ በሕግ የተሰጠውን ሰልጣን በማሻሻል፣ የኢንሹራንስ ዘርፉ ከብሔራዊ ባንክ ውጪ ራሱን በቻለ ገለልተኛ ባለሥልጣን ቁጥጥር እንዲደረግበት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ሪፖርተር አስነብቧል።

በዚህም መሠረት የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጣጠርና የሚከታተል ገለልተኛ ተቋም ለማቋቋም አማካሪ ተቀጥሮ ሥራ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ሥራ ተጠናቆ ተቋሙ ከተመሠረተ በኋላም የኢንሹራንስ ዘርፍ #ለውጭ ኩባንያዎች ውድድር ክፍት እንደሚሆን ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞኑን እንዳስታወቀው የኢንሹራንስ ሪጉላቶሪ ኤጀንሲ ራሱን የቻለ ገለልተኛ ኤጀንሲ እንዲኖረው በመንግሥት በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ኤጀንሲውን ለማቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ " የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዲገቡ እንደተፈቀደው ሁሉ ለኢንሹራንስ ዘርፉም ሊከፍት ይገባል " በሚል የሚቀርበው ተደጋጋሚ ጥያቄ አግባብ ቢሆን መጀመርያ ሊሠሩ የሚገባቸው ሥራዎች ስላሉ ይህ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ ዕርምጃ በዘርፉ የውጭ ኩባንያዎችን መጋበዝ ይሆናል ብሏል።

የኢንሹራንስ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲው ሳይቋቋም የውጭ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የማይፈቀድ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጠቆሙን ሪፖርተር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ከተማ በምታስተናግደው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ የሞተር ብስክሌት እና የባጃጅ እንቅስቃሴ መከልከሉ ታውቋል።

የከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ፤ " 36ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማችን ሞተር ብስክሌት እና የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ክልከላው ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 5/2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ፀንቶ ይቆያል ተብሏል።

ሞተር ብስክሌቶች ከዛሬ የካቲት 1/2015 ዓ.ም  ጀምሮ ስበስባድ እስኪጠናቅ የካቲት 13/2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌትን ማሽከርከር ፍጹም የተከለከሉ መሆኑ ተገልጿል።

ክልከላ የሚመለከተው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር ስራ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ ነው ተብሏል።

ክልከላድ በአዲስ አበባ ከተማ #በሁሉም አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ባጃጆችን፣ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶችን በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን ጭምር በሙሉ የሚያካትት መሆኑ ተመላክቷል።

የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች፣ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ይሄንኑ ክልከላ መሰረት በማድረግ እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል።

ክልከላድን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ኤጀንሲው አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በቱርክ እና ሶሪያ መሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ7,300 አልፈዋል። በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አሁን ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ7,300 ማለፉን ባለስልጣናት አሳውቀዋል። ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል። @tikvahethiopia
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,000 ደረሰ።

ሰኞ በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11,000 መድረሱን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከ11 ሺህ ሟቾች መካከል በትንሹ ከቱርክ 8,574 ሲሆኑ ከሶሪያ ደግሞ 2,530 ሆነው መመዝገባቸው ተመላክቷል።

ሰዎችን ከህንፃ ፍርስራሾች ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ተነግሯል።

#አልጀዚራ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው። ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል። ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ…
" ቤተ ክርስቲያኗ ቡድኑ ለጊዜው በአመልካች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች ፣ቅጥር፣ቅርስና ዐብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርስ እግድ እንዲሰጥ ነው የጠየቀችው " - ጠበቃ አንዷለም በእውቀቱ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የክስ ሂደት መጀመሯ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያኗ አውግዛ የለየቻቸው ፣ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙት የቀድሞ ሥስት ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ሹመቱን የተቀበሉ አካላት ወደ አብያተ ክርስቲያናት ከመግባት እንዲታገዱ ያቀረበችው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው ጉዳዩን የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት ነው።

የቤተክርስቲያኗ የጠበቆች ቡድን አባላት ዛሬ ብይን ለመስማት ቢቀርቡም እገዳ እንዲጣልበት ጥያቄ የቀረበበት ቡድን ጠበቃ መሆኔ አይቀርም ብለው በችሎቱ የቀረቡት ግለሰብ እግድ ከተጠየቀባቸው ወገኖች ሕጋዊ የጥብቅና ውክልና ይዘው የካቲት 3 ቀን 2015 ዓም ለክርክር ይቅረቡ ሲል ፍርድ ቤት መቅጠሩን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ከቤተክርስቲያኗ ጠበቆች አንዱ የሆኑትን አቶ አንዷለም በእውቀቱ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አቶ አንዷለም ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቡድኑ ለጊዜው በአመልካች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ንብረቶች ፣ቅጥር፣ቅርስና ዐብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንዳይደርስ እግድ እንዲሰጥ ነው የጠየቀችው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ያወጀው ጾምና ጸሎት ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ያበቃል።

ቅዱስ ሲኖዶስ " ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ " ሲል ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ምዕመኑን ይህንኑ ተግባራዊ ሲያደርግ ነበር።

ቤተክርስቲያኗ ፤ " ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው " ማለቷ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በጸሎትና በምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰልፍ ይደረጋል ያለው በየካቲት 5/2015 ዓ.ም ሲሆን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ፤ ቤተክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዲሁም እየተፈፀመ ያለው ህገወጥ ድርጊት ለዓለም ህዝብ የሚገለፅበት እንደሆነ ማስረዳቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የፀጥታና ደኅነት የጋራ ግብረ–ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገሙን ገልጿል።

አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለኝ ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ " በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ " ብሏል።

ግብረሃይሉ ሰልፎቹ በሃይማኖቱ ሽፋን የሚደረጉ እና ሕገወጥ ሰልፎች ናቸው ያለ ሲሆን " በሚመለከተው አካል የተፈቀደ ሰልፍ የሌለ መሆኑ ታውቆ ኅብረተስቡ ከዚህ ሕገ ወጥ ሰልፍና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት ራሱን ይጠብቅ " ብሏል።

የጋራ ግብረ-ኃይሉ " ከዚህ ውጭ ሰልፍ አደርጋለሁ ብሎ በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ኃይል እንዲሁም ሰልፎቹን ለማስተባበር እና ለመሳተፍ የሚሞክሩ አካላት ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት ተጠያቂ ናቸው " ያለ ሲሆን " ለዜጎችና ለሀገር ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ሲባል ሕጋዊእርምጃ ይወሰዳል " ሲል አስጠንቅቋል።

ግብረ ኃይሉ " በየክልሉ የምትገኙ የፀጥታ ኃይሎችም በአካባቢያችሁ ሕገወጥ ሰልፎች እንዳይካሄዱ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያኗ፣ለእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች በአጠቃላይ ለሕዝቡ ተገቢውን የደኅንነት ጥበቃ እንድታደርጉ " ሲል አዟል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,000 ደረሰ። ሰኞ በቱርክና ሶሪያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11,000 መድረሱን አልጀዚራ ዘግቧል። ከ11 ሺህ ሟቾች መካከል በትንሹ ከቱርክ 8,574 ሲሆኑ ከሶሪያ ደግሞ 2,530 ሆነው መመዝገባቸው ተመላክቷል። ሰዎችን ከህንፃ ፍርስራሾች ውስጥ ፈልጎ የማውጣቱ እንዱሁም የነፍስ አድን ስራው አሁንም መቀጠሉ…
#Update

በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር 11,600 በላይ ሆኗል።

አስከፊ በሆነው የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክ ከ9 ሺህ በላይ ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን ዛሬ ሩቡዕ የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባቸዋል የተባሉትን ስፍራዎች በአካል ሄደው ተመልክተዋል።

ኤርጎዳን እና መንግስታቸውን ለእንዲህ መሰል አስከፊ አደጋ ቅድመ ዝግጅት አላደረገም ፤ ከአደጋውም በኃላ የታየው ምላሽ ደካማ ነው በሚል በተቃዋሚ ኃይሎች እንዲሁም በሌሎች ትችት እየተሰነዘረባቸው ይገኛል።

አንዳንድ የተቃዋሚ አመራሮች ለዚህ ሁሉ ከፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ውጭ ማንም ተጠያቂ አይደለም እስከማለት ደርሰዋል።

ነገር ግን ፕሬዜዳንቱ ይህንን ትችት የማይቀበሉት ሲሆን " ይህ ጊዜ የአንድነት እና የአብሮነት ጊዜ መሆን አለበት " ብለዋል።

በዚህ ጊዜ ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ አሉታዊ ዘመቻዎችን ለሚያደርጉ ሰዎች ቦታ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከተከሰተ በኃላ በመንግስት በኩል የተሰጠው የአደጋ ጊዜ ምላሽ ከተቃዋሚ ኃይሎች ባለፈ በርካቶችን እንዳስቆጣ የተነገረ ሲሆን ኤርዶጋን ከአደጋው በኃላ የመጀመሪያ ቀን ምላሽ ወቅት ችግሮች /መዘግየት እንደነበሩ አምነዋል፤ ነገር ግን መዘግየቱ በተበላሹ መንገዶች እና የአውሮፕላን ማረፊያዎች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።

ሁለተኛው ቀን እና ዛሬ ችግሮች ታርመው ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር መሆኑን ተናግረዋል።

ኤርዶጋን የሀገሪቱ ዜጎች የባለስልጣናትን መልዕክት እንዲያዳምጡ ከዛ በዘለለ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ አሉታዊ መልዕክት የሚያሰራጩትን ችላ እንዲሉ ጥሪ አቅርበዋል፤ የሀገሪቱ መንግስት መስራት ያለበትን ስራ እየሰራ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia