TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE • 12,787 ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም ብለው ጥለው ወጥተዋል። • በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል። ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ገልጿል። ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ለፈተና ከተቀመጡ 595 ሺህ ተፈታኞች ውስጥ 586 ሽህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን ወስደዋል ብሏል። " ፈተናው በተጀመረበት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከተሳተፈው ሰው ብዛት፣ ከተፈታኙ ብዛትና በዚህ መልኩ ፈተና ሲሰጥ የመጀመርያ ከመሆኑ አንጻር የሚጠበቅ ቢሆንም አጋጥመዋል ያላቸው ቁልፍ ችግሮች ፦

- በቂ ኦሬንቴሽን ባለማግኘት ወይም በማወቅም ጭምር የተከለከሉ ቁሶችን ይዘው የመጡና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች መኖራቸው፤

- ነፍሰጡርና መጫት ተፈታኞች በሌላ ዙር እንደሚፈተኑ አስቀድሞ ቢገለፅም በዚህኛው ዙር ለፈተና መምጣታቸው፣

- በፈተና አዳራሽ #በጋራ_ካልሰራን ብለው ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ግብ ግብ የፈጠሩ ተፈታኞች ማጋጠማቸው፤

- ከተሰጣቸው መመሪያና ከፈታኝ የማይጠበቅ ተግባር ላይ የተሳተፉ የፈተና አስፈፃሚዎች ማጋጠማቸው፤

- በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ዘግይተውና አምሽተው በዩኒቨርስቲዎች የደረሱ መኖራቸው፤

- ተማሪዎች ስልክ እንደሌላቸውና ፈተና ቢወጣ እንኳ እንደማያገኙ እየታወቀ ፈተና እንለጥፋለን የሚሉ " የቴሌግራም ገፆች " ማጋጠማቸውና ፈተና ካለቀ ወይም በመሰጠት ላይ እያለ አንድም ሁለትም ገፅ መለጠፋቸው፤ 

(የትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ብቻ ተማምነው ወደፈተና ማዕከላት እንዲመጡ ጠየቀ።

በራሱ በመተማመን መፈተን ያልፈለገ ተማሪ ወደ ማእከላት ባይመጣ ይመረጣል ብሏል ቢሮው።

ከሰሞኑ በጥቂት ማእከላት የተፈጠረው ክስተት የአማራ ክልልን ህዝብና ተማሪዎችን የማይመጥን ድርጊት ነው ሲልም ገልጿል።

በቀጣይ ሳምንት ፈተና የሚወስዱት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከተጠናቀቀው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት በመማር ፍጹም ለአሉባልታና ለወሬ ሳይበገሩ ፈተናቸውን በሰላም እንዲወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

ለቀጣዩ ፈተና ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አካላት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም በበኩሉ ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በጥቂት ማእከላት የተፈጠረው ችግር የወላጆችን ፣የመምህራንን እና አጠቃላይ የማህበረሰቡን ልፋት መና ያስቀረ ፤ በቀጣይ በፍጹም መደገም የሌለበት ስህተት ነው ብሏል።

ተማሪዎች ዩንቨርስቲ የሚመጡት ፈተና ለመፈተን እንጂ ለሌላ ተልእኮ አለመሆኑን በመገንዘብ የተቀመጡትን ህግና ደንቦች አክብረው እንዲፈተኑ ጠይቋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተና መርሐግብር ከጥቅምት 08 እስከ 11/ 2015 ዓ. ም የሚሰጥ ሲሆን በአማራ ክልል ብቻ ከ119,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ።

በዚሁ አጋጣሚ ፦

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ከባለፈው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ጋር በተያያዘ በተለያዩ ተቋማት የተፈተኑ ተማሪዎች አስተያየት፣ የወላጆችን መልዕክት ስንቀበል ውለናል አሁንም እየተቀበለን ሲሆን ተማሪዎች መረጃ ስትልኩ " ሰማሁ " ፣ " እየተባለ ነው "  እያላችሁ ሳይሆን በትክክል የምታውቁትን እና ያረጋገጣችሁትን ብቻ እንድትልኩ እንጠይቃለን።

@tikvahethiopia
#ከሰሞኑን

(ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት)

- በኢህአዴግ ዘመን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ፤ " የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር " ሆነው ሰሞኑን ተሹመዋል።

በሌላ የሹመት መረጃ ፤ የቀድሞ የ " ብአዴን " ከፍተኛ አመራር ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። ሹመቱ ተቋሙን ለ10 ወራት በዋና ዳይሬክተርነት የመጡር አቶ ብሩ ወልዴ ከኃላፊነት በመልቀቃቸው ነው።

- ሰሞኑን አሜሪካ ፣ ብሪታንያ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ ፣ ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም እና የሰላም ድርድር እንዲጀመር በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

በመግለጫው ፦

• ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወታደራዊ ግጭት እንዲቆም ፤ ይህንን ለማድረግ ስምምነት እንዲደረስ፣ 

• የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ

#የኤርትራ_ሠራዊት ከግጭት ተሳትፎው እንዲታቀብ እና ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር መለስ ዓለም ፥ " መግለጫው ከዚህ በፊት ከወጡት መግጫዎች የተለየ ነገር የለውም " ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ፤  " መንግሥት ሰላም እንዲመጣ ቀደም ሲል የወሰዳቸው የመተማመን ምንፈስ የሚፈጥሩ እርምጃዎች አሉ። " ያሉ ሲሆን " መንግሥት ለሰላም ዝግጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ሞኢቦን በቀለ ከትላንት በስቲያ በቡራዩ ከተማ እና አዲስ አበባ አዋሣኝ (ልዩ ቦታው ሳንሱዚ) ቤታቸው አካባቢ ምሽት 1 ሰዓት ገደማ " ማንነታቸው ባልታወቀ " ሰዎች #በጥይት_ተመተው መገደላቸውን ፓርቲው ገልጿል። አቶ ሞኢቦን በቀለ በጥይት ከተመቱ በኃላ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም።  ኦነግ ግድያው ፤ " በገለልተኛ አካል " ይጣራሊኝ ሲል ጠይቋል።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፤ መተከል ዞን፤ ማንዱራ ወረዳ #በታጣቂዎች_ጥቃት የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ሂስ ሄጮን ጨምሮ ስድስት (6) ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾች መካከል ሹፌራቸው እና አንድ የመከላከያ ፤ ሶስት የፌዴራል ፖሊስ ይገኙበታል።

- የኢትዮጵያ መንግስት #ለአይርላንድ በፃፈው ደብዳቤ ሀገሪቱ " በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ደባ እየፈፀመች " መሆኑን በመገልፅ ከዚህ አይነት ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል። ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያያዞ አየርላንድ " ህወሓትን በመደገፍ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ውስጥ ያላትን የተለዋጭ መቀመጫ በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲፈጠር ግፊት እያደረገች ነው " ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት እንዲሻክር እየተንቀሳቀሰች ነው ሲል ገልጿል። ሀገሪቱ ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል።

NB. አየርላንድ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ለም/ቤቱ ጥያቄ ከሚያቀርቡ አገራት መካከል ዋነኛዋ ናት።

#ከሰሞኑን ፦ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተሰባሰቡ እና በአጭሩ የቀረቡ።

@tikvahethiopia
#መታወቂያ

በአዲስ አበባ ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ እንደሚጀመር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ገልፀዋል።

አቶ ጥራቱ በየነ ለኢዜአ የሰጡት ቃል፦

- በመታወቂያ አሰጣጥና እድሳት ዙሪያ ለተስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች ዘላቂ እልባት በመስጠት ችግሩን ለመፍታት አገልግሎቱ በጊዜያዊነት እንዲቆም ተደርጎ ነበር።

- በብልሹ ተግባሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አመራሮችና ሰራተኞችን በመለየት ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተከናውኗል።

- በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተለይም ችግሩ ጎልቶ በታየባቸው 37 ወረዳዎች በተደረገ ክትትል 90 አመራሮችና ባለሙያዎችን ተጠያቂ ተደርጓል።

- ታግዶ የቆየው #የመታወቂያ_እድሳት ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ ይጀመራል። ከዚህ ጎን ለጎን የከተማዋ ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆንኑአሰራሩን የማዘመን ስራ ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡

- በአሁኑ ወቅት የራሳቸው መለያና ምሥጥራዊነት ያላቸው መታወቂያ ለመስጠት የሚያገለግሉ ወረቀቶች በመታተም ላይ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ ለነዋሪው የመስጠት ተግባር ይከናወናል ብለዋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አምባሳደር ማይክ ሐመር ኬንያ ይገኛሉ። የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ተነጋግረዋል። ፕሬዜዳንት ሩቶ ከአሜሪካው አምባሳደር ሐመር ጋር ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ " ሰላምና መረጋጋት ለአገሮች ልማትና ብልፅግና የግድ አስፈላጊ ነው " ያሉ ሲሆን ኬንያ ፤ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም…
#Update

አምባሳደር ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ማይክ ሐመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር #ዛሬ ውይይት አካሂደዋል።

አቶ ደመቀ መኮን በውይይቱ ወቅት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር በበኩላቸው፤ አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " በውይይቱ ረጅም ዘመን ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምተዋል " ሲል አሳውቋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ከቀናት በፊት #ኬንያ እንደነበሩና ከኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

አሜሪካ አምባሳደር ሐመርን ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም እና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ወደ ኬንያ ፣ #ደቡብ_አፍሪካ ፣ ኢትዮጵያ እንደላከች ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

Photo Credit : Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

@tikvahethiopia
#ዋጋ

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ያለአገልግሎት የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን መሸጫ የዋጋ ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር)  64.00

2. ካስት አይረን  - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.75

3. አልሙኒየም - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 120.00

4. ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ / ማሽነሪ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.25

5. ያገለገለ የተሽከርካሪ / ማሽነሪ መለዋወጫ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ  (በብር) 51.25

በዚህ መሰረት መሰሪያ ቤቶች ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን የማዕድን ሚኒስቴር ለሚመድብላቸው የብረታ ብረት አቅላጭ ኢንዱስትሪ/ለአምራች ኢንዱስትሪ #ብቻ በቀጥታ እንዲሸጡ ከሽያጭም የሚገኘውን ገንዘብ ወደ መንግስት ማዕከላዊ ግ/ቤት የባንክ አካውንት ገቢ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

(ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዙትን ደብዳቤዎች ይመልከቱ)

Credit : M. (Tikvah Family)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ፤ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  ደግሞ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።

ዛሬ 3ኛው የአ/አበባ ምክር ቤት 2ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው እያካሄደ ይገኛል።

በዚህም ጉባኤ በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ምክር ቤቱ የተለያዩ ኃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል።

1. ዶ/ር ቀነዓ ያደታ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

2. አቶ ምትኩ አስማረ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

3. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

4. ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ - የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ

5. ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር

6. አቶ ጀማል ረዲ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ፤ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  ደግሞ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሾሙ። ዛሬ 3ኛው የአ/አበባ ምክር ቤት 2ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው እያካሄደ ይገኛል። በዚህም ጉባኤ በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ምክር ቤቱ የተለያዩ ኃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል። 1. ዶ/ር ቀነዓ…
#AddisAbaba

የወ/ሮ ሀቢባ ዑመር ያለመከሰስ መብት ተነሳ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ የነበሩትንና የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑትን የወ/ሮ ሀቢባ ዑመርን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።

ግለሰቧ በክፍለ ከተማው በአርሶ አደር እና አርሶ አደር ልጅ ሰበብ በተፈፀመ " የመሬት ምዝበራ " ተጠርጥረው መሆኑን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

• ከወራት በፊት "በቅርብ ቀናት በድጋሚ ይወጣል። " ሲባል የነበረውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ ነው ተብሏል።

• ትክክለኛው የዕጣ መውጫው ቀን እስካሁን አይታወቅም።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰረዘውን የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ ሲል አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ ዛሬ ለከተማው ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ " ከዚህ በፊት በ40/60 እና 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም ዕጣ በማውጣት ሂደት ያጋጠመንን ችግር የሚቀርፍ የዕጣ አወጣጥ ስርስዓት በመከተል ለባለ ዕድለኞች ዕጣ ለማውጣት ሂደቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የ40/60ና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሮ እንደነበር እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ የዕጣ አወጣት ሂደቱ ፍትሃዊ እንዳይሆን እና እንዲጭበረበር አድርገዋል የተባሉ ኃላፊዎች እንዲሁም ሰራተኞች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ መደረጉ አይዘነጋም።

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ በተለይም ደግሞ ፤ የ2005 የ20/80 የባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ለ9 ዓመታት ቆጥበው ስለምን በዕጣው ሊካተቱ እንዳልቻለ በግልፅ ማብራሪያ ሲጠይቁ፤ የቀጣዩ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከመውጣቱ በፊትም መፍትሄ እንዲፈለግላቸው መጠየቃቸው ይታወቃል።

ሌላው ከዚህ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ጋር በተያያዘ ፤ ዕጣው በወጣበት ዕለት የስም ዝርዝራቸውን በቀጥታ በቴሌቪዥን መስኮት የተመለከቱና በመድረክ ላይም ስማቸው ሲጠራ የነበሩ ነዋሪዎች ተሰባስበው የእነሱ ጉዳይ በልዩ መልክ እንዲታይላቸው ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበዋል።

" ህጋዊ በሆነ መንገድ ከእለት ጉርሳችን ላይ ቆጥበን በትእግሥት ስንጠብቅ የነበርን ምንም አይነት ህገ ወጥ የሆነ ተግባር ውስጥ የሌለን እድለኞች እድላችን ተቀምተን በአጭር ቃል ተሠርዙዋል መባላችን እጅግ ያማል " ያሉት እኚህ ነዋሪዎች የአ/አ ከተማ አስተዳደር ንፁሃንን ከወንጀለኞች በመለየት ጉዳያቸውን በልዩ ሁኔታ እንዲያይላቸው ነው የጠየቁት።

በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚጠብቁት የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የሚወጣበት ቁርጥ ያለ ቀን ባይታወቅም የከተማው አስተዳደር ዕጣውን ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia