TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Grade12NationalExam

ከዚህ ቀደም በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ ሲሰጡ ከነበሩ የትምህርት አይነቶች መካከል ሥነ ምግባርና የሥነ ዜጋ ትምህርት (Civics and Ethical Education) በዘንድሮው ዓመት 2016 ዓ/ም #አይሰጥም

የሥነምግባር እና ሥነ ዜጋ ትምህርት (Civics and Ethical Education) ፈተና ያልተካተተው በሁለቱም የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ነው።

ይህ ፈተና ለምን በብሄራዊ ፈተናው ላይ እንዳልተካከተተ / እንዳይካተት ውሳኔ እንደተለለፈ ትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ የለም።

በሌላ በኩል ፤ ባለፉት ዓመታት ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሳይሰጥ የቆየው #የኢኮኖሚክስ ትምህርት በዚህ ዓመት 2016 ፈተና ላይ ተካቷል።

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እኩል ስድስት ትምህርቶችን ይወስዳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ፤ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ ፣ ፊዚክስ ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ሶኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ፈተና ሲወስዱ የማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ ፣ ጂኦግራፊ ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

በዚሁ ዝርዝር መሰረት ከሁለቱም ዘርፎች የሥነ ዜጋና ሥነምግባር (Civics and Ethical Education) ትምህርት የወጣ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ላይ ባለፉት ዓመታት ሳይሰጥ የቀረው ኢኮኖሚክስ ተካቷል።

ፈተናው የሚሰጥበት ትክክለኛውና ቁርጥ ያለው ቀን ባይታወቅም እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ዓመታት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (#ዩኒቨርሲቲዎች) በማስገባት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Grade12NationalExam

በ2016 የ12ኛ ክፍል ፈተና የሥነዜጋ እና ሥነምግባር ትምህርት የማይሰጥ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ሳይሰጥ የቆየው ኢኮኖሚክስ ዘንድሮ ይመለሳል።

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ ከቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

" በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ምክንያት 12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ የሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ተማሪዎቹ እንዲይዙት የሚፈለገውን ፦
* እውቀት፣
* ክህሎት
* ባህሪያት መቅሰማቸው የሚፈተኑበት ይሆናል።

የሥነ ዜጋ እና ሥነ ምግባር ትምህርት በ12ተኛ ክፍል ፈተና ላይ እንዳይሰጥ የተደረገው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ምክንያት ትምህርቱ ከ10ኛ ክፍል በኋላ ስለማይሰጥ ነው።

ኢኮኖሚክስ ከዚህ ቀደምም ይሰጥ ነበር። መሃል ላይ የሆኑ የጥናት ሃሳቦች ተነስተው ከፈተና እንደወጣ እናውቃለን፤ አሁን ግን ወደ ሥርዓተ ትምህርቱ ተመልሷል፤ መጽሐፍ ታትሞለታል። እንዲማሩ እየተደረገ ካለው ጥረት አንጻር ወደ ፈተና ቢገባ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።

የዘንድሮ ፈተና መቼ ይሰጣል ? ለሚለው ፤ ከክልሎች ጋር ምክክር እያደረግን ነው። በቅርቡ እናሳውቃለን። "

@tikvahethiopia
#Grade12NationalExam

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞ ምዝገባ በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል።

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ምን አሉ ?

- የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት የመመዝገቢያ መስፈርቱን ማሟላት አለባቸው። በተቀመጠው የጊዜ ገድብ ውስጥም መምዝገብ አለባቸው።

- ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / አማካኝነት ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም
ይሆናል።

- በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው ብለዋል ፦

1ኛ. ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ አለባቸው። ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ።

2ኛ. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል አለባቸው።

3ኛ. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ አለባቸው።

4ኛ. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት ይሆናል።

5ኛ. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወርዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች ይሆናል።

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia