TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአቢ ዓዲ – ዐድዋ የተዘረጋው የባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና 90 % መጠናቀቁን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ጥገና በአብዛኛው በመጠናቀቁ የዐድዋ እና አክሱም ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ በነገው ዕለት የሙከራ ሥራ እንደሚሠራ ገልጿል።

በተጨማሪም ከዐድዋ – ሽረ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ የተዘረጋው የ66 ኪሎ ቮልት የሥርጭት መስመር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠግኖ የተጠናቀቀ ቢሆንም ከሽረ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ለመስጠት የሙከራ ሥራ ሲከናወን በብሬከሩ ላይ ችግር ማጋጠሙ ተገልጿል።

የብሬከሩን ብልሽት በመጠገን ከመስመሩ ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል

@tikvahethiopia
#GlobalBankEthiopia

" ደቡብ ግሎባል ባንክ " ስያሜውን ወደ " ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ " መቀየሩን ሪፖርተር አስነብቧል።

ባንኩ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤውን ስያሜውን ወደ " ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ " መቀየሩ ተገልጿል።

የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኩ ከዚህ በኋላ በአዲስ ስያሜና አርማ እንደሚቀጥል ያቀረበውን ሀሳብ የባንኩ ጠቅላላ ጉባኤ አጽድቆታል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስያሜ የሚቀጥለው የቀድሞ ደቡብ ግሎባል ባንክ በ2014 ሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 370 ሚሊዮን ብር ማትረፉም ተገልጿል።

ይኸም ካለፈው ተመሳሳይ የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነፃጸር 41 በመቶ ወይም የ108.4 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።

ባንኩ ተቀማጭ ሒሳቡን ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱንና ፣ በ2014 ሒሳብ ዓመትም 2.3 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#ይገምቱ

የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ?

#ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ።

የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል።

20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል ነው።

ግምቱን መላክ ሚቻለው ጨዋታው እስከሚጀምርበት ደቂቃ ድረስ ብቻ ሲሆን #Edit የተደረገ ምላሽ ተቀባይነት አይኖረም።

(ግምትዎን #ከታች_ባለው የአስተያየት ማስቀመጫ ላይ ያኑሩ ፤ ፈረንሳይ ወይስ አርጀንቲና ? ከሁለቱ ሀገራት አንዱን ብቻ ይምረጡ ፤ ውጤት / በቁጥር መገመት #አያስፈልግም )

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይገምቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ? #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ። የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል። 20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል…
#Update #WorldCup

በFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እያደረጉ የሚገኙት #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና መደበኛ 90 ደቂቃውን በ2 ለ 2 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

ምንም እንኳን አርጀንቲና በሜሲ እና ዲማሪያ ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ በበላይነት ብታጠናቅቅም ፈረንሳይ በሁለተኛው አጋማሽ ቡድኗን አጠናክራው በወጣቱ ምባፔ ሁለት ጎሎች አቻ መሆን ችላለች።

ጨዋታው አቻ መሆኑን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።

ይህን የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ ሚሊዮኖች እየተከታተሉት ይገኛሉ። ማን አሸናፊ ይሆን ?

More : https://t.iss.one/tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ድራማዊው የዓለም ሀገራት ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ወደ መለያ ምት አመራ።

የፈረንሳይ እና አርጀንቲና ጨዋታ ወደ ተጨማሪ ደቂቃ ቢያመራም ጨዋታው #በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በተጨማሪው ደቂቃ አርጀንቲና በ #ሜሲ ጎል መሪነቱን ብትረከብም ፈረንሳይ ያገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት ምባፔ ወደ ጎል በመቀየር ጨዋታ በ3 ለ 3 አቻ ውጤት ወደ መለያ ምት አምርቷል።

ይህን ድራማዊ የFIFA ዓለም ሀገራት የፍፃሜ ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይሆን ?

More : https://t.iss.one/tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🏆 #አርጀንቲና አርጀርቲና የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አነሳች። የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የ2018 ዓለም ዋንጫ አሸናፊዎቹን ፈረንሳይን በመለያ ምት በመርታት ሻምፒዮን ሆነዋል። ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል። More : https://t.iss.one/tikvahethsport @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አንስተዋል።

አርጀንቲና ከ36 ዓመታት በኃላ ነው ዋንጫውን ማሳካት የቻለችው።

የ7 ጊዜ ባላንዶር አሸናፊው ሜሲም በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ማሳካት ችሏል።

(ከድራማዊው የዓለም ዋንጫው የፍፃሜ ጨዋታ ቀደም ብሎ በትክክል አሸናፊውን ለገመቱ 20 የቤተሰባችን አባላት ለእንያንዳንዳቸው የ250 ብር የሞባይል ካርድ እንደምናበረክት አሳውቀን ነበር ፤ በአስተያየት መስጫው አርጀንቲና ብለው ለመለሱ አባላት በቅደም ተከተል ስጦታቸውን እንልካለን።)

@tikvahethiopia