TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዋሪዎችን ያማረሩት ጫኝ እና አውራጆች ፦ ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፦ " ... በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በሁሉም ሰፈር ማለት ይቻላል በህገወጥ ጫኝና አውራጆች በሚጠየቅ የተጋነነ ክፍያ ምክንያት ዕቃ መኪና ላይ መጫንም ሆነ ማውረድ አዳጋች ሆኗል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህ ህገ ወጦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ሊታደግ ይገባል። ሰው ተሰቃይቷል ፤ ህዝቡ ተበሳጭቷል ፤ ጉረቤትህ እና ልጆችህ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ጫኝና አውራጆች ያለአግባብ ገንዘብ በመጠየቅ ነዋሪዎችን እያማረሩ ነው።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በመዲናዋ ከሚገኙ የጫኝና አውራጅ ማህበራት ጋር ምክክር አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ዳይሬክተር ኮማንደር ሰለሞን ፋንታሁን ህብረተሰቡ ንብረቱን ከቦታ ቦታ ሲያንቀሳቅስ በጫኝና አውራጅ ያለአግባብ ገንዘብ እየተጠየቀ በመሆኑ ነዋሪዎች ለምሬት ተዳርገዋል ብለዋል።

ንብረቱ ከሚገዛበት ዋጋ በላይ ህብረተሰቡ እንዲከፍል እየተጠየቀ መሆኑ ንብረታቸውን በለሊት ፈረቃ እንዲያጓጉዙ ተገደዋል ሲሉም ገልፀዋል።

ጫኝና አውራጆች ያልተደራጁበት ቦታ ላይ በመምጣት እናወርዳለን በማለት ግጭት የሚፈጠርበት ሁኔታ መኖሩን አክለዋል፡፡

አቅመ ደካሞች ገንዘብ የለንም ሲሉ ፍቃደኛ አለመሆን በጉልበት ለማስገደድ መሞከር፣ጠጥተው በመምጣት ከማህበረሰቡ ጋር መጋጨት፣ ገንዘብ አስገድዶ መቀበል የሚሉት ዋናነት የሚታዩ ችግሮች መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡

በህጋዊ መንገድ የተደራጁ ጫኝና አውራጆች ደግሞ ከስራ አድል ፈጠራ ባሻገር #መብትና_ግዴታቸውን_ያለማወቅ ችግር እንዳለባቸዉ የጠቀሱት ኮማንደር ሰለሞን መሰል ሕገወጥ ድርጊቶችን መከላለል የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ ህብረተሰቡም ሊተባበር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ በተካሄደው መድረክ በከተማዋ 1072 ህጋዊና 577 ህገወጥ ጫኝና አውራጅ ማህበራት ይገኛሉ መባሉን አዲስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

#ማስታወሻ ፦ ያልተገባ ስራ የሚሰሩ ጫኝ እና ወራጆችን ወደ ህግ ከማቅረብ ይልቅ #ተስማሙ የሚሉ የፖሊስ አባላትን ህብረተሰቡ ሲመለከት በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና በ 0111110111 በመደወል ለፖሊስ መጠቆም ይቻላል።

@tikvahethiopia