TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኤርትራ

ኤርትራ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረን አውሮፕላንን ከአየር ክልሏ ማስወጣቷ ተነግሯል።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ባየርቦክ ትላንት እንዳስታወቁት፤ ወደ ጂቡቲ ሲጓዝ የነበረው የጀርመን መንግስት አውሮፕላን ያለ እቅድ ሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዱን ገልጸለዋል።

ይህ የሆነ በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማለፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በ3 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለ3 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ በጉዞ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውም ጂቡቲ ነበረች።

ሚኒስትሯ ፤ ያለ እቅድ በሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዳቸው በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያለውን አለመረጋጋት ያመለክታል ብለዋል።

ትላንት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው ለማደር የተገደዱት ሚኒስትሯ ዛሬ በጅቡቲ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ " አውሮፕላኑን በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማብረር ፈቃድ እንዳልተሰጠው ያወቅነው ትናንት ጠዋት ከበረራው ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነበር " ብሏል።

አውሮፕላኑ #በበረራ_ላይ_እያለ ፈቃዱን ያገኛል ተብሎ በመወሰኑ ወደዚያ መሄዱንም ገልጿል።

ከቤርቦክ ጋር የተጓዙት ልዑካን ፤ አውሮፕላኑ እየበረረ ፈቃድ ማግኘት እንግዳ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ቤርቦክን ፤ የሱዳን ጦርነት ጉዳይ እና የቀይ ባህር የመርከብ መንገድ ጉዳይ ትኩረት አድርጓል የተባለው የምሥራቅ አፍሪቃ ጉብኝታቸውን ነገ በደቡብ ሱዳን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

#AlAinNews #DW

@tikvahethiopia