TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደመወዝ #የትርፍሰዓትክፍያ

“ ከ9 ወር በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ”- ከ200 በላይ የጤና ባለሙያዎች

“ የትርፍ ሰዓት በየወሩ እየተከፈለ አይደለም እሱ ትክክል ነው። የከተማ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል ገብቷል ” - የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ጋሞ ዞን ፤ በሰላምበር ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ከ9 ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ጊዜ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ፣ ደመወዝም የሚገባላቸው እየተቆራረጠ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎችን ወክለው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የጤና ባለሙያ ተከታዩን ብለዋል።

- “ ከ9 ወራት በላይ ለሚሆን ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም። ሳይከፈለን 10ኛ ወር እየሰራን ነው ያለነው። ”

- “ በሌላ በኩል ደግሞ ዋና ደመወዝ ሁሌም እየተቆራረጠ ነው የሚገባው። ግማሹ ብቻ ያስገቡና ግማሹ ደግሞ ሳይገባ ወሩ ያልቃል። ”

- “ የደመወዝ ሆነ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በተመለከተ ቅሬታ ያለን 113 ጤና ባለሙያዎች (የትርፍ ሰዓት ያልተከፈላቸው) ፣ 103 ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች (የትርፍ ሰዓት ክፍያ የማይመለከታቸው) ናቸው። ”

- “ ያልተከፈለው የክፍያ መጠን እንደ ጤና ባለሙያው ፤ አሁን ለምሳሌ የእኔ 5,000 ነው በወር የሚሆነው። 15 ሺሕ የሚከፈለው አለ። 30 ሺሕ የሚከፈለው አለ እንደ ስፔሻሊቲ ከሆነ። ”

በጉዳዩ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
* የሰላምበር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የCOA ተወካይ አቶ ደካሶ ዲቻ፣
* የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘነበ ወንተ
* የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩን አግኝቶ ምላሽ እንዲሰጡ ቢሞክርም ፈቃደኛ አልሆኑም።

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ግን ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል። የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ አቶ ሰይፉ ዋናካ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሠጥተዋል።

አቶ ሰይፉ ዋናካ ምን አሉ ?

° “ ቅሬታ ሲቀርብ ወርደን እናወያያለን። ከሁለት ወራት በፊት ወርደን አወያይተን፣ አግባብተን የትርፍ ሰዓት በየወሩ እየተከፈለ አይደለም እሱ ትክክል ነው። ግን ያው የተወዘፈም እየተከፈለ ነው ያለው። ”

° “ ችግሩ ካለ ወርደን እናስከፍላለን። የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከእኛ አቅም በላይ አይደለም። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩ ካቅማችሁ በላይ ካልሆነ ከ9 ወራት በላይ ለምን ዘገዬ ? ሲል ጠይቋል።

ምላሽ ፦

° “ የከተማ አስተዳደሩ ችግርም ፣ አገራዊ ችግሮችም አለ። ሁሉ ወጥ አይሆንም። የከተማ አስተዳደሩ ለመክፈል ቃል ገብቷል። ስለዚህ የ10 ወራቱም ቢሆን ይከፈላል። ”

ጤና ባለሙያዎቹ በበኩላቸው፣ ከወራት በፊት ፒቲሽን ሰብስበው የትርፍ ሰዓት ሥራ እንደማይሰሩ አቋማቸውን ሲገልጹ ኃላፊዎች ቢያወያዩአቸውም ክፍያው እንዳልተሰጣቸው አስረድተዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia