TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወቅታዊ መራር ቀልድ...

#ሽንኩርት

"ድሮ ሲላጥ ነበር የሚያስለቅሰው ዘንድሮ ስትገዛው ነው..."

√ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የተገኘ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሽንኩርት

በቤንች ሸኮ ዞን የደቡብ ቤንች ወረዳ ገበሬዎች ለሚያመርቱት የሽንኩርት ምርት የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።

በተለያየ ጊዜ ሽንኩርት በሀገሪቱ ያሉ ገበያዎች ላይ ከዋጋዉ መናር ባለፈ የአቅርቦት ችግሩም ጎልቶ ሲነሳ ይታያል።

በቤንች ሸኮ ዞን የተመረተው የሽንኩርት ምርት ግን የሚያነሳዉ አጥቶ ሊበላሽ መሆኑ ገበሬዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተናግረዋል።

ዞኑ በኩታ ገጠም አሰተራረስ ስልት ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ዉጤታማ ከሆኑ ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን የደቡብ ቤንች ወረዳ ደግሞ ግንባር ቀደም ነው።

ይሁንና የገበያ ትስስር አለመኖሩ ሽንኩርቱ ከማሳ ሳይነሳ ይቆይ ዘንድ ምክንያት ሆኗል።

በመሆኑም የወረዳዉ ገበሬዎች ሽንኩርቱ ከመበላሸቱ በፊት የሚመለከተዉ አካል ለኛም ሆነ በሀገር ደረጃ ፋይዳ ያለውን ሸንኩርት እንዲነሳ እንዲያደግ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህ አመት በሰሩት ጠንካራ ስራ በሄክታር 1200 ኩንታል ሽንኩርት መገኘቱንና ባጠቃላይ 1622 ሄክታር መሬት በምርት መሸፈናቸዉን ገልጸዋል።

የገበያ ትስስሩን በተመለከተ በተደጋጋሚ መጠየቃቸዉን የሚገልጹት ገበሬዎቹ በዚህ ምክኒያት ችግር ላይ መዉደቃቸዉን ያነሳሉ።

የደቡብ ቤንች ወረዳ አስተዳደር  በበኩሉ የዞንና የክልል የንግድ ማህበራት እንዲሁም  በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነጋዴዎች ፣ በተማሪ ምገባ ፕሮግራም የሚሳተፉ ትምህርትቤቶችና የከተማ መስተዳድሮች  የሰንደይ ማርኬቶች ሽንኩርቱን በማንሳት ገበሬዉን በማገዝ ራሳቸዉም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጥሪዉን ያስተላለፉት የወረዳዉ ም/ አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ተስፋዬ እንደገለጹት ባካባቢዉ ካሁን በፊት ባልነበረ መልኩ ከፍተኛ የሽንኩርት ምርት መመረቱን ጠቅሰዉ ለገበሬዉ የንግድ ትሰስር ለመፍጠር አየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የቲክቫህ ቤተሰብ ሀዋሳ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ሐረሪ

" የሽንኩርት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስደናል " - የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ

የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ " የሽንኩርት ዋጋን ያለቅጥ አንረዋል " ባላቸው የሐረር ከተማ ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በዳቦ ነጋዴዎችም ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ " የሽንኩርት ዋጋን ያላግባብ ያስወድዳሉ " ያላቸውን 3 ዋና ዋና ነጋዴዎችን ጨምሮ 17 የሽንኩርት አከፋፋዮችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጿል።

በሽንኩርት ነጋዴዎቹ ላይ ዕርምጃ ከመወሰዱ በፊት ቀደም ብሎ የማወያየት ሥራ መከናወኑን አመልክቷል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፦ " ባቢሌ አካባቢ የተፈጠረውን የአንድ ቀን ግጭትና መንገድ መዘጋት ተጠቅመው በሽንኩርት ላይ የተጋነነ ዋጋ ጨመሩ፡፡

ነጋዴዎቹን ቢሮ ድረስ ጠርተን ከማወያየት ባለፈ ቦታው ድረስ ባለሙያ በመላክ ሁኔታውን ገምግመናል፡፡

በጉዳዩ ላይ በመተማመን ዋጋውን ለማስተካከል ቃል ገብተው ቢሄዱም፣ ዋጋውን ባለማስተካከላቸው ወደ ዕርምጃ ተገብቷል። " ብለዋል።

ዕርምጃ የተወሰደባቸው የሽንኩርት ነጋዴዎቹ በሐረር ከተማ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎችም የማከፋፈል ሥራ የሚሠሩ ዋና ዋና ነጋዴዎች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ከ110 ብር እስከ 150 ብር አሻቅቦ የነበረው የአንድ ኪሎ የሽንኩርት ዋጋ ከዕርምጃው በኋላ መስተካከሉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ ዳቦ ቤቶችን እና ነጋዴዎችን በቀጣይ ሳምንት በቢሮው ሰብስቦ እንደሚያነጋገር አሳውቋል።

የዳቦ ግራምና ዋጋ የሚያጭበረብሩ እንዲያስተካክሉ የአንድ ሳምንት ወይም የአሥር ቀን ገደብ ይሰጣል ብሏል።

ማስተካከያ ባላደረጉ ላይ ግን ልክ እንደ ሽንኩርት ነጋዴዎቹ ሁሉ ዕርምጃ ይወሰዳል ሲል ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

#ሽንኩርት ፦ የሽንኩርት ዋጋ በመዲናዋ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ዋጋው አልቀመስ ካለ ሰንበትበት ብሏል። በርካቶች በዋጋው ንረት ሸምቶ ለመግባት ማቸገራቸውን ይገልጻሉ። እርሶስ በጉዳዩ ላይ ምን ይላሉ ? በዚህ ይነጋገሩ @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia