TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሀገር በቀልና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር 60 ልዑካንን በመያዝ መቐለ ገብቷል። የጉዞው ወነኛ አላማዎች በትግራይ ያለው የሰብአዊ እና መልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ፈተናዎችና ሁኔታዎች በክልሉ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስማትና ለመረዳት ነው። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በስፍራው ስለሚገኙ ሂደቱን እየተከታተሉ ያሳውቁናል።…
#አሁን
አሁን በመቐለ ከተማ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት ልዑክ ከትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል።
የትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህብረት / ACSOT የቦርድ ሊቀመንበር እና የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር ተስፋይ ገብረ እግዚያብሔር ውይይቱን ሲከፍቱ ከተናገሩት ፦
" ስለደርሰብን ስብራት ኣብዝተን በማውራት የምንቀይረው ብዙ ኣይኖርም።
በትንሹ ከተግባባን፣ በብዙ ከሰራን በመከራ ላይ ላለው ህዝባችን ልንደርስለት እንችላለን።
ሁኔታው ልትገነዘቡ የመጣቹህ እንግዶች፣ ትላንት ዕዱልን ኣጥታቹህ ሞራላዊና ህጋዊ ግዴታቹ ሳትወጡ ለቀራቹህ ሁሉ፣ ዛሬም ህዝባችን ስቃይ ኣለበቃም እና፣ ድምፃቹህ፣ እውቀታቹህ፣ ጉልበታቹህ ያስፈልገዋል እና
✓ መጠልያ ውስጥ ያሉት ወደ ቀያቸው፣ የተሰድዱትም ወደ ኣገራቸው
✓ ተማሪዎች ወደ ናፈቃቸው ትምህርታቸው፣ ሰራቶኞችም ወደ ስራቸው፣
✓ ህመምተኞች የሚፈልጉት መድሃኔት እንዲያገኙ፣ የተማላ የምግብ ኣቅርቦት እንዲኖር፤
✓ ነፃ የዜጎችና የሸቀጦች እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የባንክ ኣገልግሎት እንዲጀመር በፍፁም ቅንነት ድምፃቹ እንድታሰሙ፣ የምትችሉትን ሁሉ እንድትሰሩ በታላቅ ትህትና እጠይቃቸዋለሁኝ፣ ትችላላቹም። "
(ሙሉ ንግግራቸው ከላይ ተያይዟል)
Photo : Tikvah Family (Mekelle)
@tikvahethiopia

#ትኩረት
በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በዚህ ሰዓት የፀጥታ ችግር መኖሩን በወረዳው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።
ያለው ሁኔታ #እጅግ_በጣም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለው የፀጥታ ስጋት " ለነፍሳችን ሰግተናል " ያሉ ነዋሪዎች የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እና ሁኔታው እንዲረጋጋ ጠይቀዋል።
ዛሬ በወረዳው ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፤ "ሰንበቴ በአሁኑ ሰአት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች ፤ ዱኣ ወይም ፀሎት ትፈልጋለች!! የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት ትሻለች። " ሲል አንድ አጭር ፅሁፍ አሰራጭቷል።
ወረዳው ይህንን ከማለት ውጭ ስለጉዳዩ ምንም የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።
በአጣዬ በኩልም ስጋት መኖሩን ቤተሰቦቻችን እየገለፁ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው ካሉት የቤተሰብ አባላቱ ሁኔታውን ለመከታተል ጥረት ያደርጋል።
ይህ የሀገራችን ቀጠና ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግር ሲከሰትበት እና የሰዎች ህይወት ሲቀጠፍበት ፣ ንብረትም ሲወድምበት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

#Update የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳ " #በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው " ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን መርምሮ ሹመታቸውን እንደሚያጸድቅ…
ፎቶ ፦ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከስልጣናቸው በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ አግኝተው ማናጋገራቸና ምስጋና ማቅረባቸው ተሰምቷል።
ከሰሞኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና አቶ ሰላሞን አረዳ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ በምትካቸው አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
Photo Credit : PMOEthiopia

#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና " ላልተገደበ ጊዜ " እንደሚሰጥ አሳውቋል።
የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሚያገኙት ፈተናውን ወስደው ብቁ መሆናቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው ተብሏል።
ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው መውሰድ የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሀመድ ለኢፕድ ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች በየስድስት ወሩ ፈተናውን የሚወስዱበት ዕድል እንዳለ ኃላፊው ጠቁመዋል።
የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ለአንድ ጊዜ ብቻ የፈተና ወጪያቸው እንደሚሸፈንላቸው ገልጸዋል።
በመንግሥትና በግል ተቋማት ላይ የሚሰጡ ከ300 በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዳሉ ያነሱት ኃላፊው፤ በየትምህርት መስኩ እየተደረገ በአስር ዙር ፈተናው ለመስጠት ታቅዷል።
#ኢፕድ
More : @tikvahuniversity

#አስቸኳይ በአሁን ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨማሪ አሃዶችን የመፍጠር ቴክኖሎጂዎች (Blockchain technologies) ላይ የተመሰረቱ የክሪፕቶ ምርቶችና አገልግሎቶች ሁኔታ በመስፋፋት እና ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የክሪፕቶግራፊ ውጤት/ምርትንና አገልግሎትን በተመለከተ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 808/06 አንቀጽ…
#ETHIOPIA
የምናባዊ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ክሪፕቶከረንሲ) የሚመራበትን መመሪያ እና የቁጥጥር ስርዓት በመቅረፅ ላይ እንደሚገኝ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል።
አስተዳደሩ የክሪፕቶከረንሲ ግብይት አሁን ላይ ህጋዊ መሰረት የሌለው መሆኑን አስረግጦ ተገልጿል።
የክሪፕቶከረንሲ ተጠቃሚዎች በኢንሳ በይነ መረብ ኦንላይን እንዲመዘገቡ መልዕክት ተላልፏል።
የመመዝገቢያው አድራሻ https://crypto.insa.gov.et/register መሆኑ ተመላክቷታ።
አሁን ላይ የሚያንቀሳቅሱ አካላት ለህጋዊነታቸው ከወዲሁ ቢመዘገቡ ይበጃል ያለው አስተዳደሩ ሳይመዘገቡ የሚንቀሳቀሱት ላይ ክትትልና እርምጃ በቀጣይ የሚደረግባቸው እንደሚሆን አስጠንቅቋል።
Credit : FM ADDIS 97.1

ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ነው ያለውና ቤተክርስቲያንን ያሳዘነው ፤ ምዕመኑንም ያስደናገጠው የ " ጳጳሳት " ሹሙት ምንድነበር ? ትላንት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት ተፈፅሞ ጳጳሳትን የመሾም ተግባር መከናወኑን መግለጿ ይታወሳል። ይኸው ሲመተ ጳጳሳት ፤ #ከቅዱስ_ሲኖዶስ እውቅና ውጭ #በሕገወጥ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ነው ቤተክርስቲያን ያሳወቀችው። …
#Update
ዛሬ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ በሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት አስቸኳይ ጉባኤ በማካሄድ " ሃይማኖታዊ ክህደት ፣ ቀኖናዊ ጥሰት እናአስተዳደራዊ ግድፈት " ታይቶበታል ያለውን የወሊሶውን " ሹመት " ማወገዙ ተገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ተገቢውን ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ምዕመናን በጸሎት እንዲቆዩም አሳስቧል።
ጉባኤው፤ በቤተክርስቲያን ላይ የተፈፀመው ሁሉን አቀፍ ክህደት ነው ያለ ሲሆን ክህደቱን የፈጸሙት አካላት ሥልጣን የሰጣቸውን መዋቅር(ተቋም) በመካድ የፈጸሙት ድርጊት እጅጉን አሳዛኝ ነው ብሏል።
የተፈጸመው ጉዳይ ህገ ወጥና ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ወንጀል እንደሆነ ገልጾ በምንም መመዘኛ ይህን ከፈጸሙ አካላት ጋር መደራደር በተዘዋዋሪ የቤተክርርቲያንን ሕግና ሥራዓትን ማፍረስ ነው ሲል አስገንዝቧል።
ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ አካል ሊሆኑ የሚችሉ የውሳኔ ሀሳቦችን ከቀኖና ቤተክርስቲያን እና ከሕግ አንጻር በመነሳት ጠቁሟል።
ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/EOTCPR-01-23
በሌላ በኩል፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና የብፁዕ አቡኑ ኤዎስጣቴዎስን እና የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት ማሸጉ ተሰምቷል።
እርምጃው ትላንት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድ እና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ " 26 ጳጳሳትን ሾመናል " ማለታቸውን ተከትሎ የተወሰደ ነው ተብሏል።
በተጨማሪ መረጃ፤ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሕገ ወጥ መንገድ ጵጵስና ተሹመዋል ያላቸውን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ኃይል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያንን አስተዳዳሪ ማገዱ ታውቋል።
ፎቶ፦ TMC

Photo
#Update
የህ/ተ/ም/ቤት የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ነገ ይመራል።
ነገ የሚኒስትሮችን ሹመት ማፅደቅ ጨምሮ ሌሎችም አጀንዳዎች የተያዙበት የምክር ቤቱ የ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል።
በዚሁ ስብሰባ ከታይዙት አጀንዳዎች መካከል ፤ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት እና ሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ማጽደቅ ይገኙበታል።
ተጨማሪ አጀንዳዎች ምንድናቸው ? ከላይ ተያይዟል።