TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ከእስር የተፈቱት የአመክሮ ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው ነው " - የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴ

ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የኢህአዴግ እና የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ በረከት ስምኦን " የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨርሰው " ዛሬ ጠዋት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት መፈታታቸውን ታውቋል።

ጠበቃቸው ህይወት ሊላይ ፤ የአቶ በረከት ስምኦን ዛሬ ከእስር መፈታታቸውን ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴም ፤ ከጥረት ኮርፖሬሽን የገንዝብ ብክነት ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ክስ የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን የተፈቱት የአመክሮ ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። 

Credit : ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ፦ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በትናንትናው እለት ምሽት 4፡48 ላይ ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ የእሳት አደጋ ደርሶበት ውድመት ደርሷል። የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት ሲሆን ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። የአካባቢው ማህበረሰብ ከአደጋው ጋር ተያይዞ ማንኛውንም መረጃዎች በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ…
" ሰነዶች ከነባሩ ቢሮ ያልተዘዋወሩም " - ክፍለ ከተማው

ከትላንት በስቲያ ምሽት በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ እና ግብዓት ፈሶበታል የተባለው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ለቢሮ አገልግሎት ለመጠቀም አዲስ በተከራየው ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ውድመት መድረሱ ይታወቃል።

ይህ ተከትሎ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች " በቢሮው ሰነዶች ነበሩ እና ሰነዶችም ተቃጥለዋል " የሚል ሀሰተኛ መረጃ እየተሠራጨ ይገኛል ያለው ክፍለ ከተማው ፤ " ህብረተሰቡ ህንፃው ገና አዲስ የተከራየነው እና ለአገልግሎት አሠጣጥ የሚረዱ መሰረተ ልማቶች እየተዘረጉበት የሚገኝ ስለሆነ ምንም አይነት ሰነዶች ከነባሩ ቢሮ ያልተዘዋወሩ መሆኑን ሊያውቅ ይገባል " ብሏል።

" ነዋሪዎች ከሀሰተኛ መረጃዎች እራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
የብርሃን ሞባይል ባንኪንግን (*881#) ተጠቅመው :-
- የዋይፋይና ሌሎችም የኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዎችን በቀላሉ ያከናውኑ!
- የአየር ትኬትዎን ይቁረጡ!
- ቀሪ የብድር መጠንዎን ይወቁ
- ያለ ኢንተርኔት በቀላሉ ገንዘብ ያስተላልፉ!
- በሞባይልዎ የቼክ ደብተር ይዘዙ!
- የት/ቤት ክፍያዎን በቀላሉ ይክፈሉ!
- ከራስዎ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ገንዘብ ያስተላልፉ!
#ብርሃን_ባንክ
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መካሄድ እንደሚጀምር ተገልጿል። አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው ከቀናት በፊት በወሊሶ አካባቢ በብፁዕ አባ ሳዊሮስ መሪነት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ " የኤጲስ ቆጶሳት " ሢመትን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሠረት የሚካሄድ ነው። በብፁዕነታቸው ጥሪ መሰረት ከእሁድ…
#Update

ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ምእመናን የሦስት ቀናት ጸሎት አውጇል።

ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የሚሰበሰብ ሲሆን ከቀናት በፊት ቤተክርስቲያን ሕገ ወጥ ስትል በጠራችው ሹመት ዙሪያ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።

Photo Credit : EOTC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ / ወደ ትግራይ  የየብስ ትራንስፖርት መቼ ይጀምራል ? ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ከሰሞኑን ተገልጿል። ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልል የኮንድትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በህጋዊ…
#Update

ከ/ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት ለመጀመር የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ማህበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል።

ሪፖርተር ጋዜጣ ከአገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ማኅበራት ያገኘሁት ባለው መረጀ ፤ የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወደ ትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎትን ዳግም ለመጀመር ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ መመርያ ተላልፎላቸዋል፡፡

በዚሁ የሚኒስቴሩ መመርያ መሠረት ማኅበራቱ ለአባሎቻቸው አገልግሎቱን መልሶ ለማስቀጠል ዝግጁ እንዲሆኑ ያሳወቁ ሲሆን አሁን እየጠበቁ ያሉትም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ እንደሆነ ለማወቅ መቻሉን #ሪፖርተር_ጋዜጣ ዘግቧል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ  ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ማሳወቁ አይዘነጋም።

ቢሮው ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
Forwarded from Bank of Abyssinia
አፖሎ የተሰኘው ልዩ የዲጂታል መተግበሪያ ለተጠቃሚ ዝግጁ መሆኑን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው።
አፖሎን አውርደው ዛሬውኑ ይጠቀሙ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollo #OurNewProduct #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank, #poweredbybankofabyssinia, #thechoiceforall
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

ይኸው ቡድን 5 አባላት ያሉት ሲሆን በትግራይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው ዛሬ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ፋና ብሮድካስቲንግ የዘገበው።

በትምህርት ሚኒስቴር  የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ፤ " ቡድኑ ወደ መቐለ የሚያቀናው በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ለመምከር ነው " ብለዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ ቡድን በመቐለ ቆይታው ከመቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር ትምህርት ዳግም መጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ገልፀዋል።

በተጨማሪ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ትምህርትን ዳግም ለማስጀመር በሚቻልበባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቅንቶ በዩኒቨርሲቲው ዳግም የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ማድረጉ መጠቆሙን ፋና ብሮክዳስቲንግ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#AddisAbaba

ከ2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሀይሌ ግራንድ አዲስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በይፋ ስራ ጀመረ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በየካ ክፍለ ከተማ ላም በረት መናኽሪያ አካባቢ በ15 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውና ባለቤትነቱ የሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ የሆነው የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ስምንተኛ መዳረሻ " ሀይሌ ግራንድ አዲስ አበባ " ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመሩ ዛሬ ተገልጿል።

2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት "ሃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ" እ.ኤ.አ ከጥቅምት 01/2022 ጀምሮ በሙከራ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ሆቴሉ ለ450 ሰራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለ120 #አዲስ_ተመራቂ ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት ስራ እንዱጀምሩ መደረጉ ተገልጿል።

ሆቴሉ በውስጡ ፦

- 130 ክላሲክ ፤ 14 ስዊት ፤ 12 ፕሪሚየር እና 1 ፕሬዝዳንሻል ባጠቃላይ 175 አልጋዎችን የያዘ 157 ምቹና ሰፊ የመኝታ ክፍሎችን
- 4 ሬስቶራንቶች እና 2 PDR ፤
- 4 ባር፤
- 1pastery & coffe shop፤ 
- 1 የተሟላ የባህል ምግብ አዳራሽ፤
- 8 የስብሰባ አዳራሾች እና 2 ትላልቅ Ballrooms
- የጤና እና የውበት መጠበቂያ ማዕከል
- ጂም እንዲሁም 200 ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ይዟል።

ሆቴሉ የተገነባው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ብቻ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቀጣይ #ሐምሌ ወር ላይ #የወላይታ_ሶዶው ሆቴል እንደሚመረቅ፤ #የሻሸመኔው ሪዞርትም ጥገና ላይ እንዳለ ተገልጿል።

Tikvah Family (Addis Ababa)

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ት ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ለስራ ጉብኝት #ሱዳን፤ ካርቱም ገብቷል።

የስራ ጉብኝቱ ለአንድ ቀን እንደሆነ ተገልጿል።   

የሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Photo Credit : PMOEthiopia

@tikvahethiopia