TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መውሊድ

የ1497ኛው የመውሊድ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በታላቁ አንዋር መስጂድ ያለው የበዓል የአከባበር ሁኔታ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#UNHRC

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ኮሚሽን የሥራ ጊዜ ለአንድ ዓመት ተራዝሟል ፤ የስራ ጊዜው የተራዘመው ትላንት አጄኔቫ ውስጥ የተመድ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ም/ቤት አባላት ውሳኔውን በተመለከተ በሰጡት ድምጽ ነው።

የውሳኔ ሀሳቡ ጠባብ በሆነ የድምፅ ልዩነት ነው ተቀባይነት ያገኘው።

47 አባላት ካሉት የምክር ቤቱ አባላት መካከል የመርማሪ ቡድኑን ሥራ መቀጠል 21 ሀገራት ሲደግፉት 19ኙ ተቃውመውታል።

ከማላዊ " ድምፀ ተአቅቦ  " በስተቀር የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ሁሉም የአፍሪካ አገራት ውሳኔውን ተቃውመውታል።

የደገፉ ፦

- አርጀንቲና
- አርሜኒያ
- ብራዚል
- ቼክ ሪፐብሊክ
- ፊንላንድ
- ፈረንሳይ
- ጀርመን
- ሁንድራስ
- ጃፓን
- ሉቱንያ
- ሉክዘንበርግ
- ማርሻል አይላንድስ
- ሜክሲኮ
- ሞንቴኔግሮ
- ኔዘርላንድስ
- ፓራጓይ
- ፖላንድ
- ኮርያ ሪፐብሊክ
- ዩክሬን
- ዩናይትድ ኪንግደም
- አሜሪካ

የተቃወሙ ፦

- ቤኒን
- ቦሊቪያ
- ካሜሮን
- ቻይና
- ኮትዲቯር
- ኩባ
- ኤርትራ
- ጋቦን
- ጋምቢያ
- ህንድ
- ሊቢያ
- ሞሪታንያ
- ናሚቢያ
- ፓኪስታን
- ሴኔጋል
- ሶማሊያ
- ሱዳን
- ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ
- ቬንዙዌላ

ድምፀ ተአቅቦ ፦

- ኢንዶኔዥያ
- ካዛኪስታን
- ማላዊ
- ማሌዥያ
- ኔፓል
- ኳታር
- ሁዝቤክስታን

የውሳኔ ሀሳቡን መፅደቅ ተከትሎ በተ.መ.ድ. የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅ/ቤት (ጄኔቫ) ባወጣው መግለጫ ፤ የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወሙ እና አጋርነትን ላሳዩ ፣ የድምፀ ተአቅቦ ላደረጉ የም/ቤት አባላት ምስጋና አቅርቦ ፤ በሰጡት ድምፅ ጣልቃ ገብነትን፣ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማተራመስንና ማደፍረስን ነው የተቃወሙት ብሏል።

(የፅ/ቤቱ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ ክልል በረራ ማድረጉን ዛሬ ገልጿል።

ይህ ጉዞ ከ6 ሳምንታት በኋላ የመጀመሪያው ነው።

ድርጅቱ 34 ሰራተኞቹን ከክልሉ ማስወጣቱን ገልጿል።

ተጨማሪ በረራዎች በመጪዎቹ ቀናት በማድረግ ሰራተኞቹን ከመቐለ ለማስወጣት ቀጠሮ መያዙንም የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" ስልክ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ገልጿል።

የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል ያለው አገልግሎቱ ከዚህ በተጨማሪ አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል ሲል አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ #ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

ድርጊቱ #ከፍተኛ_የፈተና_ደንብ_ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ሲልም አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
" ከ90 በመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ እስካሁን ባለው አፈፃፀም ይህ ነው የሚባል ችግር እንዳልገጠመና አብዛኛው / ከ90 በመቶ በላይ ተፈታኝ ተማሪ / ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቱን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን የተነገሩት ትላንትና ምሽት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተፈታኝ ተማሪዎችን እና እየቀረበላቸው ያለውን መስተንግዶ በአካል ተገኝተው በተመለከቱበት ወቅት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ነው።

ከ90 በመቶ በላይ ተማሪ ወደ መፈተኛ ተቋሙ መግባቱን የተገለፁት ሚኒስትሩ ሙስሊሞች እና የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አማኞች #ዛሬ እሁድ ጥዋት እንደሚገቡ ፤ ከዚህ በኃላ ሁሉም ተማሪ ገብቶ #እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ ሰኞ ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ " ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። " ያሉ ሲሆን " ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው። " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተማሪዎች የተሰጣቸውን መመሪያ አክብረው ፤ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ እንዲሁም በምንም ነገር እንዳይሸበሩ አደራ ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ለተፈታኞቹ " የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ " ሲሉ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

@tikvahethiopia
" ለፈተና ሄደው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለወለዱ ተፈታኞች በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣቸዋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በእርግዝና ላይ ላሉ እና ወልደው ህጻንን ጡት እየመገቡ ላሉ ለተመዘገቡ ሴት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የእነርሱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ስርዓት በቀጣይ መዘጋጀቱን አሳውቋል።

በመሆኑም ተፈታኞቹ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሚሰጠው ፈተና መፈተን አያስፈልጋቸውም ብሏል።

ይህም ከወራት በፊት ከወረዳ ደረጃ አንስቶ ገለጻ ተሰጥቷል ፤ መመሪያም ሆኖ ወርዷል ሲል አስረድቷል።

" ሆኖም ለመፈተን ወደዩኒቨርሲቲ ከመጡ ተፈታኞች መካከል ወደ ተቋማቱ እንደደረሱ የወለዱ እንዳሉ ሪፖርት ደርሶናል " ያለው አገልግሎቱ " እነዚህ ወላድ ተፈታኞች የቤተሰብ እንክብካቤና ፈተናውን ለመፈተንም አካላዊ ማገገሚያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው እሙን በመሆኑ በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ አገልግሎቱ ዕድል ሰጥቷቸዋል " ሲል አሳውቋል።

ይህ ታውቆ ቀድሞ በተላለፈው መመሪያ መሠረት በመጀመሪያው ዙር መፈተን የማይችሉ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለፈተና ሄደው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለወለዱ ተፈታኞች በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣቸዋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በእርግዝና ላይ ላሉ እና ወልደው ህጻንን ጡት እየመገቡ ላሉ ለተመዘገቡ ሴት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የእነርሱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ስርዓት በቀጣይ መዘጋጀቱን አሳውቋል። በመሆኑም ተፈታኞቹ ከመስከረም…
#NationalExam

የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከነገ መስከረም 30 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ነገ ፈተናቸውን የሚፈተኑት በመጀመሪያ ዙር ወደ መፈተኛ ማዕከላት / ዩኒቨርሲቲ የገቡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ ስለፈተናው አጠቃላይ (ኦረንቴሽን) ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በፈተና ወቅት መከተል ስላለባቸው የስነምግባር መርሆች፣ የሰዓት አከባበርን በተመለከተ ፣ የተብራራላቸው ሲሆን የመፈተኛ ጣቢያ እና ክፍላቸውን ለይተውም እንዲያውቁ መደረጉን ሰምተናል።

ከተፈታኝ ተማሪዎች በተጨማፊ ፈታኞች፣ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ማየት ለተሳናቸው ተፈታኝ አንባቢዎችና ለመልስ ወረቀት ቆጣሪዎች ገለፃ (ኦረንቴሽን) ተሰጥቷቸዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከነገ ጥዋት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2 ድረስ ይሰጣል፤ ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

የ12ኛ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናው ጥብቅ በሆነ ዲሲፕሊን እንደሚመራ ተገልጾልናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈታናን ይመለኛል!

@tikvahethiopia