TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰሜን አሜሪካ ደርሰዋል ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓመተ ምሕረት በወሰነው መሠረት ለሕክምና ሐምሌ 18 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ሰሜን አሜሪካን የተጓዙት ብፁዕ ወቅዱስነታቸው በትናንትናው ዕለት…
#Update
ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።
በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

" የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋል " - አቶ መሐመድ እድሪስ
የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ፍቅር እና ሰላምን መስበክ እንዲሁም የአብሮነት እሴቶችን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ገለፁ።
ይህን ያሉት ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
አቶ መሐመድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃኑ ትውልድን በሃይማኖት መርሆዎች በመቅረጽ ለሰላም ግንባታ ሚናቸው የላቀ ነው ያሉ ሲሆን የችግሮች መንስኤ ከመሆን መቆጠብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በአንዳንድ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የሌሎችን ሃይማኖት አለማክበርና ማንቋሸሽ ይስተዋላል፤ ይህ አካሄድ ሊታረም ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በዘላቂነት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሃይማኖት ሚዲያ ካውንስልን ለማቋቋም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መደረሱን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ በበኩላቸው፣ በአገሪቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተሸረሸሩ የመጡ እሴቶች መበራከትና በየቦታው የሚፈጠሩ ችግሮች የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን የቤት ስራዎቻቸውን ላለመስራታቸው ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
" በርካታ አማኞች ያሉባት አገሪቱ የሚገዳደል እና መንገድ የሚዘጋ ትውልድ ተበራክቶባታል " ያሉ ሲሆን መገናኛ ብዙሃኑ ከመነቃቀፍ ይልቅ መደጋጋፍን እኛ እና እነሱ ከሚል የጥላቻ ትርክት በላይ አብሮነትን መስበክ አለባቸው ብለዋል።
ተገቢ ባልሆነ አካሄድ ውስጥ እየተጓዙ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ሰላምን እንዲሰብኩ እንመክራለን ያሉ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን በሕግ የሚጠየቁበት ሁኔታ መኖሩን አስገዝበዋል። #ኢብኮ

" ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች " - ዶ/ር ሁሴን አደም የህወሓት ኃይሎች በአፋር ያሎ በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸውም ውስጥ ወደ ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል መጥተው ህክምና የተከታተሉ…
" የህፃናት ህይወት ተቀጥፏል " - UNICEF
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ፤" አሁንም በድጋሚ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት የህፃናትን ህይወት ቀጥፏል " ብሏል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነ #የአፋር_ክልል መንደር የተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ህፃናትን ገድሏል ፤ በርካቶችንም ቁስለኛ አድርጓል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል።
UNICEF በኢትዮጵያ ላሉ ህፃናትና ለወደፊት ህይወታቸው ሲባል ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉም ወገኖች እንዲስማሙ ተማፅኗል።
UNICEF በመግለጫው ላይ ጥቃት የደረሰበትን የአፋር ክልል መንደር በግልፅ ባይሳውቅም ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች በአፋር " ያሎ " በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።
በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ዱብቲ ሆስፒታሉ እንደገቡና ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ መገለፁ ይታወሳል።

#ኮምቦልቻ
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በከተማው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 35 ህገ ወጥ ሞተር ብስክሌቶች በቁጥጥር ስር ዋሉን ገልጿል።
ሞተር ብስክሌቶቹ ከወልድያ ፣ መርሳ እና ሀይቅ የመጡ እንደሆነና ከኮምቦልቻ ከተማም ያሉ ሞተሮች እንደሚገኙበት ተመላክቷል።
ሞተሮቹ ሠሌዳ እና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ የሌላቸው ናቸው ተብሏል።
እነዚህ ሞተሮች እስከ 50,000 ብር የሚጠጋ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የተገለፀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሞተሮች በህገ ወጥ ተግባራት የመሠማራት ዝንባሌ ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ተላልፏል።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በፊትም 400 ህገ ወጥ ባጃጆች ወደ መጡበት ተመልሰዋል ብሏል።

"...አሁን ላይ እንደሀገር ባጋጠመው ችግርና በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የዘንድሮው የሩፋኤል በዓል አይከበርም" - የደጀን ወረዳ ፖሊስ አሁን ላይ ካለው ሀገራዊ ችግር እና የፀጥታ ስጋት አኳያ ከአራት ቀናት በኃላ (ጷግሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም) በደጀን ወረዳ አባይ ድልድይ ላይ የሚከበረው የሩፋኤል በዓል አይከበርም። የደጀን ወረዳ ፓሊስ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ አባይ በርሀ ውስጥ…
⚠️ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት ⚠️
የሩፋኤል በዓል በየአመቱ " ጳጉሜ 3 " ቀን አባይ ወንዝ ላይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ህዝቦች በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል።
ነገር ግን የዘንድሮው (2014 ዓ/ም) ዓመታዊ የሩፋኤል በዓል በተፈጠረው ክልላዊ እና ሀገራዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት #እንደማይከበር የደጀን ከተማ ፖሊስ ባስተላለፈው የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት አሳውቋል።
ይህን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት ጥሶ የሚገኝ አካል ላይ በሚፈጠረዉ ችግር ፖሊስ ሀላፊነቱን እንደማይወስድና የህግ ተጠያቂነት እንደሚኖረውም በጥብቅ አሳስቧል።
ባለፈው ዓመትም (2013 ዓ/ም) በተመሳሳይ እንደ ሀገር ባጋጠመ ችግር እና በአካባቢው ላይ በነበረ የፀጥታ ስጋት ምክንያት በዓሉ እንዳይከበር ተወስኖ ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።

#SafaricomEthiopia #DireDawa ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ ፣ ለአየር ሰዓት እና ልዩ ልዩ የደንበኞች አገልግሎት ከ3ቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከላት (ከዚራ፣ መስቀለኛ፣ ኮኔል ከሚገኙት) በተጨማሪ ብራንድድ በሆኑ በሁሉም የከተማው ሱቆች #ሲም_ካርድ እና #አየር_ሰዓት ማግኘት እንደሚቻል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል። #SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa…
#SafaricomEthiopia
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ6 ሳምንታት ውስጥ በአዲስ አበባ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚጀምር የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር አስነብቧል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀናት በፊት በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ መጀመሩ ይታወሳል። አገልግሎቱ በራሱ መሰረተ ልማት የተጀመረ መሆኑ ተጠቁሟል።
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሲካሄድ የነበረው የመሠረተ ልማት ስምምነት በቶሎ ባለማጠናቀቁ አገልገሎቱን ለማስጀመር ጊዜ መውሰዱን ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትርፍ ለማግኘት ቢያንስ 5 ዓመታት ሊፈጅበት እንደሚችል አስታውቋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ፣ በሲሚንቶና በሌሎች ግብዓች ላይ ዋጋ መጨመሩ ኩባንያው በቶሎ ትርፍ ለማግኘት እንቅፋት ሊሆንበት እንደሚችል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ባልቻ ሬባ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሠጡት ቃል ፤ ኩባንያው እስከ ሚያዚያ 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን 25 በመቶ የኅብረተሰብ ክፍል የሚሸፍን አገልግሎት እንዲያቀርብ ውል ገብቷል ብለዋል።
በዚሁ በተጠቀሰው ጊዜ የሚጠበቅበትን ካላሟላ ኦዲት ተደርጎ በገባው ውል መሠረት ቅጣት ይጣልበታል እንደሚጣልበት፤ ይሁን አንጂ የቴሌኮም ኩባንያው አሁን በተሳካ ሁኔታ ሥራውን እያከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ ኩባንያቸው የዋጋ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የቴሌኮም አገልግሎት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-08-31

የኢፌዴሪ መንግስት ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር (አማራ ክልል) አካባቢ ወረራ ከፍቷል ሲል አሳወቀ።
ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ ያወጣው የኢፌዴሪ መንግስት ፤ " ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም " ብሏል።
በዚህ ምክንያት ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ነው ብሏል።
ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱን የገለፀው የኢፌዴሪ መንግስት ወራራውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል ብሏል።
ዛሬም ድረስ ለሰላም አማራጮች የተዘረጉ እጆች አልታጠፉም ያለው የኢፌዴሪ መንግስት ይህ ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን ያድርግ ሲል አሳስቧል።
" ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሓት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ ያውጣ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
(የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#ብርሃን_ባንክ
ካሉበት ሆነው ገንዘብ ማስተላለፍ እና መሰል ጉዳይዎትን በምቾት ይከውኑ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc

#UnitedNation
የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አንስተው ነበር።
ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ?
- በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ግጭት መቀጠሉን እና አሁን ላይ ያለድ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ገልፀዋል።
- የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች ማለትም በያሎ እና ጉሊና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለ ውጊያ ሳቢያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
- በአፋር እና አማራ አዋሳኝ ቦታ ጭፈራ ወረዳ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሚገልፅ ሪፖርት መኖሩን አመልክተዋል።
- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከሚገኘው የጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ተጠልለው የነበሩ 30 ሺህ ሰዎችም ለሁለተኛ ጊዜ ተፈናቅለዋል።
- ዳግም ባገረሸው ግጭት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ የሰብዓዊ መብት ፍላጎትን ይጨምራል ብለዋል።
(ተጨማሪ ከላይ ተይይዟል)

#UnitedNation የተመድ ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትላንት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተው የነበረ ሲሆን በመግለጫው ላይ የሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይን አንስተው ነበር። ስቴፋን ዱጃሪች ምን አሉ ? - በሰሜን ኢትዮጵያ አሁንም ግጭት መቀጠሉን እና አሁን ላይ ያለድ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት እንደሆነ ገልፀዋል። - የአፋር ክልል ከትግራይ ጋር በሚዋሰንባቸው ቦታዎች ማለትም…
የጃራ ተፈናቃዮች ጉዳይ!
የጃራ ተፈናቃዮች ትናንት ወደ አፋር ጭፍራ ቢሄዱም አትገቡም ተብለው ዛሬ ወደነበሩበት መመለሳቸውን ተናግረዋል።
በጃራ በመጠለያ ጣቢያ የሴቶችና ህፃናት አስተባባሪ ወ/ሮ ዘነበወርቅ ጣውዬ ፥
" በካምፑ ውስጥ ከተለያዩ የራያ፣ ኮረም ቆቦና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያው የነበሩ ከ30 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ባገረሸው ግጭት በስጋት ሳቢያ ወደ ጭፍራ ተጉዘው አዳራቸውን በዚያው አድርገዋል።
ተፈናቃዮቹ ከማንነት ጋር በተያያዘ ከ 'ህወሓት' ጥቃት ይደርስብናል በሚልና ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የውሃና የምግብ እጥረት በመከሰቱ ጭምር የሸሹ ናቸው። "
ከተፈናቃዮች መካከል አቶ ዝናቡ መሰለ ፦
" ሁሉም ተፈናቃይ ለሶስት ቀናት በመጠለያ ጣቢየው ቢቆይም፣ የምግብና የውሀ እጥረት በመከሰቱ እንደገና ለመፈናቀል ተገደናል።
የአማራ ክልልን አቋርጠን አፋር ክልል ብንደርስም ጠብቁ ተብለን እዛው ሜዳ ላይ አድረን ወደመጣቹበት ተመለሱ ተለናል።
በዚህም ምክንያት ዛሬ እየተመለስን ቢሆንም ብዙዎች አቅመደካሞች ህፃናትና እናቶች በየበረሀው ቀርተዋል።
አካባቢው እጅግ ሙቀት በመሆኑ ህፃናትና የሚያጠቡ እናቶች ለከፍተኛ የውሀ ጥምና ርሀብ ተጋልጠዋል። "
ትናንት ከጃራ ጭፍራ ዛሬ እንደገና ከጭፍራ ጃራ ተጉዘው ወደ መጠለያ ጣቢያው ከደረሱት መካከል አንዳንዶቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችና የማብሰያ እቃዎች በመዘረፋቸው፣ የውሀና የምግብ አቅርቦት ባለመኖሩ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዓለሙ ይመር ፦
" መጠለያ ጣቢያውን ሁሉም ተፈናቃዮች አለቀቁም። የሄዱትም ቢሆኑ እተመለሱ ነው ብለዋል፡፡ የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ በተመለከተ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቦታው ይላካል " #ዶቼቨለ

#OFC
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በላከው መግለጫ " በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ግጭት በመባባሱ እጅግ አዝናለሁ " ብሏል።
ፓርቲድ የነዚህ ግጭቶች መባባስ እና መቀጠል ህዝቡን ዳግም ለከፋ ሞት እና መፈናቀል የሚዳርግ ከመሆኑ ባሻገር ለንብረትና መሰረተ ልማቶች ውድመት የተዳረጉ አካባቢዎችን ለበለጠ አለመረጋጋት ይዳርጋል ብሏል።
ኦፌኮ ጦርነቶቹ ከመቀሰቀሳቸው ቀድም ብሎ ጦርነት ለኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል እንደገለፅኩት አሁን ዳግም በአፅንዖት እገልፃለሁ ብሏል።
አሁን ያሉት ችግሮች በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት በእውነተኛ እና ሁሉን አቀፍ ድርድር ብቻ ነው ሲል እምነቱን ገልጿል።
በሁሉም ወገን ያሉ ተፋላሚ ሀይሎች ግጭቱን በማብረድ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲሹ ጠይቋል።
ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ሁሉ ተጨማሪ ሞት እና የዜጎችን መከራ ለማሰቀረት በንቃት እና በተቀናጀ መልኩ ይረባረብ ሲልም ጥሪ አሰምቷል።
ኦፌኮ በኦሮሚያ እየተስፋፋ ነው ያለውን ግጭት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመፍታት ቀርቶ እውቅና ሊሰጠው አልቻለም ያለ ሲሆን ይህ እንደሚያሳስበው ገልጿል።
በክልሉ በተለይም በግጭትና በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲልም ገልጿል።
የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እየተባባሰ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በድርድር እንዲፈታ ሁኔታዎችንን እንዲያመቻች ጠይቋል።
ፓርቲው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ገዥው ፓርቲ፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች እና አክቲቪስቶች ግጭቱን ከሚያባብሱ ንግግሮች እንዲታቀቡ እና ችግሩን ለማርገብና ለመፍታት በአንድ ድምፅ እንዲተባበሩ ተማጽኗል።