TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰማያዊ ፓርቲ‼️

ሰማያዊ ፓርቲ ከኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ መስማማቱ ተገለፀ።

ሰማያዊ ፓርቲ በትላንትናው ዕለት ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ #የሽዋስ_አሰፋ ለFBC ተናግረዋል።

"ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለኢትዮጵያ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የኢህአዴግ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ አረና፣ የቀድሞው አንድነት እና ሌሎች ፓርቲዎች ተወካዮች በክብር እንግድነት መታደማቸው ተገልጿል።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤው ከሶስቱ ፓርቲዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በአላማ ከሚመሳሰሉ ፓርቲዎች ጋር ተዋህዶ ትልቅ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት መወሰኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

በቀጣይም ሰማያዊ፣ ኢዴፓ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት እና የቀድሞው አንድነት ከወረዳ ጀምሮ መዋሃድ የሚጀምሩ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የአራቱ ፓርቲዎች ጥምር አገራዊ ፓርቲም በአዲስ ስያሜ እስከ መጋቢት 30 ይፋ የሚደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ በጠቅላላ ጉባኤው ባሳለፈው ውሳኔ እና በቀጣይ ስራዎቹ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ የሚሠጥ መሆኑን አቶ የሽዋስ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርበኞች ግንቦት 7🔝

በዛሬው እለት አርበኞች ግንቦት 7 በአዊ ዞን እንጅባራ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም እና በአዊ ባህል ማዕከል አዳራሽ የተሳካ እና ደማቅ ሕዝባዊ ውይይት አድርጓል። በርካታ ሕዝብ በተገኘበት በዚሁ ስብሰባ የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕ/ር #ብርሃኑ_ነጋ ፣የሰማያዊ ፖርቲ ሊቀመንበር አቶ #የሽዋስ_አሰፋ ፣ የኢዴፓ ሊቀመንበር ዶ/ር # ጫኔ_ከበደ እና የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ #አለነህ_ማህፀንቱ ተገኝተው ከስብሰባው ታዳሚዎች የተነሳላቸውን ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን በመቀበል ስለ #ዜግነትን መሠረት ያደረገ ፖለቲካን እና # ማኅበራዊፍትህን በተመለከተ ለታዳሚው ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

Via Patriotic Ginbot 7
@tsegabwolde @tikvahethiopia