TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አባታዊ የደስታ መልዕክት !

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በወቅታዊ ጉዳይ አባታዊ የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ውድ ወገኖቻችን ጦርነትን የሰሙ ጆሮዎቻችን ዛሬ #ሰላምን እና #እርቅን በመስማታቸው ደስታችን ወደር የሌለው መሆኑን ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያውያት ልጆቻችን ለመግለጽ እንወዳለን።

አገራችን ኢትዮጵያን ከአስከፊ የጦርነት ታሪክ ለማውጣት፣ እግዚአብሔር በሰጣት መልካም ዕድል፣ የተፈጥሮና የሃይማኖት ሀብት እንድታድግ ሰላምን መናፈቅና የሰላም መልእክተኛ መሆን ያስፈልጋል።

ሀሳብ የበላይ ሲሆን የጦር መሣሪያ የእርሻ መሣሪያ ወደ መሆን ይለወጣል። እኛም በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪያችንን እያስተላለፍን የቆየን እንደመሆኑ መጠን በዚህ መልካም የምሥራች ደስ ብሎናል።

አሁንም ኢትዮጵያውያን በሙሉ አገሩ የሁላችን ነውና ልንጠብቀው፤ አለመግባባታችንን በውይይት ልንፈታው ፤ ቃላችንን ከመሬት ላይ አሳርፈን እርቁን እውነተኛ ልናደርገው ይገባናል።

#ወጣቶች ሲሞቱ ሳይሆን ተምረው ሲመረቁ ፤ ተዋደው ጋብቻ ሲመሠርቱ ለማየት እንናፍቃለን።

የተዘጉ ደጆች ሁሉ በምሕረት እንዲከፈቱ ፤ የተጨነቁ ሁሉ ፀሐይ እንዲወጣላቸው በብርቱ እንሻለን።

ለዚህ እርቀ ሰላም መምጣት በብርቱ የደከሙትን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አባላትንና የሰላም ጥሪ የተቀበሉት ልጆቻችንን እግዚአብሔር አምላካችን ዐስበ ሐዋርያትን እንዲከፍልልን እንመኛለን። ለሞቱት ዕረፍተ ነፍስን ለታመሙት ፍጹም ጤንነት እንዲሰጥልን እንለምናለን። "

(የቅዱስነታቸው መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA🇪🇹

ከቀናት በፊት በጎረቤታችን #ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በ "አልሸባብ" በተፈፀመ የሽብር ጥቃት እጅግ በርካታ ሰዎች መሞታቸው እና መቁሰላቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ፤ የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህንን ጥሪ ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት ዶክተሮችና የህክምና ቁሳቁሶችን እየላኩ ይገኛሉ።

ዛሬ ሀሙስ የሀገራችን #ኢትዮጵያ ዶክተሮች ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚደረገውን የአደጋ ጊዜ ምላሽ ለመቀላቀል ሞቃዲሾ ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ዶክተሮች አዳን አብዱሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሶማሊያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሊ ሀጂ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል እንደተደረገላቸው ከሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update • ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው ኔትዎርክ ጀምሯል ፤ አላማጣና ኮረም በሰዓታት ውስጥ አገልግሎት ያገኛሉ። ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው የኔትዎርክ አገልግሎት ጀመረ። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ፤ የኔትዎርክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት ዓዲ አርቃይ እና አካባቢው ዳግም የኔትዎርክ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ዛሬ ገልፀዋል። የጄኔሬተር ነዳጅ ወደ አካባቢው በመላክ…
በየትኞቹ አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት ጀመረ ?

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩና ዳግም ያስጀመረባቸውን አካባቢዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

የቴሌኮም አገልግሎት የጀመረባቸው አካባቢዎች ፦

- አላማጣ፣
- ኮረም፣
- ዓዲ አርቃይ፣
- ጸለምት፣
- ጪሮ ለና፣
- ጎብዬ ቆቦ፣
- ቆቦ ሮቢጥ፣
- ዞብል
- ዋጃ ናቸው።

#በሌሎችም የቴሌኮም አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች #በቅርቡ አገልግሎት ለማስጀመር እየሠራ እንደሚገኝ ኢትዮ ቴሌኮም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግጭት አካባቢዎች ተቋርጦ የከረመውን የባንክ አገልግሎት በፍጥነት ለማስቀጠል በከፍተኛ ርብርብ እንደሚሰራ ማምሻውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የፀጥታ_ችግር ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ  ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ…
* የፀጥታ ችግር

በአርሲ ጀጁ ወረዳ በ " ሒሩታ ዶሬ " ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎች ከፈቱት ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ ጥቃቱ ምሽት 2:00 - 3:00 ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

በአከባቢው ኔትዎርክ በመቋረጡ የጉዳቱን መጠን በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም ይህ መረጃም ከጥቃቱ ተርፈው ለህክምና ወደ አዳማ ከመጡ ሰዎች እንዲሁም በአከባቢው አቅራቢያ ኔትዎርክ በሚሰራባቸው ቦታዎች ካሉ ሰዎች ጠይቀው መረዳታቸውንም ነው የነገሩን።

" ይህ ጥቃት የመጀመሪው አይደለም " ያሉት መረጃውን ያደረሱን ሌላው የቤተሰባችን አባል ከ5 ቀናት በፊት አንድ ወጣት ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደለ አስረድተዋል።

ከትላንት በስቲያ ህይወታቸው ያለፈው 4ቱ ሰዎች በእድሜ የገፉ መሆናቸውን እንዲሁም ከመካከላቸውም አካል ጉዳተኞች መኖራቸውን ጠቅሰዋል። አንዷ የጥቃቱ ሰለባ በጾታ ሴት መሆናቸውን ገልጸዋል። የሚመለከተው አካል የከፋ ጥቃት ከመከፈቱ በፊት እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በዚህ ጉዳይ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* የፀጥታ ችግር በአርሲ ጀጁ ወረዳ በ " ሒሩታ ዶሬ " ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ምሽት ታጣቂዎች ከፈቱት ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል። አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ ጥቃቱ ምሽት 2:00 - 3:00 ላይ መድረሱን ገልፀዋል። በአከባቢው ኔትዎርክ በመቋረጡ የጉዳቱን መጠን በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም ይህ መረጃም ከጥቃቱ ተርፈው ለህክምና ወደ አዳማ ከመጡ ሰዎች እንዲሁም…
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦

- በምስራቅ ሸዋ ዞን ፤ በፈንታሌ ወረዳ መተሃራና አካባቢው ባንክ እና ኔትዎርክ ተቋርጦ ህዝቡ እየተጉላላ ነው። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉ ዘንድ ቤተሰቦቻችን ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ አካባቢ በሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮ በተደጋጋሚ ጊዜ ሰዎች መገደላቸው ፣መቁሰላቸው ፣ የኔትዎርክ አገልግሎትም ሲቋረጥ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

- አሁን ላይ ወቅቱ ዩኒቨርሲቲዎች ለእረፍት የወጡ ተማሪዎችን እየጠሩ ያለበት መሆኑን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ፣ ምስራቅ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ባሉ የፀጥታ ችግሮች ሳቢያ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ለመመለስ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ናቸው / አንዳንዶቹ በእግር ሁሉ ለመጓዝ መገደዳቸው ተጠቁመናል። በፀጥታ ችግር መንገድ የተዘጋባቸው አካባቢዎች ስላሉ ተቋማት ይህን ታሳቢ እንዲያደርጉ መንግስትም የፀጥታ ችግር ባለባቸው መንገዶች ደህንነትን የማረጋገጥ ስራ እንዲሰራ ቤተሰቦቻችን ጠይቀዋል።

- በኦሮሚያ ክልል ፤ የፀጥታ ችግሮች ባለባቸው አካባቢዎች ቤተሰቦቻቸው ያሉ አባላት የንፁሃን ሰዎች ህይወት እያለፈ ፣ ኢኮኖሚው እየደቀቀ፣ ሰላም ወጥቶ ለመግባት፣ ለተማሪዎች ትምህርት፣ ለመነገድ ፣ ለማረስ ፈተና እየሆነ ከመጣ አመታት ማለፉን በመግለፅ መፍትሄ እዲፈለግ ፤ ለሰሜን ኢትዮጵያው ችግር ከታሰጠው ትኩረት ትንሽ እንኳን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶ ለመፍትሄ ርብርብ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
ዛሬን ጨምሮ የዕረፍት ቀናቶችን የት ለማሳለፍ አስበዋል ?

የአዲስ አበባ ከተማን ገፅታ ከቀየሩ ፕሮጀቶች አንዱ " የወዳጅነት ፓርክ " ነው።

የዚህ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተከፍቶ በርካቶች እየጎበኙት እንደሆነ ይታወቃል ፤ ከቀናት በፊት ደግሞ የሁለተኛው ምዕራፍ በይፋ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተከፍቶ በነፃ እየተጎበኘ ነው።

የምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክት ምን ይዟል / ስለፓርኩስ የሚታወቀው ምንድነው ?

ይህ የምዕራፍ 2 የወዳጅነት ፓርክ በ11 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ነው ያረፈ ሲሆን 3 ክፍሎችም አለቱ።

1ኛ. የህፃናት መጫወቻ ስፍራ ፦

ሰፊውን የፓርኩን ክፍል የሚሸፍን ሲሆን ልጆች አካላዊ እና አእምሯዊ እድገታቸውን ለመጨመር እንዲያግዝ ተድረጎ ያተገነባ ነው። በተጨማሪ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን መለማመድ ያስችላቸዋል።

2ኛ. የወጣቶች የስፖርት ስፍራ፦

የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያው ስፍራ ወጣቶች የአካል ብቃት የሚሰሩበት እና አእምሯቸውን ዘና የሚያደርጉበት ሲሆን በውስጡ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ፣ የቴኒስ መጫወቻ ፣ የመሮጫ መም ፣ የባስኬት መጫወቻ የያዘ ነው።

3ኛ. የሰርግ አፀድ፦

ይህ የፓርኩ ክፍል ጥንዶች የሰርግ ስነስርዓታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ነው። ጥንዶች ጋብቻቸውን ሲፈፅሙ እንደአንድ አማራጭ አድርገው ሊወስዱት የሚችል ደረጃውን የጠበቀ ስፍራ ነው።

የወዳጅነት ፓርክ ምዕራፍ 2 እንደ ፕሮጀክት 1 ሁሉ ለፎቶ፣ ቁጭ ብሎ እራስን ለማዝናናት፣ ከራስ ጋር ለመሆን ምቹ ስፍራ ነው።

መግቢያ አለው ?

ፓርኩ ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ ከነገወዲያ እሁድ ድረስ #በነፃ ለጎብኝዎች ክፍት ሲሆን በቀጣይ ተመጣጣኝ የሆነ የመግቢያ ዋጋ ይፋ ይደረግለታል ተብሏል።

ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር እስከ እሁድ መጎብኘት ትችላላሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
* Confirmed

በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች በኩል ዝርዝሩን በተመለከተ በግልፅ ለህዝቡ ምንም ሳይባል ሰዓታት አልፈው ነበር።

ይህም አንዳንድ ሲሰራጩ የነበሩት የስምምነቱ " Draft " ወረቀቶች ትክክል ናቸው / ሀሰት ናቸው የሚሉ አካላትን ፈጥሯል።

ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በሰላም ንግግሩ ተሳታፊ የሆኑት እና እዚህ የስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ብዙ የቡድን እልህ አስጨራሽ ክርክሮች ተደርጎ የተፈረመበት ያሉትን ትክክለኛውና ዝርዝር ስምምነቱን የያዘውን ወረቀት አሰራጭተዋል።

(አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተረጋገጠ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰራጩት የስምምነቱን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia