TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በህግ ማስከበር ስም የድሆችን ቤት እና ቤተ እምነቶችን ማፍረስ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " - ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በአዲስ መልክ በመደራጀት ላይ ባለው " ሸገር ከተማ " ባለፉት ጥቂት ወራት ህገ ወጥ ግንባታዎችን ለመከላከል በሚል በተወሰደው እርምጃ በርካታ ቤቶች በመፍረስ ላይ እንዳሉ እንደሚታወቅ እና እርምጃው ዛሬም ድረስ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

ፓርቲው እየተወሰደ ባለው እርምጃ በርካታ ቤቶች እንዲፈርሱ የተደረገ መሆኑንና በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሚያሳዝን ሁኔታ ጎዳና ላይ እንዲወድቁ መደረጉን አመልክቷል።

እርምጃው ቤታቸው በፈረሰባቸው ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና እንግልት ከማሳደሩም ባሻገር፣ የማፍረስ ሂደቱ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ ቀስቅሷል ሲልም አክሏል።

ነእፓ ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጫለሁ እንዳለው ቤት የማፍረስ እርምጃው ህጋዊ ፍቃድ የሌላችውን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ህጋዊ ሰነድ ያላቸውን ዜጎች ጭምር ሰለባ ያደረገ መሆኑና ይህም ቤት የማፍረስ እርምጃው ዓላማ ግልጽነት የጎደለው እንዲሆን ማድረጉን ገልጿል።

" የማፍረስ እርምጃው ከዜጎች የመኖሪያ ቤት በተጨማሪ የእምነት ተቋማትን ኢላማ ያደረገ ነው " ያለው ነእፓ " በዚሁ ሳቢያ በርካታ #መስጂዶች መፍረሳቸው ተረጋግጧል፡ " ብሏል።

ይህ እርምጃ ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ተጠያቂነት የጎደለው ተግባር ከመሆኑ ባሻገር የእምነት ተቋማትን ክብር ያጎደፈ እና መንግስት ለምእመኑ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ሲል ገልጿል።

ነእፓ ፤ " አብዛኛው የሀገራች ህዝብ በአስከፊ ድህነት ውስጥ እየኖረ ባለበት፣ የእለት ጉርስ እና የአመት ልብስ ማግኘት ህልም በሆነበት፣ ዳቦ፣ ዘይት እና ስኳር ቅንጦት በሆነበት፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በጦርነት እና በግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ባሉበት ሀገር ያለ በቂ ጥናት እና ዝግጅት የዜጎችን ቤት በጅምላ ማፍረስ በህግም ሆነ በሞራል ተቀባይነት የሌለውና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ብሏል።

" በሀገራችን ተንሰራፍቶ በቆየው ብልሹ አስተዳደር ሳቢያ፣ እንዲሁም መንግስት የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ ባለመቻሉ፣ ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ከጸሀይ ሀሩር እና ከክረምት ዝናብ የሚከልሉበት ጎጆ እንዲቀልሱ ተገደው ኖረዋል " ያለው ፓርቲው " በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች በመንግስት #ደካማ እና #በሙስና የተጨማለቀ አሰራር ምክንያት ዜጎች ለበርካታ አስርት አመታት ህጋዊ ይዞታ የሚያገኙበት ስርአት ሳይዘረጋላቸው ቆይቷል " ሲል ገልጿል።

ይህንን የመንግስት እንዝላልነት እና ብልሹ አሰራር ህግ እና ስርአት በጠበቀ መልኩ ማስተካከል ሲገባ፣ ዜጎች በሀብታቸው፣ በንብረታቸው እና በህይወታቸው ዋጋ እንዲከፍሉ ማድረግ ሰብአዊነት እና ኃላፊነት የጎደለው ታሪካዊ ስህተት ነው ብሏል።

" ቤት ማፍረሱ ሳያንስ፣ ዜጎች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ጎጆ በቂ ጊዜ እና አማራጭ የመኖሪያ ስፍራ እንዲያገኙ እድል ሳይሰጥ ' በጊዜ የለንም ' ፍጥነት ከመኖሪያ ደጃቸው እንዲነሱ የተደረገበት አሰራር ሂደቱን ይበልጥ አሳዛኝ፣ አሳሳቢ እና አጠያያቂ አድርጎታል " ያለው ነእፓ በአዲሱ የሸገር ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው ቤት የማፍረስ ዘመቻ ፦
- በቂ ህጋዊ መሰረት የሌለው፣
- ከፍተኛ የአፈጻጸም ክፍተት ያለበት ፣
- የክልሉን ብሎም የሀገራችንን አሁናዊ የጸጥታ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ድርብርብ ችግሮች እና ሀቆች በቅጡ ያላገናዘበ በመሆኑ #በአፋጣኝ_እንዲቆም አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia