TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.6K photos
1.6K videos
216 files
4.35K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰማ ይፍጠን። ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ በመቀበል ብቻ ብር ይታፈሳል!

#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
115😡24👏22🙏10🤔8😱8
" የኢትዮጵያን ሰላም የሚያናጋው 60% የኢትዮጵያ ሃብታም ነው " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

➡️ " እየቀለባችሁ ፤ ፋይናንስ እያደረጋችሁ እኔን መልሳችሁ ' ሰላም ' ብትሉኝ አይሆንም። ሰላም ከፈለጋችሁ ፋይናንስ አታድርጉ ! "

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ባለሃብቶች የሰላም ችግር በስራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ ሰላም በሰጡት ማብራሪያ ባለሃብቶች ጫካ ያሉትን ታጠቂዎች በገንዘብ መደገፍ ወይም ማበረታታት እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

ባለሃብቶች እውነተኛ ሰላም ፈላጊ ከሆኑ በጫካ ያሉ ኃይሎችን መደገፍ ፣ መቀለብ አቁመው ወደ ሰላም እንዲመጡ መምከር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

" ሰላም የሚፈልግ ካለ በእኛ በኩል ምንም ችግር የለውም እንቀበላለን እናተ ጫካ ብር አትላኩ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ " መንግስት በሰላም የሚመጡ አካላትን ተቀብሎ ለማወያየት ዝግጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ህግ ማስከበር ስራችን ስለሆነም የሚቀጣ ካለ እንቀጣለን " ሲሉ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሃብታሞች የሀገሪቱን ሰላም በማደፍርስ ላይ 60 በመቶ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

" እየቀለባችሁ ፤ ፋይናንስ እያደረጋችሁ እኔን መልሳችሁ ' ሰላም ' ብትሉኝ አይሆንም። ሰላም ከፈለጋችሁ ፋይናንስ አታድርጉ " ሲሉ አሳስበዋል።

" የሰላም ችግር ትልቅ ኪሳራ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ተቃዋሚዎችም ሆኑ ባለሃብቶች ሰላምን የማረጋገጥ ግዴታ የመንግስት ብቻ አድርገው በመውሰድ ከሃላፊነት መሸሽ ተገቢ አይደለም " ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል መንግስት ኮንትሮባንድን እና ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር ባዘጋጃቸው የፍተሻ ኬላዎች የኮቴ እያሉ ገንዘብ የሚጠይቁ አካላት እንዳሉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ፥ እነዚህ የፍተሻ ኬላዎች የማይኖሩ ከሆነ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች እየገባ የሰዎችን ህይወት እንደሚቀጥፍ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ገንዘብ ሳይጠየቅ ፍተሻ የሚደረግበትን መንገድ ለማመቻቸት መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል፡፡

#PMOffice #Ethiopia

@tikvahethiopia
😡2.09K1.67K😭118🤔110👏63🕊55😱40🙏36💔31😢18🥰17
TIKVAH-ETHIOPIA
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ምንድነው ያሉት ? 🔴 ፕሬዝዳንቱ አብዛኛው ንግግራቸው ስለ ሀገራቸው ኤርትራ የውስጥ ጉዳይ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት ጉዳይ ነበር ! ኤርትራ ትላንት ቅዳሜ 34ኛ ዓመት የነፃነት በዓሏን አክብራለች። ለ34 ዓመታት አገሪቷን በብቸኝነት እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለ34ኛ ጊዜ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዜዳንቱ 20 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው…
#Ethiopia🇪🇹

" አሁን ኩርፊያ መጥቷል ፤ መወራጨትም አለ " - የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

" ለመተባበር ብዙዎችን ጋብዘናል ኤርትራን ሳይቀር ጋብዘናል ፤ አብረን እንስራ ብለናል ፤ ባህር ለሁላችን ይሁን ብለናል ፤ የ20 ዓመት ፍጥጫ ይቁም ብሎ መንግሥታችን የነበረውን ቁርሾ በመፍታት ወደ ልማት ፣ ወደ ኢንተግሬሽን፣ ወደ ጋራ ተጠቃሚነት ፣ ወደ አብሮ መበልፀግ እንድንገባ ኤርትራውያንም የሚጠቀሙት ጥቅም ካለ ከኢትዮጵያ እንዲጠቀሙ ኢትዮጵያም ከኤርትራ እንድትጠቀም በጣም ሰፊ ስራ ተሰርቷል ፤ ተልፍቷል።

በጣም ባልተለመደ መንገድ የኤርትራንና የኢትዮጵያን ግንኙነት ለመፍታት መንግሥታችን ረጅም ርቀት ሄዷል፤ ግን አልተሳካም።

አብረን እንጠቀም ነው እንጂ የባህር በር ይዤ እናተን እንደፈለኩ ላድርጋችሁ የሚል አስተሳሰብ ስላለ አይ እንደዛ ሳይሆን በጋራ ተጠቃሚነት ፣ በእኩልነት ነው ፤ የሆነ ቁልፍ መሳሪያ ይዘህ በቁልፍ መሳሪያ ይሄን ሁሉ ማህበረሰብ ለማሽከርከር መሞከር ልክ አይደለም የሚል ነገር ሲመጣ አሁን ኩርፊያ መጥቷል መወራጨትም አለ። "

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.88K😡482🕊131🤔126👏80🙏46😢39💔34😭23😱20🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Kenya ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ ድንበር የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ…
#Ethiopia #Kenya

ሊተገበር መመርያ እየተዘጋጀለት ያለው የኢትዮ ኬንያ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ ጥያቄ ተነሳ። 

ሊተገበር መመርያ እየተዘጋጀለት ያለው የኢትዮ ኬንያ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ " ጉድለቶች አሉት " ሲሉ ነጋዴዎችና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሞያሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የስምምነቱ ይዘቶች ማሻሸያ እንዲደረግባቸዉ የንግዱ ማኅበረሰብ እየጠየቀ እንደሆነ አስረድተዋል።

የኢትዮ - ኬንያ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት በኬንያዋ የዉቅያኖስ ዳርቻ ከተማ ሞምባሳ፣ በኢትዮጵያዉ ንግድ ና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ፒኤችዲ) እና በኬንያዉ አቻቸዉ ሊ ክኛንጁይ መካከል ነበር ባለፈዉ ሚያዚያ ወር ነበር ስምምነቱ የተፈረመዉ።

ይህ ‘ታሪካዊ’ የተባለዉና የአፍሪካ የነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት አካል መሆኑ የተነገረዉ ስምምነት የሁለቱ ሀገራትን የንግድ ግንኙነትን በይበልጥ ያሳልጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ነው።

ሆኖም የስምምነቱ ፊርማ ከተፈፀመ ወደ ሁለት ወር ቢጠጋም እስካሁን ግን ተግባራዊ አለመሆኑን የሞያሌ አካባቢ ነጋዴዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

አቶ አዲሱ ንግሴ የሞያሌ ከተማ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ " በሚያዝያ ወር ኬንያ ና ኢትዮጵያ የተፈራረሙት ስምምነት የአካባቢዉ የረዥም ዓመት ጥያቄ ነዉ " ያሉ ሲሆን ሆኖም እስካሁን አለመተግበሩን ጠቁመዋል።

ፕረዚዳንቱ የስምምነቱ ይዘቶች ማሻሸያ የሚያስፈልጋቸው ናቸዉ በሚል ያነሳሉ። በዚህም ስምምነቱ ያጎደላቸዉ የሚሏቸውን አራት ነገሮች ዘርዝረዋል።

ፕረዚዳንቱ ያነሷቸው ማሻሻያ ነጥቦች ምንድን ናቸው ?

" አንደኛው፣ በስምምነቱ ነፃ የንግድ ቀጠና ስፋቱ፣ በኬንያ በኩል 100 ኪሎ ሜትር  ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን 50 ኪሎሜትር ብቻ መሆኑ፣ በእኛ በኩል ቅሬታን ፈጥሯል።

ምክንያቱም አርብቶአደር የሆነዉ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ተጠቃሚ አይሆንም፣ በ50 ኪ.ሜ. ራድየስ ዉስጥ ያሉት ከተሞችም ጥቂት ስለሆኑ፣ ቢያንስ ከድምበር እስከ 300 ኪሎሜትር አካታች እንዲሆን ስንጠይቅ ቆይተናል።

ሁለተኛዉ ደግሞ በዚህ ንግድ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር ማነስ ነዉ። ሶስተኛዉ ለ አንድ ነጋዴ የተፈቀደዉ የሸቀጦች ጅምላ ድምር ጣርያም በቂ አለመሆንና አራተኛ ላይ የሸቀቶቹ አይነቶችም እስካሁን በጥያቄ ዉስጥ ያሉ ናቸው " ሲሉ አብራርተዋል።

ለንግድ ስምምነቱ ትግበራ በኬንያ በኩል የሀገሩ መንግስት ና ነጋዴዎች በቂ እንቅስቃሴ ላይ ናቸዉ ያሉት አቶ አዲሱ፥ በኢትዮጵያ በኩል ያለዉን ሁኔታ ግን በመተቸት " ኃሳቡ ለሀገር ጥቅምን የሚያስገኝ ቢሆንም፣ ነጋዴዎች እያነሱት ያሉት ነጥቦች ከትግበራዉ በፊት መስተካከል አለበት " ብለዋል።

የቦረና ዞን አስተዳደር ንግድ ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?

የቦረና ዞን አስተዳአደር ንግድ ፅህፈት ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

አቶ ቀራርሳ ዴራ የፅህፈት ቤቱ ገበያ ጥናት ባለሞያ ሲሆኑ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝደንቱ ያነሱትን ቅሬታ በትክክልም እንዳለ ገልጸዋል።

" የዞኑ ነዋሪ ከዚህ ስምምነት ተጠቃሚ ለመሆን ለዓመታት ሲጠይቀው የነበረ ጥያቄ ነዉ ካሉ በኋላ፣ ጥያቄዉም ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ ነዉ " ብለዋል።

የሞያሌ ከተማ ንግድ ፅህፈት ቤት፣ የተሳታፊ ነጋዴዎች አኃዝን በተመለከተ፣ በነጋዴዎች በኩል የሚነሳ ቅሬታን መስማቱን ገልፆ ነገር ግን የስምምነቱ ትግበራ መመርያ እስካሁን ስላልደረሰ በሁኔታዉ ላይ ምላሽ መስጠት እንደማይችል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቦረና ዞን አስተዳአደር ንግድ ፅህፈት ገበያ ጥናት ባለሞያ አቶ ቀራርሳ አክለውም፥ መመርያዎች እየተዘጋጁ መሆናቸዉን ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዳማ
#TikvahEthiopiaFamilyAdama

@tikvahethiopia
1.2K🙏43🕊31🤔25🥰20😡11😢10😱6😭2
#Ethiopia #USA

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግስት የመጀመሪያ ግንኙነታቸዉን አካሂደዋል።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ነጩ ቤተመንግስት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

" ይኸው ግንኙነት በቀጣይ ጊዜአት ለሚደረጉ በርካታ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል " ያለው ኤባሲው " ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ናቸው በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ ናቸው " ብሏል።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት የተገኙትን ስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም ተገናኝተዋል።

Photo credit: The White House

@tikvahethiopia
956👏161😡78😭64🤔41🙏38🕊22😢17😱9🥰4
#ETHIOPIA #USA

ዛሬ ጥዋት ላይ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ ማሪን ኮርፕስ ጄኔራል እና አፍሪኮም አዛዥ ከሆኑት ጄነራል ማይክል ላንግሌይ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።

ውይይቱ የጋራ ፍላጎት በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንዳተኮረ አመልክተዋል።

አሜሪካም ጄነራሏ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ማድረጉን አሳውቃለች።

ውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ የአልሸባብ እና የአይኤስ የሽብር ስጋትን መከላከል ላይ ያተኮረ እንደነበረም ጠቁማለች።

በሌላ በኩል ፥ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (AFRICOM) ጀነራል ማይክል ላንግሌይ ኢትዮጵያን እንደጎበኙ አሜሪካ አሳውቃለች።

በዚህም ወቅት ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጋር መምከራቸውን ገልጻለች።

ምክክራቸው ፦
- ቀጠናዊ ሰላምና ደህንነት፣
- በቀጠናው ላይ ያሉ ችግሮችን በጋራ የመፍታት ጥረት፣
- በሱማሊያ ያለውን ሽብርተኝነት መዋጋት ላይ፣
- በአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ መረጋጋትን ስለ መደገፍ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ አሜሪካ አሳውቃለች።

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ምን አለ ?

ሀገር መከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ (አፍሪኮም)  ጀነራል ሚካሄል ላንግሌይ የተመራ ልዑክን ተቀብለው እንዳነጋገሩ ገልጿል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ  ጁላ " አሜሪካና ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ ግንኙነት አላቸው " ያሉ ሲሆን " ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በመከላከያ ዘርፉ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

በውይይቱ በቀጠናው ባለው ሁኔታ የጋራ መግባባት የተያዘበትና በተለይም በቀይ ባህር ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በሚታዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ  ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  መስማማታቸውን አመልክተዋል።

የአፍሪኮም አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ላንግለይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር መሆኗን እንደተናገሩ መከላከያ አሳውቋል።

በቀጣይ በወታደራዊና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን እንደተናገሩም አክሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

Photo ፦ PM Office & US Embassy

@tikvahethiopia
1.23K😡410🙏51🤔50🕊36😭30👏18💔17😢11
#Ethiopia

" ኢትዮጵያ በሚቀጥለው መስከረም ወር ላይ የመጀመሪያ ዙር የጋዝ ምርት ለገቢያ ታቀርባለች " ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስት ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ጉዳይ የተናገሩት ከሚዲያ እና ከኮሚኒኬሽን ባለሞያዎች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ነው።

" ላለፉት ዓመታት በዚህ ጉዳይ ምን ሲሰራ እንደነበር አታውቁም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ከነገርናችሁ ከውስጥም ከውጭም ጣጣው ስለሚበዛ ነው ዝም ብለን የሰራነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ምርት የት አከባቢ እንደሆነ በቀጥታ ባይናገሩም በንግግራቸው ወቅት " ላለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት እኔ የምጎበኘው ጋዙን ነው እናንተ የምታዩት ስንዴውን " ሲሉ ተናግረዋል።

" እስካሁን ያልነገርናችሁ በህዳሴ ላይ የከፈልነውን ዋጋ ከፍተኛ ስለሆነ ነው " ሲሉ ፕሮጀክቱ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ መንገዶች በሚዲያው ከሚደርስበት ጫና ለመላቀቅ በዝምታ መስራታቸውን አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
3.25K😡738🤔343👏289😭150🙏101🕊57😢36😱30💔30🥰23
#Ethiopia

ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት በቅርቡ ከናይጄሪያው ባለኃብት ዳንጎቴ ጋር እንደምትፈራረም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ ሐምሌ ወር አጋማሽ የስምምነት ፊርማው እንደሚደረግ የገለጹ ሲሆን " በቀጣይ 3 ዓመታት ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ይኖራታል " ሲሉ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

ይህ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ በጎዴ አከባቢ እንደሚገባ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የ3 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት መሆኑን መግለጻቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2.14K👏393😡162🤔115🙏77😭44🕊40😱31😢27💔17🥰9
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም #የአረንጓዴ_አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
#Ethiopia🌱

የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ።

በአጠቃላይ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል  ዕቅድ ተይዟል።

በዛሬው ዕለት በወንዝ ዳርቻ ልማት አንዱ ክፍል በሆነው በእንጦጦ ዙሪያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕረዚዳንት ካቲም ሼቲማን ጨምሮ የክልል አመራሮችና ሚኒስትሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ፥ የሚስማማውን ችግኝ በሚስማማው ቦታ እንዲተከል ጥሪ አቅርበዋል።

የአረንጓዴ አሻራ በቀጣይ አመት ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በስምንት ዙር የችግኝ ተከላ መርኃግብር (የአረንጓዴ አሻራ ሲጠናቀቀ) የተከለቻቸውና የምትተክላቸው ችግኞች አጠቃላይ ብዛት 50 ቢሊዮን እንደሚደርሱ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
652😡397👏21😭19🕊15🤔14😱13🙏13💔6🥰3😢2
#Ethiopia

የንብረት ታክስ በክልሎች በሚቀጥለው በጀት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ተባለ።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት ክልሎች የንብረት ታክስን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራሉ " አሉ።

ይህን ያሉት በህዝብ ተ/ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ላይ ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

" ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ እዳ እየከፈለ የሚገኘው መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ገቢ እያገኘ መምጣቱን መጥቷል " ያሉ ሲሆን " ገቢ የማያስገኝ አገልግሎት አክሳሪ ነው " ብለዋል።

በአዲስ አበባ የንብረት ታክስ ክፍያ ተግባራዊ መደረጉን በማስታወስ " በሚቀጥለው በጀት ዓመት የንብረት ታክስ በክልሎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጀመራል " ነው ያሉት።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
😡552332😭24💔19😱12👏9😢4🕊4