TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GetachewKassa

በይበልጥ " ሀገሬን አትንኳት " ፣  " ውብ አዲስ አበባ " ፣ " የከረመ ፍቅር " በተሰኙት ዘመን አይሽሬ የሙዚቃ ስራዎች የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ድምፃዊ ጌታቸው ባደረበት ህመም የካቲት 12 ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሀገሬን አትንኳት ...

" የብዙሃን እናት መጠጊያ የምንላት
እማማ ናትና ሀገሬን አትንኳት።

በዓድዋ በማይጨው ጀግኖች የሞቱላት
ህፃን ሽማግሌ የተሰየፈላት
ደመ መራራና ቁጡነት ያለባት
ጎጆዬ ናትና #ኢትዮጵያን አትንኳት !

ዘርዓይ ደረስ ወንዱ በሮሞ የቆመላት
ጀግኖች በጦር ሜዳ ወጥተው የቀሩላት
እኔም በተጠንቀቅ አለሁሽ የምላት
ጥቁሯን አፍሪካዬን ኢትዮጵያን አትንኳት። "

NB. አንፋጋው ድምፃዊ ጌታቸው የተጫወተው ' ሀገሬን አትንኳት ' የተሰኘው ዘመን አይሽሬ ስራ በአንጋፋው ደራሲና ገጣሚ ጋሽ አበራ ለማ የተፃፈ ነው።

@tikvahethiopia