TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ : እርቀ ሰላም !

በአዊ እና በመተከል ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች በሚኖሩ ህዝቦች መካከል የሚፈጠሩ የግጭት መንስኤዎችን  በዘላቂነት ለማስወገድ ዛሬ የእርቀ ሰላም ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በሁለቱ ዞኖች አጎራባች በሆኑ ፓዊና ጃዊ ወረዳዎች በሚኖሩ ህዝቦች የሚፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለማስወገድ ተስፋ የተጣለበት ይኸው እርቀ ሰላም በጃዊ ወረዳ ወርቅ ሀገር ቀበሌ ነው የተካሄደው።

Photo Credit : መተከል ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ATTENTION

ደባርቅ !

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ከወቅታዊ ፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አሳውቋል።

የፀጥታ ምክር ቤቱ በከተማው ውስጥ የሚገኘው የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግባት እንደማይችል ከልክሏል።

የባጃጅ ተሽከርካሪችም ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ይህን በሚያደርጉ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስቧል።

ሌላው፤ የከተማው ባለሆቴሎች እና ባለአልጋ ቤቶች ማንነቱ ያልታወቀ አንጋች በድርጅታቸው ሲጋጥምቻቸው ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ምክር ቤቱ አሳስቧል።

የቤት አከራይዎች ቤታቸውን ሲያከራዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የሚያከራቱትን ግለሰብ ማንነት ለይታተው እንሲያውቁ በመረጃ ፎርም ሞልተው ለፀጥታ ጽ/ቤት እንዲያሳውቁ ብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ መላው የከተማው ማህበረሰብ በአደረጃጀቶች አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላፍሏል።

የተላለፉትን የውሳኔ ሀሳቦች የሚጥስ ማንኛውም አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ደባርቅ ! የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ከወቅታዊ ፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን አሳውቋል። የፀጥታ ምክር ቤቱ በከተማው ውስጥ የሚገኘው የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግባት እንደማይችል ከልክሏል። የባጃጅ ተሽከርካሪችም ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ይህን በሚያደርጉ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ…
#ATTENTION

ወልድያ !

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል።

በዚህም ፦

• ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ #ተከልክሏል

• ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ወልድያ ! የወልድያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን አካባቢ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከነሐሴ 22 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ አስቀምጧል። በዚህም ፦ • ከተመደበው የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ሰው መንቀሳቀስ #ተከልክሏል። • ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጠው ተሽከርካሪ ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪ…
#ATTENTION

ደሴ !

ከደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማው ሰላም እና ደህንነት ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦

- የምግብ ቤቶች ፣ የምሽት መጠጥ ቤቶች/ግሮሰሪዎች/ ከምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በማንኛውም ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ተከልክሏል።

- ማንኛውም ምርት ላይ የዋጋ ጭማሬ የሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

- በመፈናቀል ሆነ በሌላ ማንኛውም ምክንያት ወደ ደሴ ከተማ የገቡ ተፈናቃዮች የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል የፀጥታ ኃይሎች ለጋራ ደህንነት ለሚተገብሯቸው የፍተሻና የቅድመ-ጥንቃቄ ስራዎች ተባባሪ የመሆን ግዴታ አለባቸው ተብሏል።

- አልጋ ቤት፣ የመኖሪያ ቤት ወይም መደብ ቤት አከራዮች የየትኛውንም ተከራይ ማንነትን የሚገልፅ መረጃ ለፀጥታ ተቋማት የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

- ወደ ደሴ በማንኛውም ምክንያት የገቡ እንግዶች ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- ከተፈቀደላቸው የከተማው የፀጥታ ሃይሎች ውጭ ጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ ተከልክሏል።

- ከዛሬ ጀምሮ የትኛውም የከተማችን ነዋሪ ከምሽቱ 2:00 /ሁለት/ ሰዓት ጀምሮ በተናጠልም ሆነ በጋራ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።

- በከተማ ደረጃ እውቅና ያላቸው የተሰጣቸው የታክሲ አሽከርካሪዎች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ብቻ ህዝቡን እንዲያገለግሉ ተወስኗል።

- በሁሉም አካባቢወች የሚገኙ ባጃጆች እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።

- የDSTV አገልግሎት መስጫዎች ፣ በጋራ ተሰብሰቦ ጫት የሚቃምባቸው መቃሚያ ቤቶች ፣ የሽሻ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ በይፋም ሆነ በስውር አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለ ... ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ ሌሎች የሰራቸው ስራዎች ፦ 👉 የተሳካ አገልግሎት ለማቀረብ አንዲሁም የሙያ እና የክህሎት ሽግግርን ለማጠናከር ብቃት ያለው የአመራሮች ሰብስቦ አዋቅሯል። 👉 የሰው ኃብቱን ወደ 500 ያሳደገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 320ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በቀጣይም ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ሠራተኞች እንዲኖሩት ለማድረግ እየሰራ ነው። 👉
#ሳፋሪኮም

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል።

ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው።

በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን ደንበኞች በዐ7 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት ይችላሉ፡፡

ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሁፍ መልዕክቶች ጥቅል ያገኛሉ።

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎት መጠቀም መቀጠል ይችላሉ፡፡

በከዚራ፣ መስቀለኛ እና ኮርኔል ያሉ 3 የሳፋሪኮም ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት እንደሆኑ ተገልጿል።

በድሬዳዋ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳፋሪኮም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው። በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች…
#DireDawa #SafaricomEthiopia

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች አገልግሎት በ " 700 " ላይ በመደወል ማግኝት ይቻላል።

ዛሬ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ ጀምሯል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቶች በጥሪ ማዕከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም ፦
- በአማርኛ
- በአፋን ኦሮሞ
- በሱማሊኛ
- በትግርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ የማግኘት አማራጭ የሚኖራቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን " 700 "  ላይ በመደወል ማናገር ይችላሉ።

* ማስታወሻ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት ናቸው። የሽያጭ ማዕከሎቹ የሚገኙት ፦
- #ከዚራ
- #መስቀለኛ
- #ኮርኔል ነው።

#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ወልድያ

ወልድያ ከተማ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እንደቀጠለ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተለያዩ ሚዲያዎች እና የፖለቲካ ተንታኝ ነን የሚሉ የውጭ አካላት በማህበራዊ ሚዲያው ወልድያን በተመለከተ ሀሰተኛ ዜና እያሰራጩ ይገኛሉ።

" ከወልድያ አመራሩ ወጥቷል፣ ወልድያንም ህወሓት ይዟል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ሁሉም ሀሰት መሆኑና ህዝቡን ለማሸበር የሚሰራ ስራ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ግጭት በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ አይነት በሀሰት ህዝብን የማሸበር ስራ ሲሰራ፣ ህዝብን ለማስደንገጥ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉና በዚህ ሳቢያ ብዙ መመሰቃቀል ሲፈጠር እንደነበር አይዘነጋም።

እስካሁን ድረስ በወልድያና በቀጠናው ባለው ሁኔታ ከወልድያ ከተማም ይሁን ከጅቡቲ ወደብ የሚነሱ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን ከተለመደው የዕለት ተዕለት ጉዟቸው ያስተጓጎላቸው ሁኔታ እንዳልተከሰተ ከወልድያ ከተማ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ደግሞ ፤ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚማሩ ተማሪዎች ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው የወጡ፤ የትራንስፖርት አጥተውም በእግር የተጓዙ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል።

አንዳንድ መልዕክት የላኩ የግቢው ተማሪዎች ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ " ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ እንዲደረግ ፤ አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ እነሱም ቤተሰብም ጭምር ጭንቀት ላይ በመሆኑና በዚህ ሁኔታ ትምህርትን በንቃት መከታተል ስለሚያስቸግር ተቋማቸው መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል።

በተማሪዎቹ ስጋት ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።

@tikvahethiopia
" በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት የአካልጉዳተኞችን መብቶች ያከብሩ " - የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር

ወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ነዋሪ የሆነው እያሱ ዴላባሌ የተባለ አካልጉዳተኛ ግለሰብ፣ በስራ ቅጥር ወቅት የደረሰበት የአንድ አመት ውጣውረድ በሚዲያ ለሕዝብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ መረጃውን ለሚዲያ ተቋማት ያደረሰው ግለሰብ ከፍርድቤት ትእዛዝ ውጭ ለእስር መዳረጉን እና በሗላም በፍርድ ቤት ውሳኔ በዋስ መፈታቱን የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማጣራት ችሏል፡፡

ማህበሩ በአቶ እያሱ ላይ የተፈጸመውን የመብት ጥሰት አስመልክቶ ለሚዲያ ተቋማት መረጃ በሰጠው ግለሰብ ላይ የተፈጸመው የመብት ጥሰትም ሆነ ያላግባብ በእያሱ ላይ የተፈጸመው የተንዛዛ የስራ ቅጥር ሂደት፣ ህገወጥ እና ተቀባይነት የሌላቸው በበቂ ሁኔታ ሊወገዙ የሚገባቸው የመብት ጥሰቶች መሖናቸውን እገነዘባለሁ ብሏል።

በዚህ ተጨባጭ ጉዳይም ሀሳብን በነጻነት  የመግለጽ፣ ከህገወጥ እስር የመጠበቅ፣ በአርባስምንት ሰአት ውስጥ ፍርድቤት የመቅረብ መብት እንዲሁም ሌሎች ሰባዊ መብቶች የተጣሱ መሆናቸውን፤ በሌላ በኩልም የእያሱ ዴላባሌ  የስራ ቅጥር መብት   የተጣሰ  መሆኑን ማህበሩ ማረጋገጡን ገልጿል

በመሆኑም የወላይታ ዞን አስተዳደር በህገወጥ እስር እንዲፈጸም ያደረጉ ሰዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ , የአቶ  እያሱ ዴሌባሌ የስራ ቅጥር ሂደት በአስቸኳይ ተጠናቆ የስራ ቅጥር  እንዲፈጸምለት እንዲደረግ, የአቶ እያሱ ዴላባሌን ጉዳይ እንደመነሻ በመውሰድ የወላይታ ዞንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት የአካልጉዳተኛ የስራ ቅጥር አመልካቾችን እና ሰራተኞችን መብቶች እንዲያስከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Haile_Hotels_and_Resorts

ሃይሌ ሪዞርት በአዲስ አበባ ያስገነባውን ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በቅርቡ ያስመርቃል።

ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ያስገነባውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በቅርቡ እንደሚያስመርቅ ተገልጿል።

ባለ ዘጠኝ ወለል ዘመናዊ ሕንጻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንደሆነ የተነገረለት የሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴል 8ኛ ሆቴል "ሃይሌ ግራንድ ሆቴል" ተብሎ እንደተሰየመ ተሰምቷል፡፡

ሆቴሉ 160 ምቹ የመኝታ ክፍሎች ፤ ስታንዳርድ እና ፕሬዝደንሺያል ተብለው የተለዩ ልዩ የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች ፤ የመዋኛ ገንዳ ፤ ጂምናዝየም ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ የቤት ውስጥ እግር ኳስ ፤የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች እና የምሽት ክበብ አካቶ የያዘ ነው ፡፡

በተጨማሪም 300 መኪኖች የሚይዝ ፓርኪንግ በሕንጻው ምድር ክፍል ተገንብቶለታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሰራተኞች ቅጥር እና ስልጠና በመካሔድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በሃዋሳ አንድ ብሎ የመጀመሪያውን ሆቴል የከፈተው ሃይሌ ሪዞርት እና ሆቴሎች በቅርቡ በወላይታ ሶዶ ፤ ደ/ብርሃን እና ኮንሶ ተጨማሪ ሶስት ሆቴሎች እንደሚከፍት ታውቋል፡፡

በቀጣይ በጎርጎራ ከአንድ ቢሊየን ብር  በላይ ወጪ ልዩ የመዝናኛ ሆቴል እንደሚገነባ እና ሃይሌ ሪዞርት ዓለም አቀፍ ብራንድ በማድረግ በምስራቅ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች ሆቴሎች እና ሪዞርቶች የመገንባት እቅድ እንዳለው ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

@tikvahethiopia