TIKVAH-ETHIOPIA
🏆 #አርጀንቲና አርጀርቲና የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አነሳች። የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የ2018 ዓለም ዋንጫ አሸናፊዎቹን ፈረንሳይን በመለያ ምት በመርታት ሻምፒዮን ሆነዋል። ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል። More : https://t.iss.one/tikvahethsport @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አንስተዋል።
አርጀንቲና ከ36 ዓመታት በኃላ ነው ዋንጫውን ማሳካት የቻለችው።
የ7 ጊዜ ባላንዶር አሸናፊው ሜሲም በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ማሳካት ችሏል።
(ከድራማዊው የዓለም ዋንጫው የፍፃሜ ጨዋታ ቀደም ብሎ በትክክል አሸናፊውን ለገመቱ 20 የቤተሰባችን አባላት ለእንያንዳንዳቸው የ250 ብር የሞባይል ካርድ እንደምናበረክት አሳውቀን ነበር ፤ በአስተያየት መስጫው አርጀንቲና ብለው ለመለሱ አባላት በቅደም ተከተል ስጦታቸውን እንልካለን።)
@tikvahethiopia

" ሸገር ከተማ ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው "
በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ስድስት (6) ከተሞች የተዋቀረው ሸገር ከተማን የማደራጀት ሥራ መጀመሩን የከተማው ኃላፊዎች እንደገለፁ ሪፖረተር ጋዜጣ አስነብቧል።
የከተማው ምክትል ከንቲባ እንደሆኑ የተነገረላቸው አቶ ጉግሳ ደጀኔ ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ 6 ከተሞች በአንድ ከተማ አስተዳደርና በአንድ ከንቲባ እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ከተሞቹ ፦
• ሰበታ፣
• ቡራዩ፣
• ለገጣፎ ለገዳዲ፣
• ሱሉልታ፣
• ገላንና መናገሻ በሥሩ የሚገኙ ከተሞች እንደሆኑ ተገልጿል።
አቶ ጉግሳ ደጀኔ ለጋዜጣው በሰጡት ቃል ፦
- አዲሱ የሸገር ከተማ በ12 ክፍላተ ከተሞች፣ በ36 ወረዳዎች፣ 40 የገጠር ቀበሌዎች የተደራጀ (የተዋቀረ) ነው።
- የከተሞች ዕድገት ወደኋላ የቀረ በመሆኑና በከተሞች መስፋፋት ሳቢያ አርሶ አደሮች ከመኖሪያ ቀዬአቸው በመፈናቀላቸው ነው ከተማው የተመሰረተው።
- ስድስቱ ከተሞች በጋራ የሚያከናውኑት ሥራ ተፎካካሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ሲሆን ዋና ጽሕፈት ቤታቸው #አዲስ_አበባ፤ ሳሪስ አካባቢ ነው።
- ዋና ጽሕፈት ቤቱን ለመምረጥ (አ/አ) የራሱ የሆነ መነሻ ተቀምጦለታል ፤ ይህም ለሁሉም ከተሞች አማካይ መሆን የሚያስችል ቦታ ታሳቢ በማድረግ ነው።
- ሸገር ከተማ ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው። እንደማንኛውም መንግሥታዊ አስተዳደር ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና የዳኝነቱ ሥርዓትን የሚመሩ አካላት ይኖሩታል።
- ለአዲሱ የሸገር ከተማ በቅርቡ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-12-19
Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

#GOFA በጎፋ ዞን ለተከታታይ 4 የምርት ዘመን በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተው የምግብ እጥረት በዛላ ፣ ኡባ ደብረ-ፀሃይ እና ደምባ ጎፋ ወረዳዎች እጅግ በርካታ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል። በተለይም በዛላ ወረዳ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በምርት ዘመን አስፈላጊው ምርት ባለማግኘቱ ዜጎች ለከፍተኛ ራሃብ ተጋልጠዋል። በዛላ ወረዳ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ፤ አንድ የቤተሰባችን…
ፎቶ ፦ በጎፋ ዞን የሀይማኖት ፎረም አስተባባሪነት በዛላ ወረዳ ከሁሉም ቤተእምነት በመውጣጣት በአከባቢው ለገጠመው ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ ፈጣሪ ምህረቱን እንዲያወርድ የአደባባይ ፀሎት ተካሄደ።
ዛሬ ከሁሉም ቤተ እምነት የተውጣጡ ነዋሪዎች ከንጋቱ በ11:00 ላይ አደባባይ በመውጣት እንደየ እምነታቸው ፈጣሪ ምህረትን እንዲያወርድ ተማፅነዋል።
በወረዳው ለተከታታይ ዓመታት በሰውና እንስሳት ላይ ለደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ነው መላው ማህበረሰብ፣ ሀገር ሽማግሌዎች ፣ ሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች ወጥተው የአደባባይ ፀሎት ያካሄዱት።
በዋናነት የአደባባይ ጽሎት ያስፈለገበት ምክንያት በአከባቢው 4 ተከታታይ ዓመት ዝናብ ባለመዝነቡ ወንዞች እየደረቁ በሰውና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከፈጣሪ ቁጣ በመድረሱ ነው።
በጸሎታቸው " ፈጣሪ ለኃጥያታችን ሁሉ ይቅርታ እንዲያደርግ ፤ ቁጣዉን እንዲመልስልን፤ ምህርቱን እንዲሰጠን " በንስሐ በፈጣሪ ፊት በመንበርከክ ፀሎትና ምልጃ አቅርበዋል።
መረጃው የዛላ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

" እኔ የትራፊክ አደጋ አልደረሰብኝም " - አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ
አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የትራፊክ አደጋ #እንዳልደረሰበት ተናገረ።
አትሌት ኃይሌ " የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት " ሚዲያዎች እየዘገቡ ሲሆን አትሌቱ ለአል ዓይን አማርኛው ክፍል በሰጠው ቃል " መረጃው ሀሰት ነው እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ አልደረሰም " ብሏል።
ኃይሌ ፤ " ያለንበት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው፣ ሌላም ነገር ቢሆን እንዲህ ነው የውሸት መረጃ የሚሰራጨው " ብሏል።
ዛሬ ጠዋት " ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 " በተሰኘው ሬድዮ ጣቢያ ከሚሰራጨው " አውቶሞቲቭ " የሬድዮ ፕሮግራም ጋር በስልክ ተደውሎልኝ ስለፍጥነት መገደቢያ ወይም ስፒድ ብሬከር ችግር መሆኑን አስተያየት ሰጥቼ ነበር ያለው ኃይሌ ፤ " ይህ ማለት ግን ዛሬ በእኔ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶብኛል ማለት አይደለም " ሲል ተናግሯል።
አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በተሰራጨው ሀሰተኛ ዘገባ ምክንያት ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ አሳስቧቸው እጅግ ብዙ የስልክ ጥሪዎች እያደረሱኝ ነው ሲል ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጠው ቃል ተናግሯል።
#አልዓይንኒውስ

#ጥቆማ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩንቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች ፦
- በመምህርነት፣
- በተመራማሪነት እና በረዳት መምህርነት መቅጠር እንደሚፈልግ አሳውቋል።
መወዳደር የምትፈልጉ መስፈርቱን የምታሟሉ በተጠቀሱት አድራሻዎች ማመልከት ትችላላችሁ።