TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አፈ ጉባኤዋ ይቅርታ ጠየቁ!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት #ዋና_አፈ_ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት #ይቅርታ ያድርግልኝ ሲሉ በይፋ ጠየቁ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረውን የክልሉን አምስተኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ላለፉት አስራ አንድ ወራት የምክር ቤቱን መደበኛ ጉባኤዎች ባለመጥራቴ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ይቅርታ ያድርጉልኝ ሲሉ ተማፅነዋል።

የህዝብ ውክልና ያለው ምክር ቤት በየጊዜው ማከናወን የነበረበትን ስብሰባ አለማድረጉ በየትኛውም መመዘኛ #ትክክል አይደለም ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ በቀጣይ ተመሳሳይ #ስህተት እንደማይደገም በምክር ቤቱ ፊት ቃል እገባለሁ ብለዋል። በእርግጥ እንደምክንያት ማቅረብ ባይቻልም ምክር ቤቱ ማድረግ የነበረበትን መደበኛ ጉባኤዎች ሳያካሂድ የቀረው ክልሉ አጋጥሞት ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ የተነሳ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዓመት #አራት መደበኛ ጉባኤዎችን ማድረግ የሚገባው ቢሆንም ባለፈው የጥቅምት ወር የመጀመሪያውን ስብስባ ካደረገ ወዲህ ዳግም ሳይሰበሰብ ነው የበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው። በዚህም ምክንያት የክልሉ ዓመታዊ በጀት እስከአሁን ባለመፅደቁ የአስፈጻሚ ቢሮዎች ከሀምሌ 1 2012 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስራዎቻቸውን በምክር ቤት ባልጸደቀ በጀት ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia