TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ገንዘብ #አጭበርባሪዎች ጥቆማ!

TechTalk With Solomon⬇️

"ገንዘብ #አጭበርባሪዎች ጥቆማ! በርካቶች በኢትዮጵያ እና በሌላም ቦታ ያሉ ሰዎች "እኛ አናደርግላችኋለን" በሚሉ አጭበርባሪዎች በኩል #የቢትኮይን ኢንቨስትመንት ውስጥ እየገቡ እንዳለ እየተነገረኝ ነው! አንድ ጠቃሚ ምክር ልስጣችሁ፤ ማንም ሰው ወደናንተ ቀርቦ ሃብታም አደርጋችኋለሁ እያለ ለፍታችሁ የሰራችሁትን ገንዘብ ለዚህ ጉዳይ ቢጠይቃችሁ ፍጹም እንዳታረጉት! ይህ በአሁን ሰዓት እየተበራከተ ያለ ወንጀል/#ማጭበርበር ነው።

"ሰዎች ብር ሲሰሩ እያየሁ ነው" ትሉ ይሆናል። ይህ አይነት ወንጀል #ከክሪፕቶከረንሲ በፊትም የነበረ ሲሆን፣ ነገሩ እንዲህ ነው -በኢንቨስትመንት ዓለም የሚታወት አንድ አደገኛ ወንጀል አለ "ፖንዚ ስኪም" ይባላል። ይህ ማለት ገንዘባችሁን በናንተ ስም ኢንቨስት አድርጌ #ትርፍ አመጣላችኋለሁ የሚለው አካል አብዛኛውን ገንዘብ ራሱ ከበላ በኋላ፣ ከአዲሲሶቹ ተጠቂዎች የሰበሰውን ለበፊቶቹ ተጠቂዎች በመስጠት በእርግጥ ትርፍ እያስገኘ እንዳለ ማስመሰል ነው። ከዚህ ወንጀል በጣም በጣም በጣም ተጠበቁ!

ክሪፕቶከረንሲ ላይ እጅግ በመጠኑ ኢንቨስት ማድረግ ከተፈለገ (አሁን ብዙም ባይመከርም) በትክክለኛ ሁኔታ እና በታወቁ አፖች (መተግበሪያዎች) በራሳችሁ ማድረግ ትችላላችሁ (ችግሩ በኢትዮጵያ የባንክ ካርድ አሰራር ማነስ እና እነዚህ አፖች ምናልባትም በኢትዮጵያ ላይሰሩ መቻላቸው ነው)"

@tsegabwolde @tikvahethiopia