TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion ➡️ " ... በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነው " - የሶዶ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኞች ➡️" ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " - የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ የ2 ወራት ደሞዛችን ይከፈለን ያሉ የወላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች አደባባይ መውጣታቸዉን…
#ደመወዝ #ደቡብኢትዮጵያ

° " ...ድርጊቱ የደመወዝ ቅሸባ ነው ሊባል የሚችለው ፤ እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል ሰምተንም አናውቅ " - ሰራተኞች

° " ከእኛ #የሚወርደው የበጀት ሀብት እኮ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው " - የክልል ፋይናንስ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች " የደመወዝ ይከፈለን " ጥያቄ በብርቱ ከተነሳባቸው አካባቢዎች አንዱና ዋነኛው የ #ወላይታ_ዞን እንደሆነ ይታወቃል።

ሰራተኞቹ ችግር ሲብስባቸው እና ታግሰው ሲመራቸው ሰልፍ  ጭምር በመውጣት ጥያቄ አቅርበዋል።

ለ3 ወራት ያለ ደመወዝ የቆዩት የመንግስት ሰራተኞች አሁን ላይ #የ40_በመቶ እና #የ50_በመቶ ክፍያ ብቻ እየተፈጸመላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል #የፋይናንስ_ቢሮ ፤ " ደመወዝ ባለመክፈል የመንግሥት ሰራተኛውን እያስራቡ ይገኛሉ " ባላቸው የዞንና የወረዳ የስራ ሃላፊዎች ላይ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ #እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል።

ቢሮው ለወረዳዎቹ በቂ በጀት ማስተላለፉን ገልጿል።

" ለሰራተኛው #ግማሽ_ደመወዝ በመክፍል ቀሪውን ለሌላ የወጭ ርዕስ ይጠቀሙበታል " ሲል ወቅሷል።

አሁን በተለያዩ ወረዳዎች እየተከፈለ ይገኛል የተባለው ደመወዝ በዞኑ መንግሥት ሰራተኞች ዘንድ አጥጋቢ ምላሽ ተደርጎ አልተወሰደም።

ሰራተኞቹ ለ ' ዶቼ ቨለ ሬድዮ ' በሰጡት ቃል ፤ " ምላሹ አጥጋቢ ያልሆነ ፣ የሰራተኛውን ስነ ልቦናም የጎዳ ነው " ብለውታል።

የመንግስት ሰራተኞቹ ፥ ደመወዛቸው ባልተለመደ ሁኔታ ተቆራርጦ እየተከፈላቸው እንደሚገኝ ተናግረው ፤ " የሰራተኞች ጥያቄው ተመልሷል ለማለት እንቸገራለን " ብለዋል።

በአብዛኞቹ ወረዳዎች ላይ አሁን እየተከፈለ የሚገኘው የደመወዛቸውን ከ40 እስከ 50 ፐርሰት ያህል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሰራተኞቹ ፦

ደሞዛችን እንደተፈለገ ተቆረጦ እየቀረ ነው፤

አከፋፈሉ የፋይናንስንም ሆኖ የመንግሥት ሰራተኛ አስተዳደር መመሪያን የሚጻረር ነው፤

ድርጊቱ #የደመወዝ_ቅሸባ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም ምክንያቱም እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል በትኛውም ዓለም ሰምተን አናውቅም ብለዋል።

ሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ዎላይታ ሶዶ ላይ የፋይናንስ ባለሙያዎች ሥልጠናዊ ውይይት አካሄዶ ነበር።

በመድረኩ የደሞዝ ጉዳይ በሰራተኞች ተነስቷል፡፡

የቢሮው ሃላፊ የሆኑት አቶ ተፈሪ አባተ ፥ ፋይናንስ ቢሮ ለወረዳዎች በቂ የበጀት ሀብት እያስተላለፈ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

ወላይታን ጨምሮ በክልሉ አንዳንድ ወረዳዎች ውቅጥ የፋይናንስ ቁጥጥር / ኦዲት / መደረጉን ጠቅሰዋል።

" ወደ ወረዳዎች ሚወርደው የበጀት ሀብት የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው፡፡ ይሁን አንጂ አንዳንድ ወረዳዎች ከአሰራር ውጭ ደመወዝ #በፐርሰንት_እየከፈሉ ሰራተኛው እንዲራብ ፣ በክልሉ ላይም እንዲያማርር እያደረጉ ይገኛሉ " ብለዋል።

ክልሉ በቀጣይ በእነኝህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ " #ለሽብረቃ የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመገደብ የሚያስችል የወጭ ቅነሳ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል " ሲሉ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

Credit - #ዶቼቨለሬድዮ
@tikvahethiopia