TIKVAH-ETHIOPIA
"...አሁን ላይ እንደሀገር ባጋጠመው ችግርና በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የዘንድሮው የሩፋኤል በዓል አይከበርም" - የደጀን ወረዳ ፖሊስ አሁን ላይ ካለው ሀገራዊ ችግር እና የፀጥታ ስጋት አኳያ ከአራት ቀናት በኃላ (ጷግሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም) በደጀን ወረዳ አባይ ድልድይ ላይ የሚከበረው የሩፋኤል በዓል አይከበርም። የደጀን ወረዳ ፓሊስ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ አባይ በርሀ ውስጥ…
⚠️ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት ⚠️
የሩፋኤል በዓል በየአመቱ " ጳጉሜ 3 " ቀን አባይ ወንዝ ላይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ህዝቦች በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል።
ነገር ግን የዘንድሮው (2014 ዓ/ም) ዓመታዊ የሩፋኤል በዓል በተፈጠረው ክልላዊ እና ሀገራዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት #እንደማይከበር የደጀን ከተማ ፖሊስ ባስተላለፈው የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት አሳውቋል።
ይህን የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክት ጥሶ የሚገኝ አካል ላይ በሚፈጠረዉ ችግር ፖሊስ ሀላፊነቱን እንደማይወስድና የህግ ተጠያቂነት እንደሚኖረውም በጥብቅ አሳስቧል።
ባለፈው ዓመትም (2013 ዓ/ም) በተመሳሳይ እንደ ሀገር ባጋጠመ ችግር እና በአካባቢው ላይ በነበረ የፀጥታ ስጋት ምክንያት በዓሉ እንዳይከበር ተወስኖ ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።
@tikvahethiopia