TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle #AddisAbaba

• " ክልከላው ላይ የለንበትም ፤ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች

• " ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም። ... ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

• " ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን " - የፌዴራል ፖሊስ

ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚደረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች በረራ ላይ በተለይም #ወጣት መንገደኞች እንዳይጓዙ ክልከላ ስለመኖሩ መንገደኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

ትናንት ታህሳስ 30/2015 ዓ/ም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የአየር ቲኬት ቆርጠው አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተገኙት #በርካታ_ወጣቶች ጉዟቸው መሰረዙ ተሰምቷል።

መንገደኞች እንደሚሉት ከሆነ ክልከላው ከ16 ዓመት በላይ እና ከ64 ዓመት እድሜ በታች በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ነው።

አንድ ቃሉን ለቢቢሲ የሰጠ መንገደኛ (የአዲስ አበባ ነዋሪ) ፤ " የልጆች እናት፣ የህክምና ሪፈር ያላቸው እና በእድሜ የገፉት ግን መሄድ እንደሚችሉ ነው የፌደራል ፖሊስ አባላቱ የነገሩን " ብሏል።

ይኸው መንገደኛ ፤ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚኖር ፤ መታወቂያውም የአዲስ አበባ እንደሆነ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደሄደና አስፈላጊውን መረጃ እንዳረበ ነገር ግን ሊቀበሉት እንዳልቻሉ አመልክቷል።

የአየር መንገዱ ሠራተኞች ክልከላው ከቁጥጥራቸው ውጪ እንደሆነ ነግረውናልም ብሏል።

አንድ መንገደኛ ደግሞ አዲስ አበባ የሚያስተዳድረው ተቋም መኖሩን የሚገልፅ መረጃ ካሳየ በኃላ በረራ እንደተፈቀደለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ክልከላው ከመቐለ በተጨማሪም #በሽረ ኤርፖርትም ስለመኖሩ ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ ማን ምን አለ ?

የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉ አካላት ፤ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ትግራይ ቴሌቪዥን) በሰጡት ቃል በዚህ ክልከላ እንደሌሉበት እና የክልከላው እርምጃ በፌደራል መንግስት የተወሰደ እንደሆነ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገረ መሆኑን አሳውቋል።

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም።

እንደምታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድሜና ጾታ ክልከላ የለውም። ምክንያቱም በሕግ እና በሥርዓት ነው የሚተዳደረው። እስከ ዛሬ እንዲህ አይነት ክልከላ የለንም። ወደ ድረ ገጻችን ብትገቡም ምንም አይነት ክልከላ እንደሌለ ታያላችሁ።

በተጨማሪም ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም።

ምናልባት #የአካባቢው_መመዘኛ_ወጥቶ እንደሆነ የክልሉ ባለሥልጣናትን ብትጠይቁ የሚሻል ይመስለኛል።

በእኛ በኩል ግን እስካሁን የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ከመንግሥት የተሰጠ ትዕዛዝም የለም። "

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" መረጃው የለኝም።

ተጓዦች በእድሜ ተለይተው በአውሮፕላን እንዳይጓዙ ተከልክለዋል የሚለውን መረጃ አሁን ከእናንተ ነው የምሰማው።

ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን። "

በጦርነት ምክንያት ለረጅም ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ እና ሽረ እንደስላሴ የሚደረገው የመንገደኞች በረራ በቅርቡ ዳግም መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia