TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MadingoAfework

ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MadingoAfework ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። @tikvahethiopia
" አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል " - ፖሊስ

ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ፤ ድምፃዊው ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ለሕክምና መሄዱና ሕክምና ማድረጉን ከቆይታ በኋላም ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

ማዲንጎ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ኢብኮ ዘግቧል።

የድምፃዊው ወዳጆች በበኩላቸው ፤ ማዲንጎ ህመም ተሰምቶት እራሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ህክምና ስፍራ መሄዱን ከዛ በኃላ ህይወቱ እንዳለፈ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አስክሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል " - ፖሊስ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ከሆነ ፤ ድምፃዊው ዛሬ ጠዋት ላይ ሕመም ተሰምቶት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወደ ሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ለሕክምና መሄዱና ሕክምና ማድረጉን ከቆይታ በኋላም ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል። ማዲንጎ ምንም ዓይነት አካላዊ…
ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ?

- ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው።

- ማዲንጎ አፈወርቅ ያደገው በጦር ቤት ውስጥ ነው፤ እናት እና አባቱ "ተገኔ" /የኔ ጠበቃ/ ነበር የሚሉት፤ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ተገኔ" ነው። ማዲንጎ የሚለውን ስም ያገኘው በወታደር ቤት ውስጥ እየሰራ እያለ ነው፤ ከዛ በኃላ መጠሪያው ሆኖ ቀጥሏል።

- በልጅነቱ የሙዚቃ ፍቅር ያደረገበት ማዲንጎ ከደብረ ታቦር ወደ አዘዞ በተመለሰበት ወቅት በ7ኛ ክፍለ ጦር ካምፕ ውስጥ በ603ኛ ኮር ውስጥ ያለ የሙዚቃ ቡድን ልምምድ ሲያደርግ በመግባት ዘፈን እንደሚችል በመግለፅ እድል እንዲሰጠው ይጠይቃል፤በኃላም እድል ተሰጥቶ የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ ከተጫወተ በኃላ አድናቆት በማግኘቱ ተቀባይነት አግኝቶ በዛው ሊቀጥል ችሏል።

- ማዲንጎ ከጦሩ ከወጣ በኃላ በ1982 ዓ/ም አካባቢ ገና በ12 ዓመቱ በባህር ዳር የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አንድም ድምፃዊ የመሆን ህልሙን መስመር ያስያዘበት በሌላ በኩል ገቢ በማግኘት እራሱንና ቤተሰቦቹን ማገዝ የቻለበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል።

- ማዲንጎ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኃላ በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች የተለያዩ አንጋፋ ድምፃዊያንን ስራዎች ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን በኃላም የራሱን ስራዎች (ነጠላና የአልበም ስራዎች) ለአድናቂዎቹ አቅርቧል።

- ማዲንጎን በስራዎቹ የሚያውቁት ወዳጆቹ ዜማ በመያዝ ችሎታ፣ ሙዚቃን አሳምሮ በመጫወትና የአድናቂዎቹን ቀልብ በመሳብ የተካነ በማህበራዊ ህይወቱም ተግባቢ፣ ቅንና ተጫዋች እንደሆነ ይመሰክሩለታል።

(ከጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም/ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘ መረጃ)

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ? - ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው። - ማዲንጎ አፈወርቅ ያደገው በጦር ቤት ውስጥ ነው፤ እናት እና አባቱ "ተገኔ" /የኔ ጠበቃ/ ነበር የሚሉት፤ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ተገኔ" ነው። ማዲንጎ የሚለውን ስም ያገኘው በወታደር ቤት ውስጥ እየሰራ እያለ ነው፤ ከዛ በኃላ መጠሪያው…
" እስካሁን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው የለም፤ ነገር ግን አንድ ሐኪም ቃል እንዲሰጥ ተደርጎ ተለቋል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አስክሬን ምርመራ እንደተጠናቀቀ ውጤቱ ለህዝብ ይገለፃል ሲል አሳውቋል።

ማምሻውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፤  " ማዲንጎ ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 17/2015 ዓ.ም. ጠዋት 1፡30 አካባቢ ለሐኪሙ ስልክ እንደደወለና ወደ ክሊኒክ መሄዱን ፖሊስ ተረድቷል። " ብለዋል።

ከዚያም በኋላ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወደሚገኘው አንድ የግል ክሊኒክ በመሄድ የህመም ማስታገሻዎችን እና ሌሎች መድኃኒቶችን ወስዶ እንደነበር ተናግረዋል።

ማዲንጎ ሕይወቱ ያለፈው ረፋድ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ገልፀዋል።

የድምጻዊ ማዲንጎ አስክሬን ሕይወቱ ካለፈበት የግል ክሊኒክ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዶ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ማርቆስ " ፖሊስ በቀረበለት አቤቱታ መሠረት የድምጻዊውን ሞት መንስኤ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን እየተጠባበቀ ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

ምርመራው እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ፖሊስ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ከማዲንጎ ህልፈት ጋር በተያያዘ ህክምና ካገኘበት ክሊኒክ ሠራተኞች ታስረዋል ስለሚባለው ጉዳይ ም/ኮማንደር ማርቆስ ፤ " እስካሁን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው የለም፤ ነገር ግን አንድ ሐኪም ቃል እንዲሰጥ ተደርጎ ተለቋል " ሲሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Somalia #Ethiopia

የሶማሊያ ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ኘሬዝደንት ሃሰን ሼክ መሃሙድ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሃሰን ሼክ መሃሙድ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱ ሃገራት እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ፕሬዜዳንቱ ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ በተለያዩ ሀገራት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

Photo Credit : የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰን ግድያ አስመልከቶ ባወጣው መግለጫ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ተጨማሪ የጸጥታ ሥጋቶች በመኖራቸው በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰቡን ይታወሳል። ኢሰመኮ…
" ነዋሪዎቹ ጠባቂና ከለላ አጥተዋል ፤ እየደረሰ ያለው ስቃይ ከፍተኛ ነው " - የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ቲክቫህ ቤተሰቦች

ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል በተለይ ደግሞ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በዛው አካባቢ ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ አባላት አሳውቀው ነበር።

ባለው ሁኔታ የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት እንኳን ለማወቅ ስልክ ሊሰራ ባለመቻሉ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸውን ሲገልፁ ነበር።

አሁንም ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። ምን ያህል ሰዎች እንኳን ህይወታቸውን እንዳጡ ማወቅ አዳጋች ሆኗል።

ትላንት መልዕክታቸውን የላኩልን አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ " በተለይ በአሙሩ ፣ ጃርዳጋ ጃርቴ ፣ አቡና ህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት ነው። በእነዚህ ቦታዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በዞኑ ውስጥ ያለው ህዝብ በሰላም እጦት ከፍተኛ ስቃይ ላይ ነው " ብለዋል። "

የፖለቲካ ሊህቃን ጉዳዩን ለራሳቸውን የፖለቲካ ጥቅም ሲሉ እያባባሱት ነው " ያሉት እኚሁ የአካባቢው ነዋሪ " የአካባቢው ነዋሪዎች ጥበቃ እና ከለላ አጥተዋል ፤ መንግስት ታክስ ይሰበስባል ነገር ግን ምንም ጥበቃ እያደረገላቸው አይደለም ይልቁንም ጉዳዩ ለፖለቲካ አለማ እየዋለ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ሌላ የቤተሰባችን አባል ደግሞ ፤ " በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በጃርደጋ ጃርቴ፣ አሙሩ ያለው ሁኔታ በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ የማይተናነስ ነው " ብለዋል። አብዛኛው ቦታ ስልክ ዝግ መሆኑን ገልፀው አልፎ አልፎ በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሰዎች ህይወት እያለፈ እና ቤቶች እየወደሙ መሆኑን ሰምተናል ሲሉ ገልፀዋል።

ሌላኛው የቤተሰባችን አባልም ፤ " በወለጋ ያለው ሁኔታ በቂ ትኩረት አላገኘም " ሲሉ ወቅሰዋል ፤ በየዕለቱ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚናገሩት ሀገራት፣ ተቋማት እና የተቋማት መሪዎች በወለጋ ስለሚረግፈው ንፁሃን ትንፍሽ አይሉም ፤ ይህ ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባር ነው ብለዋል።

" በየትኛውም ስፍራ ላሉ ንፁሃን ዜጎች መጮኽ ተገቢ ነው " ነገር ግን ከሰው ሰው በመለየት ሌላ ቦታ ያለው ንፁሃን ደህንነት ሳያሳስባቸው ትኩረትም ሳይሰጡት እየመረጡ መጮሃቸው ትርጉሙ ሌላ ነው ሲሉ ተችተዋል።

" የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ነን የሚሉ ፣ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የንፁሃን ህይወት ደህንነት  ያሳስበናል የሚሉ፣ በየዕለቱ በትዊተርና ፌስቡክ ሲፅፉ የሚውሉ የተለያዩ ተቋማት ፣ የተቋማት መሪዎች እውነትም ስለ ሰብዓዊነት ተቆርቋሪ ከሆኑ ሁሉንም የሰው ልጆች በእኩል ሊመለከቱ እና ትኩረት ሊሰጡ ይገባል " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚው ስራው መሆኑን በመገንዘብ በየዕለቱ ስጋት አለብኝ / በሰላም እጦት ተሰቃየሁ እያለ ለሚጮኸው ህዝብ ህይወቱን ለመታደግ ሙሉ አቅሙን ሰጥቶ መስራት አለበት " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MadingoAfework

የተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ይፈፀማል።

ስርዓተ ቀብሩ 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ነው የተነገረው።

የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ሲሆን የኮሚቴው ቃል አቀባይ ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን " የቀብር ሥነ ስርዓቱ ሐሙስ ዕለት በቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል። ከቀብር ሥነ ስርዓቱ አስቀድሞም የሽኝት ፕሮግራም ይካሄዳል " ብሏል።

ይህን በተመለከተ ዝርዝሩን ኮሚቴው በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ተናግሯል።

#Update : ነገ በድምፃዊ ማዲንጎ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በወዳጅነት ፓርክ ከ6 ሰዓት ጀምሮ ስንብት ይካሄዳል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸምም ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል። ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ…
በጋምቤላ_ከተማ_በክልሉ_የጸጥታ_ኃይሎች፣_በኦነግ_ሸኔ_እና_የጋነግ_ታጣቂዎች_የተፈጸሙ_የሰብአዊ_መብቶች.pdf
235.3 KB
#ሪፖርት

ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል፣ ጋምቤላ ከተማ ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) በጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) መካከል የተደረገው ውጊያን ተከትሎ ከሰኔ 7 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ/ም በክልሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ታጣቂ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ የንብረት ጉዳት እና ዘረፋዎችን በተመለከተ ነው።

ከሰኔ 20 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ምርመራ ያደረገው ኢሰመኮ ዛሬ ይፋ ያደረገው ባለ 13 ገጽ ሪፖርት ነው።

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጋምቤላ_ከተማ_በክልሉ_የጸጥታ_ኃይሎች፣_በኦነግ_ሸኔ_እና_የጋነግ_ታጣቂዎች_የተፈጸሙ_የሰብአዊ_መብቶች.pdf
ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦

" ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በኋላ እንዲሁም ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋናነት በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች " የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሣሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሣሪያ አውጡ " በሚል ምክንያት ሴቶችና የአእምሮ ሕመምተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሲቪል ሰዎች በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን፣ ቢያንስ 25 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም በበርካታ ሰዎች ላይ የመደብደብና የማሰቃየት ተግባር መፈጸሙን ኮሚሽኑ (ኢሰመኮ) አረጋግጧል።

በተጨማሪም በኦነግ ሸኔ፣ በጋነግ፣ በክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሻዎች እና ተባባሪ ወጣቶች በበርካታ ሰዎች ላይ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ ተፈጽሟል።

ውጊያው በተካሄደበት በሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የኦነግ ሸኔ እና ጋነግ ታጣቂዎችም በተኩስ ልውውጡ ወቅት “ተኩሳችሁብናል” በሚል ምክንያት እና በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ ያገኟቸውን ቢያንስ 7 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል፤ እንዲሁም በሲቪል ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት አድርስዋል፣ በበርካታ ሲቪል ሰዎችም ላይ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት አድርሰዋል፡፡ በተጨማሪም በተኩስ ልውውጥ ወቅት በየትኛው አካል እንደተገደሉ ያልታወቀ 6 ሰዎች ሞተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከነዋሪዎች እና ከዓይን እማኞች በሰበሰበው መረጃ እና በሌሎች ማስረጃዎች በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሲቪል ሰዎች አስክሬን በክልሉ ልዩ ኃይሎች እና መደበኛ ፖሊሶች በጭነት መኪና ተሰብስቦ ወዳልታወቀ ቦታ እንደተወሰደና በጅምላ እንዲቀበሩ የተደረገ መሆኑን፤ እንዲሁም አስክሬን እንዲሰጣቸው ጥያቄ ያቀረቡ የሟች ቤተሰቦች መከልከላቸውን አረጋግጧል።"

ሙሉ ሪፖርተር 👉 ይጫኑ

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ምን አጋጠመው ?

ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት እክል አጋጥሞት እንደነበር አስታወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም በአንደኛው ዋና ጣቢያው (core site) ላይ ባጋጠመው የውስጥ የኃይል አቅርቦት ቴክኒካል ችግር ምክንያት በከፊል ደንበኞቹ ላይ የአገልግሎት መቆራረጥ ችግር አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።

ለተፈጠረው ችግር #ይቅርታ የጠየቀው ኢትዮ ቴሌኮም ችግሩ የተፈታ መሆኑን አሳውቋል።

ዛሬ በከሰዓት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የቴሌኮም አገልግሎት የሚያገኙ የድርጅቱ የተለያዩ ደንበኞች ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ አለመስራት፣ ስልክ ለመደወል አለመቻል ፣ SMS ለመላክ አለመቻልን ጨምሮ ሙሉ የአገልግሎት እክል አጋጥሟቸው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ለመረዳት ችሏል።

@tikvahethiopia