TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ የተናገሩት ፦ - ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ የሚያስጀምሩት በዋና መ/ቤት የሚገኙ ሰራተኞች በጊዜያዊነት በከተማዋ በማሰማራት ነው። በአሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት የሚሰሩ ሰራተኞችን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው። ለጊዜው ከዚህ ሰዎች እየሄዱ ይሰራሉ፤ ይመለሳሉ። እዚያም ጥቂት ሰዎች አግኝተናል።…
#Mekelle

መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ።

ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች።

ትላንት የበረራ ቴኬት ለማግኘት ብሞክርም አልተሳካልኝም፤ በቀጣይ ቀናትም ያሉት ከወዲሁ ተይዘዋል" ያለችው ሄርሞን አየር መንገዱ በየዕለቱ የሚያደርገድን በረራ እንዲያሳድ ጠይቃለች።

" የምወዳትን እናቴን ድምፅ ከሰማሁ ወራት ተቆጥረዋል፣ አባቴም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም፤ ቤተሰቦቼም ምን ገጥሟቸው እንደሆነ የማውቀው ነገር የለኝም፤ ወደ መቐለ ሄጄ ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ቸኩያለሁ፤ በረራው ቁጥሩ ጨምሮ ብሄድ ደስ ይለኛል ይሄ የኔ ብቻ ሳይሆን እጅግ የብዙ የትግራይ ተወላጆች ጥያቄ ነው " ስትል ገልፃለች።

ሌላው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ካህሳይ፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በረራ እንደሚጀምር መስማቱ በዛው ያሉትን ቤተሰቦቹን ለማያት ትልቅ ተስፋ እንዳሳደረበት ገልጿል።

ካህሳይ በመቐለ ያሉ ቤተሰቦቹን ሳያይና ድምፃቸውን ሳይሰማ ከዓመት በላይ እንደሆነው ገልጾ ወደመቐለ ለመጓዝ ትኬት ለመቁረጥ ቢሞክርም መሙላቱን አመልክቷል አየር መንገዱም ፤ የበረራ ቁጥር እንዲያሳድግ  ጠይቋል።

በተጨማሪ " በዚህ ወቅት በአውሮፕላን የሚኬደው አማራጭ መንገድ ባለመኖሩም ጭምር በመሆኑ የትኬት ዋጋ አስተያየት ይደረግበት " ብሏል።

በተመሳሳይ ሌሎችም በርካቶች የበረራ ቁጥር እንዲጨምርና የትኬት #ዋጋ ላይ አስተያየት እንዲደረግ እየጠየቁ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ። ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች። ትላንት…
#AddisAbaba #Mekelle

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቐለ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንደተስተካከለ በየዕለቱ የሚካሄደውን በረራ እንደሚያሳድግ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት ቃል አየር መንገዱ የአውሮፕላን ችግር እንደሌለበትና በቀን አራትም፣ አምስትም በረራ ማድረግ እንደሚችል ገልፀዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን የተቸገርነው መቀለ የቴሌኮም አገልግሎት ስለሌለ የስልክ ግንኙነት እንኳን ማድረግ አልቻልንም። ከእዛ ለሚመለሱት እንኳን የ boarding pass እና የ baggage process እየተደረገ ያለው አዲስ አበባ ነው። የቴሌኮም ጥገናው እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ስለዚህ ይህ እንደተስተካከለ እኛም በራራውን እንጨምራለን። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ይህ ምናልባት በመጪው #ሶስት እና #አራት ቀናት ሊስተካከል ይችላል። " ሲሉም አክለዋል።

በሌላ በኩል ከየአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ጋር በተያያዘ 3 ሺህ የነበረው አሁን እስከ 9 ሺህ እየተሸጠ እንደሆነ ይነገራል ይህ ለምን ሆነ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

" ዘጠኝ ሺህ የተሸጠው business class ነው " ያሉት አቶ መስፍን " የeconomy class ትኬት ቀድመው የገዙ ሶስት ሺህ ብር ገደማ ነበር፣ በአለም አቀፍ አሰራር መሰረት ትንሽ ዘግይቶ የሚገዛ ደግሞ ወደድ ይላል፣ አራት ሺህ ገደማ ገብቷል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለበረራ የሚጠቀምበት አውሮፕላን 138 ሰው የሚጭን ቦይንግ 737 መሆኑን ጠቁመዋል።

" ወደፊት ፍላጎቶችን እያየን ከዛም በላይ የመጫን አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖችን መጠቀም እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤልያስመሰረት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ ዛሬ ቀን 6:00 ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ መደበኛ በረራውን ማድረግ መጀመሩን አሳውቋል።

የአየር መንገዱ የኮሙኒኬሽን ባለሙያው አቶ አሸናፊ ዘርዓይ ፤ " ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአየር ትራንስፖርት ዛሬ ቀን 6 ሰዓት ላይ በይፋ ጀምሯል " ሲሉ  ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

Credit : ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ መንገደኞችን ይዞ የበረረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን #በሰላም አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አርፏል። ዛሬ መቐለ ያረፈው የመንገደኞች አውሮፕላን ከ19 ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Photo : Addis Ababa Bole Airport (ENA)

@tikvahethiopia
#Update

መቐለ ከተማ የስልክ አገልግሎት ማግኘቷን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የስልክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት መቐለ ላይ የተሳካ ጥሪ ማድረግ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና ተከናውኖ በ27 ከተሞች የስልክና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ማስጀመር ተችሏል ብለዋል።

የቴሌኮም አገልግሎቱ ዳግም መጀመር በመቻሉ 61 የባንክ ቅርንጫፎችም ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

#Peace #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ታህሳስ19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በቁልቢ እና በሐዋሳ እጅግ ከፍተኛ ምዕመን በተገኘበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል። በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የንግስ በዓሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው። ቅዱስነታቸው…
" ገንዘብ እና ሌሎች ቁሳቁስ ሰርቀው እጅ ከፍንጅ የተያዙ 6 ግለሰቦች ከ1 ዓመት ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት ከ7 ወር የሚደርስ እስራት ተረዶባቸዋል " - የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል

ዛሬ በቁልቢና ሀዋሳ የተከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ንግስ በዓል ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም የተጠናቀቀ ስለመሆኑ ሪፖርት ተደርጓል።

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፤ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሰላም መጠናቀቁን ገልጾ ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ፦
- የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣
- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣
- የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ፣
- የሀረሪ ክልል ፖሊስ
- የድሬዳዋ ፖሊስ ከሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ከኅብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ የፀጥታ እና ደህንነት ተግባር ማከናወናቸውን ገልጿል። 

ከበዓሉ ታዳሚዎች የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ፣ ገንዘብ እና ሌሎች ቁሳቁስ ሰርቀው እጅ ከፍንጅ የተያዙ 6 ግለሰቦች ከፖሊስ፣ ከዐቃቤ ሕግና ከፍ/ቤት ተውጣጥቶ በተቋቋመ ጊዜያዊ ፈጣን ችሎት ፊት ቀርበው ከ1 ዓመት ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት ከ7 ወር የሚደርስ እስራት እንደተፈረደባቸው ግብረ ኃይሉ አሳውቋል።

በተመሳሳይ ዓመታዊው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እና በታላቅ ድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ መምሪያ አሳውቋል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia