TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ኩራት - በአምላክ ተሰማ👍

የ2019 አፍሪካ ዋንጫ ታላቁን የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሴኔጋል ከ ቱኒዚያ ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት 120 ደቂቃዎቹን በሚገባ መርተዋል። በ90 ደቂቃ የጨዋታ ጊዜ 2 የፍፁም የቅጣት ምቶች ለሁለቱም ሰጥተዉ ወደ ጎል ከመሆን ከሸፈዋል። ሆኖም ሴኔጋል በጭማሪዉ 30 ደቂቃዎች ባስቆረዉ 1 ጎል ጨዋታዉ በሴኔጋል 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቌል። በአፍሪካም ሆነ በአለም ደረጃ በአሁኑ ሰአት #ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማ ከፍተኛ የዳኝነት ደረጃ መድረሳቸውን በምሽቱ ጨዋታም አሳይተዋል።

Via Ethio-Kickoff
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ በችግር ላይ ላሉና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረጉ።

#ኢትዮጵያዊው ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ለመጪው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በወሎ በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ላይ ላሉ እና በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የሚከፋፈል 106 በሬዎችን እና 100 በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አድርገዋል።

ሼይኽ መሀመድ አል አሙዲ ለኡዲሂያ እንዲሆን በማሰብ ድጋፍ ያደረጓቸው በሬዎች ፣በጎች እና ፍየሎች በወሎ በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችም በተለያዩ መስጂዶች እና ተቋማት በኩል እንዲከፋፈል መደረጉ ተገልጿል።

መረጃው የተገኘው ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ ነው።

@tikvahethiopia
" #ኢትዮጵያን በማስጠራቴ ትልቅ ክብር ይሰማኛል " - የወጣቱ የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ ትንሳኤ አለማየሁ

#ኢትዮጵያዊው የሕዋ ሳይንስ ተመራማሪ ወጣት ትንሳኤ አለማየሁ ዓለም አቀፉ የአስትሮኖቲካል ፌደሬሽን የ2023 ወጣት የህዋ መሪዎች ብሎ ከሰየማቸው አምስት ተመራማሪዎች አንዱ ሆኗል።

ፌደሬሽኑ ስያሜውን እውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለሌሎች ወጣቶች በማጋራትና ማህበረሰብ በመድረስ እንዲሁም በትምህርት እና ምርምር ለአስትሮኖቲክ መስክ አበርክቶ ላደረጉ ወጣቶች የሚሰጠው ዕውቅና ነው።

ፌደሬሽኑ ሽልማቱን በባኩ አዘርባጃን በመስከረም 2016 ዓ.ም በሚደረገው በ74ኛው የዓለም አቀፉ የአስትሮኖቲካል ኮንግረስ ለወጣት ተመራማሪዎቹ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በዓለም አቀፉ ፌደሬሽን በወጣቶች ዘርፍ የሚሰጠውን ትልቁን ሽልማት በማግኘቱ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማው ትንሳኤ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።

ሽልማቱን በማግኘት ኢትዮጵያን በማስጠራቱ ትልቅ ክብር እንደሚሰማውም ገልጿል።

በሜካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ከ #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ ያገኘው ትንሳኤ አለማየሁ ፤ ለህዋ ሳይንስ ባለው ራዕይ እና ለዘርፉ ላደረገው አበርክቶ በርካታ ሽልማቶችን አጊኝቷል። 

ካገኛቸው ሽልማቶች ውስጥ ፦

- እ.ኤ.አ. በ2022 ከዓለም አቀፉ የጠፈር ተመራማሪዎች ፌደሬሽን (አይኤኤፍ) የተበረከተውን ተስፋ የተጣለባቸው ስፔስ መሪዎች ሽልማትን፤

- ከ30 አመት በታች የአፍሪካ ስፔስ ኢንዱስትሪ ሽልማት፤

- በ2021 ከስፔስ ኢን አፍሪካ እና ከSGAC የግሎባል ግራንት ፕሮግራም ሽልማትን፤

- በ2019 ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የወጣት ሕዋ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሽልማቶችን እና እውቅናዎችን አግኝቷል።

ወጣቱ ተመራማሪ አሁን ላይ የዓለም ዐቀፉ የህዋ ጄነሬሽን አማካሪ ም/ቤት (SGAC) የአፍሪካ ቀጣናዊ አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

https://www.iafastro.org/news/the-iaf-is-proud-to-introduce-the-2023-iaf-young-space-leaders.html

More : @tikvahuniversity