TIKVAH-ETHIOPIA
* ዛሬ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሂዳል። አስቸኳይ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ነው የሚካሄደው። በዚህም የአስቸኳይ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል። ከዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብሎ ትላንት ነሐሴ 11 የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስቸኳይ ስብሰባው አጀንዳዎች…
#Update
ፌዴሬሽን ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት የስራ ጊዜ 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
ም/ቤቱ በስብሰባው ከሚወያይባቸው አጀንዳዎች መካከል በዋነኝነት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች #በጋራ_ክልል_ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ ላይ ሲሆን ጥያቄውን መርምሮ #ያፀድቃል ተብሏል።
ምክር ቤቱ በሌሎች ጉዳዮችም ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#Afar በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሚገኝ የማቆያ ካምፕ ውስጥ #ያለፈቃዳቸው ተይዘው ከነበሩት የትግራይ ተወላጆች መካከል የተወሰኑት በአውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። በሺዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ተወላጆች ከአፋሯ አብኣላ ተይዘው ወደ ሰመራ ተዘዋውረው የነበረ ሲሆን ከ8 ወራት እስር በኋላ ወደ አብኣላ እየተመሰሉ…
" ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመሩን በበጎ እቀበለዋለሁ " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጿል።
ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ የሚገኙትን አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች በተመለከተ ያካሄደውን ክትትል እና ያወጣውን ሪፖርት አስታውሰዋል።
ይህንኑ ተከትሎ በካምፖቹ የነበሩ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱ ተግባር መጀመር እና የባንክ አገልግሎት ማግኘትን ጨምሮ ሌሎች እየተደረጉ ያሉ ሰብአዊ ድጋፎችን ኮሚሽኑ በበጎ እንደሚመለከተው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በአማራ ክልል፣ ወሎ ይገኛሉ ያላቸውን የጃራ እና የጃሬ ካምፖች በተመለከተ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ፤ ከአስተዳደራዊ እና የፀጥታ አካላትም እያሰባሰበ ያለውን መረጃ የሚያካትት ሪፖርት በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ዶ/ር ዳንኤል ገልፀዋል።
ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/71528?single

#Update ፌዴሬሽን ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት የስራ ጊዜ 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ በስብሰባው ከሚወያይባቸው አጀንዳዎች መካከል በዋነኝነት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ስር ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች #በጋራ_ክልል_ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ ላይ ሲሆን ጥያቄውን መርምሮ…
#Update
12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።
ምክር ቤቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል።
ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂዱት ፦
- የወላይታ ዞን፣
- የጋሞ ዞን፣
- የጎፋ ዞን፣
- የደቡብ ኦሞ ዞን፣
- የጌዴኦ ዞን፣
- የኮንሶ ዞን፣ እንዲሁም
- የደራሼ ልዩ ወረዳ፣
- የአማሮ ልዩ ወረዳ፣
- የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣
- የኧሌ ልዩ ወረዳ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ናቸው።
ቀሪዎቹ የሀድያ ዞን ፣ ሀላባ ዞን ፣ ከምባታ ጠንባሮ ዞን፣ ጉራጌ ዞን ፣ ስልጤ ዞን እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ይቀጥላሉ ተብሏል።

#Update 12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት 12ኛ ክልል እንዲቋቋም የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል። ምክር ቤቱ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የነበሩ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ወስኗል። ሕዝበ ውሳኔ የሚያካሂዱት ፦ - የወላይታ ዞን፣…
#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል
" በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ "
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፦
- የወላይታ፣
- የጋሞ፣
- የጎፋ፣
- የደቡብ ኦሞ፣
- የጌዴኦ፣
- የኮንሶ ዞኖች እንዲሁም
- የደራሼ፣
- የአማሮ፣
- የቡርጂ፣
- የአሌ፣
- የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " ለመመስረት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጿል።
ም/ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል የሕዝብን ይሁንታ ማረጋገጥ በማስፈለጉ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ በሆነ መልኩ ገለልተኛ በሆነው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ ወስኗል።
የሕዝብ ውሳኔው ውጤት ሪፖርትም ለምክር ቤቱ እንዲቀርብ፣ እንዲሁም የሕዝብ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና የሕዝብን ሰፊ ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በአብላጫ ድምጽ ወስኗል።
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የሀድያ ፣ ሀላባ ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ የሚቀጥሉ ይሆናል ብሏል።

" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ ችግር ውስጥ ናቸው " - የሶማሌ ክልል
የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ አካባቢዎች ላይ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።
ክልሉ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
ከመኖሪያ ቀዬአቸው የተፈናቀሉት ዜጎች በአሁኑ ወቅት በሲቲ ዞን ኤረር ወረዳ አስቡሊ እና በድዌይ በሚባል አካባቢ የተሰባሰቡ ቢሆንም በክረምቱ ከባድ ዝናብ ምክንያት መንገዶች በመቆራረጣቸውና ወደ አካባቢው ተሽከርካሪ ሊገባ ባለመቻሉ ምንም አይነት የእለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረብ አልተቻለም ብሏል።
በአሁኑ ወቅት ተፈናቃዮቹ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ ያለው የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት አፋጣኝ እርዳታ ለማቅረብ ጥረትና ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
ለዚህም የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ እና ም/ርዕሰ መስተደድር ኢብራሂም ኡስማን የተካተቱበት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልኡካን ቡድን ተፈናቃዮች በሚገኙበት በሲቲ ዞን በመገኘት ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ በማስተባበር ላይ ይገኛሉ ሲል ክልሉ አሳውቋል።

" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ ችግር ውስጥ ናቸው " - የሶማሌ ክልል የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚገኙ አካባቢዎች ላይ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአስከፊ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል። ክልሉ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። ከመኖሪያ ቀዬአቸው የተፈናቀሉት ዜጎች በአሁኑ ወቅት…
" የተሰራጨው ሀሰተኛ ወሬ ነው " - የሶማሌ ክልል መንግስት
የሶማሌ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ላይ "የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው" በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል።
የክልሉ መንግስት " በትላንትናው እለት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ ተብሎ የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን " ብሏል።
በትላንትናው ዕለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደርን የሚመለከቱ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።
አንደኛው ይኸው "የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው" የሚለው ሲሆን የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው የተባለው ለስራ ጉዳይ "ቢኪ" የሚባል ቦታ በሄዱበት ወቅት ነው።
ሌላኛው ደግሞ፤ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ወደዚሁ "ቢኪ" የተባለ ስፍራ በሄዱበት ወቅት ወጣቱን ጨምሮ፤ ህብረተሰቡ በመቆጣቱ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበር፤ ድንጋይም እስከመወርወር የደረሰ ክስተት እንደተፈጠረ የሚገልፅ መረጃ ነው።
የክልሉ መንግስት፤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ላይ "የግድያ ሙከራ አልተደረገባቸውም ውሸት ነው" የሚል መግለጫ ቢሰጥም በተመሳሳይ ሰዓት ስለተሰራጨው የ "ቢኪ" ከፍተኛ ተቃውሞ በተመለከተ እንዲሁም ርዕሰ መስተዳደሩ ወደ ተባለው ስፍራ አቅንተው እንደሆነ፤ ሄደውስ ምን እንደተፈጠረ የገለፀው ነገር የለም፤ ማስተባበያም አልሰጠም።
ዘግየት ብሎ ከሲቲ ዞን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በደረሰን መልዕክት ትላንት ፕ/ት ሙስጠፌ ቢኪ ላይ ተቃውሞ ገጥሟቸው እንደነበር፤ በዚህም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት እንደነበር፤ በኃላም ሁኔታውን እንደተቆጣጠሩ፣ የግድያ ሙከራ የተባለው ግን ትክክል እንዳልሆነ ገልፀዋል።

#Skillmart_International_College_and_Kindergarten
👉Registration has started
👉More than 80 merit based scholarships
Address:
👉Addis Ababa, Megenagna, Meseret Defar Building 6th floor, 0928 000 333/111 ።
👉Bahirdar Merkato Market center 0927000222/333
👉Kindergarten Addis Ababa Kotebe 0928000999
Join us 👉
https://t.iss.one/joinchat/hnbmUYObA5hjNDI0

#Ethiopia
• ህወሓት የፌዴራል መንግስት "ጥቃት ፈፅሞብኝ ነበር "ሲል የፌዴራል መንግስት " ሀሰት ነው ከሰላም ንግግር ለመሸሽ ነው " ብሎታል።
ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሰላም ድርድር እንዲፈታና ህዝቡም እንዲርፍና ወደ ቀደመው ህይወቱ እንዲመለስ ሊያደርጉ የሚችሉ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ናቸው።
ነገር ግን ባለፉት 48 ሰዓታት ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በኃይሎቼ ላይ የፌዴራል መንግስት ጥቃት ፈፀመብኝ የሚል ክስ ማሰማቱ ጥሩ መሻሻል እየታየባቸው ያሉ ሁኔታዎችን ወደኃላ እንዳይጎት አስግቷል።
ህወሓት ፤ ከቀናት በፊት (ነሃሴ 9) የፌደራል መንግሥት ጦር (በበላይ አካላት እየታወቀ) በምዕራብ ትግራይ በኩል ደደቢት አካባቢ ባሉ ኃይሎቹ ላይ በከባድ መሳሪያ ለአንድ ሰዓት የቆየ ድብደባ አደደረሰበት ገልጿል።
በዚህም ለወራት ታውጆ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ የተኩስ አቁም አዋጅ ተጥሷል / ፈርሷል ብሏል።
ምንም እንኳን ጥቃት ቢሰነዘርም የአጸፋ ምላሽ ሆነ ወደ ግጭት ያልገባነው ከእንያንዳንዱ የሰላም ቀን የትግራይ ህዝብ ይጠቀማል ብለን ነው ሲል ገልጿል።
ህወሓት ተፈፀመብኝ ያለው ጥቃት የፌዴራል መንግስት ለሰላም ዝግጁ አለመሆኑን ማሳያነው ሲል ከሷል።
ከዚህ ክስ ጋር በተያያዘ ዛሬ የፌዴራል መንግስት ምላሽ የሰጠ ሲሆን ክሱን " ሀሰት ነው " ብሎታል።
የጠቅላይ ሚንስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ህወሓት ላይ ተኩስ ከፍቷል መባሉ ሀሰት መሆኑን ገልፀዋል።
ህወሓት ያሰማውን ክስ " ከሰላም ንግግር ለመሸሽ እንደ ምክንያት የቀረበ ነው " ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

#ETHIOPIA ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ለመፈለግ እና ችግሩን በሰላማዊ ድርድር ለመቋጨት በፌዴራሉ መንግስት የተቋቋመው " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ላይ ከተጠቀሱ #ወሳኝ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ፦ • ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የትግራይ፣ የአፋር፣ የአማራ ክልል አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ዜጎች በእለት ተእለት ኑሮዋችው ላይ…
#GoE
የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችን አስንተዋል።
ከካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ በሰላም አመራጭ ኮሚቴ በኩል ስለ ተዘጋጀው የሰላም ረቂቅ ሰነድ ነው።
በዚህም የሰላም ረቂቅ ሰነዱ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለተከሰተው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት፤ በመጪዎቹ ሳምንታት የተኩስ አቁም እንዲደረስ፣ የሰላም ውይይት እንዲሁም ሌሎች በእንጥልጥል የቀሩ ጉዳዮች ደግሞ በብሄራዊ ምክክሩ እንዲዳሰሱ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።
ሰነዱ መንግስት ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ በሚፈታበት ሁኔታ ላይ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት አመላካች ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል መላሶ ግንባታ እና መሰረታዊ ድጋፎች ላይ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
መንግስት ባለሙያ በመላክም ሆነ እዛው ያለውን የሰው ኃይል በመጠቀም በክልሉ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎት ለመመለስ ፍላጎት እንዳለውና ለዚህም ደግሞ አንዳንድ በመሬት ላይ ያሉ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡
መንግስት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በማንኛውም ጊዜና ቦታ የሰላም ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ቢልለኔ በዛሬው መግለጫቸው ከአማራ ክልል ወደ አ/አ በሚደረገው ጉዞ ተጓዦች ላይ ስለሚደርስ እንግልት ተጠይቀው መልሰዋል።
በዚህም፤ "ህወሃት በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ወረራ በፈፀመበት ወቅት የዘረፋቸውን የመንግስት ማህተሞች በመጠቀም ሀሰተኛ መታወቂያ በማሳተም ለእኩይ ተግባሩ እያዋለ በመሆኑ ይህንን ድርጊቱን ለመግታትና ተከታትሎ ለመያዝ በተወሰደ እርምጃ የተፈጠረ ነው" ብለዋል።
አሁን ላይ ግን የትራንስፖርት አገልግሎቱ ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለሱን ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ከኤፍ ቢ ሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#ፊንላንድ
ከወደ ፊንላንድ የተሰማ ...
በእድሜ ወጣት የሆኑት የ36 ዓመቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ፓርቲ ላይ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ቪድዮ ሾልኮ ከተለቀቀባቸው በኃላ ከፍተኛ ትችት እየደረሰባቸው ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ሾልኮ በወጣው ቪድዮ ከዝነኛ ፊላንዳውያን ጓደኞቻቸው ጋር ሲጨፍሩ እና ሲዘፍኑ ታይተዋል።
ከዚህም በኃላ የጠቅላይ ሚኒስትሯን ድርጊት በተለይ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ከፍተኛ ትችት አስከትሎባቸዋል።
አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትሯ " የአደንዛዥ እጽ ምረመራ ይደረግላቸው " ሲሉ ጠይቀዋል። ሌሎች ደግሞ ብዙ ሀገራዊ ጉዳይ እያለ ስለጭፈራ ማውራቱ ጊዜው አይደለም ሲሉ ተችተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ግን " አደንዛዥ እጽ አልወሰድኩም " ያሉ ሲሆን አልኮል መጠጣታቸውን እና በሙሉ ኃይላቸው በፓርቲው ላይ መጨፈራቸውን ግን ተናግረዋል።
ቪዲዮ እየተቀረጹ መሆኑን እንደሚያውቁ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሯ " ለሕዝብ ዕይታ መቅረቡ ግን ያበሳጫል " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
" ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ፓርቲ አድርጊያለሁ ሁሉም ሕጋዊ ናቸው። እኔ ወይም በአካባቢዬ አደንዛዥ እጽ በሚወሰድበት ቦታ ሆኜ አላውቅም " ሲሉም አክለዋል።
በተጨማሪ " የቤተሰብ ሕይወት አለኝ፣ የሥራ ሕይወት አለኝ፣ እንዲሁም ከጓደኞቼ ጋር የማሳለፈው ነጻ የምሆንበት ጊዜ አለኝ። በእኔ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
መሪን ከእ.አ.አ. 2019 መጨረሻ ጀምሮ ፊንላንድን እየመሩ ሲሆን አሁንም ድረስ ከፓርቲያቸው ጠንካራ ድጋፍ እንዳላቸው ቢቢሲ አስነብቧል።

ፍትሕን በገንዘብ ያልሸጣት ምስጉን ዳኛ!
በምእራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ሰዓት ላይ አንዲት ህፃንን አስገድዶ በመድፈሩ ምክንያት ተከሳሽ ተይዞ ጉዳዩ በህግ ይታያል።
በዚህን ጊዜ የተከሳሽ ወንድምና ጓደኛ መዝገቡን የሚያየውን ዳኛ በከተማው በሚገኝ ፅናት ሆቴል ይቀጥሩታል። ኃሳባቸውም ለዳኛው 10 ሺህ ብር ጉቦ በመስጠት ተከሳሽ ነጻ እንዲወጣ ማድረግ ነበር።
ዳኛውም ቀጠሮዎን አክብሮ ከቦታው ይደርሳል፥ የተከሳሹ ተባባሪዎችም ገንዘቡን አውጥተው ለዳኛው ሊሰጡት ሲሉ ዳኛዉ አስቀድሞ ለፖሊስ አሳውቆ ነበርና እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸዉ እንደሚገኝ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ያገኘነው መረጃ ያሳል።
አንዳንድ ፍትሕን በገንዘብ የሚሸጡ፣ ያስተማራቸውን ያሳደጋቸውን ማህበረሰብ እና ሀገርን በገንዘብ የሚለውጡ የፍትህ አካላት እንዳሉ ሁሉ ከላይ መረጃውን እንዳነበብነው አይነት ምስጉን የፍትህ አካላት አሉ። ማህበረሰቡን እና ሀገርን በታማኝነት የሚያገለግሉ አካላት ሊመሰገኑ ይገባል።
በእርግጥ ሁላችንም ባለበት ቦታ ኃላፊነታችንን መወጣት ፤ ታማኝነታችንን ማሳየት ፣ ለማህበረሰባችን ፣ ለሀገራችን የገባነውን ቃል ማክበር ግዴታችን እና የሚጠበቅብን ቢሆንም እንዲህ ያሉ የሚያስመሰግኑ ተግባራትን ማበረታታና ማመስገን ይገባል።
@tikvahethmagazine

ፎቶ ፦ የደብረ ታቦር በዓል በደብረታቦር ከተማ !
በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን የሚከበረው የደብረታቦር (የቡሄ ) በዓል በታላቁ ደብር ደብረታቦር እየሱስ ቤተክርስቲያን ባህላዊ እና ሐይማኖታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ ተከብሯል።
Credit : ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine