TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TikvahFamilyMekelle

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ ያገኘናቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ አባላት ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ ለዚህ ቀን በመብቃታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልፀውልናል።

እጅግ በጣም ፈታኝ እና አስቸጋሪ በነበሩ ወቅቶች የመቐለ ነዋሪዎች አብሯቸው ስለነበሩ ፣ አይዞአችሁ እኛ አለንላችሁ ስላሏቸው ፣ ለእራሳቸው እየተቸገሩ ከሚበሉት ላይ ቀንሰው ስላካፈሏቸው ፣ ከሚጠጡት ቀንሰው ስላጠጧቸው፣ ፍቅር ስላስተናገዷቸው ፣ እንደልጆቹ ስለተንከባከባቸው ምስጋና እንድናደርስላቸው ጠይቀውናል።

እኛም ምንም እንኳን የመቐለ ነዋሪዎች በኢንተርኔት መቋረጥ ይህንን መልዕክት ባያዩትም ምስጋናውን አድርሰናል።

#Congratulations

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamilyMekelle

ዛሬ ከሰዓት የባንክ አገልግሎት መጀመሩን የመቐለ ቲክቫህ አባላቶቻችን አሳውቀዋል።

የንግድ ባንክ ቅርጫፎች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

እጅግ በርካታ ሰዎችም ገንዘብ ለማውጣት ረጅም ሰልፍ ተሰልፈው ነበር።

በተለይ በዋናው የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የነበረው ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የመቐለ ቲክቫህ አባላት በስልክ ገልፀዋል።

ከኢፕድ ድረገፅ እንደተመለከትነው ደግሞ የመቐለ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ የግል ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ትዕዛዝ መተላለፉን አሳውቀዋል።

የቲክቫህ አባላት በከተማቸው የባንክ አገልግሎት አለመኖር ነዋሪውን ክፉኛ ችግር ላይ ጥሎት እንደነበር ነግረውናል። አሁን ባንክ መከፈቱ መልካም ቢሆንም ጫናው እንዲቃለል ሁሉም ባንኮች በፍጥነት ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ በከተማው ያለው የዋጋ ንረት ለነዋሪዎች ከፍተኛ ፈተና ሆኗል፤ይህም በፍጥነት እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

በፀጥታ በኩል አሁንም የሚታዩ ዘረፋዎች መኖራቸውን በመጠቆም ለህዝቡ በሰላም መንቀሳቀስ የደህንነት ስራው እንዲጠናከር አደራ ብለዋል።

በሌላ በኩል፦

የመቐለ ቲክቫህ አባላት ኔትዎክ በሌለባቸው የትግራይ ከተሞች የዘመድ አዝማዶቻቸውን ደህንነት ለማወቅ እንደተቸገሩ ገልፀዋል።

አንዳንዶችም በሰዎች ደብዳቤ በመላክ የእናት እና አባቶቻቸውን ደህንነት ለማወቅ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ነግረውናል።

ኔትዎርክ በሌለባቸው አካባቢዎች ኔትዎርክ ሲከፈት የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በዝርዝር ለቲክቫህ አባላት እንደሚያጋሩ አሳውቀዋል።

በትግራይ የሚኖሩ እና በተለያዩ የሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ሄደው የሚማሩ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ MoSE ለተማሪዎቹ ሊደረግ ስለታሰበው ነገር በሚዲያ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
" የህዝብን ደህንነት መጠበቅ የመንግስት ዋነኛ ተግባር መሆኑ መዘንጋት የለበትም " - የትግራይ ዩኒቨርስቲዎች ምሁራን ማህበር

የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሁራን ማህበር ከቅርብ ግዚያት ወዲህ በክልሉ እየታዩ ያሉ የፀጥታ ስጋቶችና ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። 

ማህበሩ በመግለጫው እንዳለው ባለፉት ወራት በክልሉ የከተማና የገጠር አከባቢዎች ወንጀሎች እየተበራከቱ ሰዎች እየተገደሉ ፣ አካላቸው እየጎደለ ፣ እየታፈኑ  ፣ ንብረታቸው እየተዘረፉ ነው ፤ ለምሳሌ በኣሸንዳ ሳምንት ያጋጠሙ ሁለት ከፍተኛ ወንጀሎች ለበርካቶች የሞትን የመቁሰል አደጋ ምክንያት ሆነዋል ሲል ገልጿል።

በተለይም በእህታችን ዘውዱ ሃፍቱ ላይ ያጋጠመ ወንጀል የተለየ እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ የግድያ ተግባር ነው ያለው የማህበሩ መግለጫ " በዚህም በዓሉን ለማክበር ከሌላ አከባቢ ለመጣና ለነዋሪው ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል " ብለዋል። 

የምሁራን ማህበሩ መግለጫ ወንጀሎች ፣ የሰላምና የድህንነት ስጋቶች እየቀነሱ ሳይሆን እየጨመሩ መሆናቸው ገልፆ ፤ የግዚያዊ መንግስቱ አስተዳደርና በየደረጃው ያሉት የመንግስት አካላት የህዝብ ደህንነት መጠበቅ ዋነኛና የቀን ተቀን ተግባራቸው መሆን መዘንጋት የለባቸውም ሲል አስገንዝቧል።

#ስለ_ዘውዱ_ሃፍቱ ፦ ነሃሴ 13/ 2015 መኪና በሚነዱ ማንነታቸው እስከ አሁን ባልታወቁ ሰዎች በመቐለ ፤ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ደስታ ሆቴል አከባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ለህልፈት የተዳረገች እንስት ስትሆን ፤ በወቅቱ አብራት የነበረች ሰምሃል የተባለች ጓደኛዋ በሁኔታው ደንግጣ ዓይደር ሆስፒታል ገብታለች።

የዘውዱ ገዳዮች እስከ አሁን በቁጥጥር ስር ባለመዋላቸው ህዝቡ በተለይ በውስጥና በውጭ የሚገኙ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ቁጣቸው በመግለፅ ላይ ናቸው። የከተማው ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ የምርመራው ስራ ስላልተጠናቀቀ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገር አመልክቷል።

በሌላ መረጃ ፤ ነሃሴ 26 / 2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:20  በመቐለ በተለምዶ " ዳያስፓራ " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ ወንጀል  ተፈፅሟል።

በአከባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንዳሉት የሰሌዳ ቁጥር " 02779 ኮድ 3 " ከሆነች መኪና በመውረድ በጉዞ ላይ የነበረ አንድ ወጣትን ለማጥቃት ሲጀምሩ ሰው ስለደረሰባቸው በያዙዋት መኪና ገጭተው አምልጠዋል። 

ይህንን መሰል የወንጀል ተግባሮች በመቐለ እና በሌሎች የክልሉ ከተሞች እየተባባሰ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ማሳያ ናቸው መባሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahFamilyMekelle
                          
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ላለፉት 39 ቀናት ያካሄድኩትን ሰብሰባ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አጠናቅቃለሁ " - የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ " ለ64 ቀናት ስብሰባ ተቀምጠን ህዝብን የሚረባ ጠብ ያለ ቁምነገር የለም " - የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜደንት ጌታቸው ረዳ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ላለፉት 39 ቀናት ከፀጥታ ሃይሎች ፣ ከተተኩ…
# Update
 
ህወሓት ለ41 ቀናት ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ከ64 ቀናት በላይ መካሄዱ የሚገልፁት ረጅም ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁ ፍንጭ ተሰጠ።

ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጥር 19/2016 ዓ.ም አመሻሽ " ኢንስቲትዩት ግርዓልታ ንመፅናዕትን ስልጠናን " ከትግራይ ህዝባዊ ግንኙነቶች ጉባኤ በመተባበር ባዘጋጀው የሁለት ቀን ውይይት ማጠቃለያ ተገኝተው እንዳሉት ድርጅታቸው ህወሓት ያካሄደው የግምገማ ፣ ሂስና ግለሂስ መድረክ ዛሬ መጠቃለሉን ፍንጭ ሰጥተዋል። 

ፕረዚደንቱ ዛሬ በመድረኩ በመገኘት ባደረጉት ንግግር ስብሰባው መጠናቀቁን የሚመለከት ፍንጭ ሰጥተዋል።

በተሰብሳቢዎቹ መካከል መግባባት መደረሱን፣ ህዝቡን ወደ ተሻለ የለውጥ ጉዞ መምራት የሚችል ማስተካከያ መደረጉንም ተናግረዋል።

ፕረዚደንቱ " ተደረሰ " ስላሉት መግባባትና ማስተካካያ ዝርዝር መረጃ እንዳልሰጡ ከቦታው የዘገበው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።  

#TikvahFamilyMekelle
                   
@tikvahethiopia            
#PretoriaAggrement

አሜሪካ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር እና በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤቪን ማሲንጋ ጋር ሆነው ወደ ትግራይ መቐለ ተጉዘው ከክልሉ ባለልስጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር ሀመር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት አሜሪካ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር አሜሪካ ድጋፏን እንደምታደርግ ገልጸዋል።

የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ቀደመው ህይወት ለመመለስ ለተጀመረው ስራ 15 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግም በይፋ አሳውቀዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ፤ የአሜሪካ መንግስት የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ፣ የፕሪቶሪያው ውል እንዲተገበር የሚያደርገውን ጥረት የሚደነቅ ቢሆንም ከዚህ በላይ አጠናክሮ መስራት አለበት ብለዋል። 

መቐለ የሄዱት አምባሳደር ማይክ ሃመር እና አምባሳደር ማሲንግ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ አቶ ጌታቸው ረዳን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር በመሆን አግንኝተዋቸው መክረው ነበር።

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PretoriaAggrement አሜሪካ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር እና በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤቪን ማሲንጋ ጋር ሆነው ወደ ትግራይ መቐለ ተጉዘው ከክልሉ ባለልስጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ሀመር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ከሌሎች…
#USA

አምባሳደር ሃመር እና አምባሳደር ማሲንጋ በመቐለ ቆይታቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (TPLF) ሊቀመንበር የሆኑትን ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን አገኝተው ተወያይተዋል።

ውይይታቸው የፕሪቶሪያ ስምምነትን አተገባበርን የተመለከተ ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ በኩል በፕሪቶሪያ ስምምነት ውል አተገባበር ዙሪያ ብዙ ጉዳዮች ቢፈፀሙም ፦
- ከጦርነት በፊት የነበረው የትግራይ አስተዳደር ግዛት መመለስ
- ህዝብ ነፃ የማውጣት ፣
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ ፣
- ለረሃብ ለተጋለጠ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ የማቀረብ ጉዳዮች ሳይፈፀሙ ረጅም ጊዜ መውሰዳቸው ለልኡካኑ ገልፀዋል።

ተመላሽ የሰራዊት አባላት የማቋቋም ጉዳይ ትኩረት የሚሻ ቢሆንም  ቀዳሚው ጉዳይ ከጦርነት በፊት የነበረው የትግራይ አስተዳደር ማረጋገጥና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ መሆኑ ዶ/ር ደብረፅዮን መግለፃቸውና ውይይቱ በቀጣይ ለሚኖሩ ለውጦች የሃሳብ ልውውጥ እንዲደረገ መግባባት መደረሱ ለማወቅ ተችሏል። 

#TikvahFamilyMekelle
                    
@tikvahethiopia            
#መቐለ

ባለፈው የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት በትግራይ መቐለ ከተማ ዓይደር ከፍለ ከተማ በተለምዶ " ሓሚዳይ የኢንዱስትሪ መንደር " ተብሎ በሚጠራ ቦታ በቡድን የተደራጁ ዘራፊዎች የተጠና ስርቆት ሊፈፅሙ ሲሉ ተደርሶባቸው አምልጠዋል።

በወቅቱ ይህ መረጃ የደረሰው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ቦታው ድረስ በመሄድ ጉዳዩን ተከታትሏል።

ድርጊቱ እንዴት ተፈፀመ ?

የካቲት 14/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት የተደራጁ ዘራፊዎች በሁለት አቅጣጫ #ጠባቂ_በመመደብ የተቀሩት በከፍታ ቦታ የተሰቀለው ባለ 400 ኪሎ ቮልት ትልቅ ትራንስፎርመር መሳልል በመጠቀም ወደ መሬት ለማውደቅ ይጥራሉ።

በዚህ መሃል በአከባቢው የነበረ ጥብቃ ማንነታቸው ሲጠይቃቸው ዘራፊዎቹ የመንግስት ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውንና ከማደናቀፍ ተቆጥቦ ስራውን እንዲሰራ ያስጠነቅቁታል።

ብዛት ያላቸው መሆናቸው የተገነዘበው የጥበቃ ባለሞያ ትእዛዛቸው ተቀብሎ የሄደ በመምሰል ራቅ ወዳለ ቦታ በመሄድ በአካባቢው ከሚያውቃቸው ጥበቃዎች ወደ አንዱ ስልክ ይደውላል።

በዚህ መሃል ዘራፊዎቹ ትራንስፎርመሩ ከነበረበት ከፍታ ቦታ ወደ መሬት በመጣል የሚፈልጉት የውስጥ አካል ለመዝረፍ በጥድፍያ ይሰራሉ።

በዚህ ሰዓት በፀጥታ የተዋጠው አከባቢ በጥይት #ቶክስ እና በጥሩምባ ድምፅ ይረበሻል።

ዘራፊዎቹ እጅግ ከመደንገጣቸው የተነሳ የጀመሩት ሳይጨርሱ በሩጫ በትንትናቸው ይወጣል።

በአከባቢው በነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ጥረት ስርቆቱ ከመፈፀም ቢድንም ትራንስፎርመሩ ከከፍታ ወደ መሬት ተከስክሶ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

የስርቆት ሙከራው ወደ ፓሊስና የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎተ ሪፓርት ተደርገዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እያፈላለገ ነው።

የኤሌክትሪክ ሃይል የቴክኒክ ቡድን ከስርቆት አምልጦ መሬት ላይ ወድቆ የተከሰከሰው ትራንስፎርመር ተጥግኖ መልሶ አገልግሎት መስጠት ይችል እንደሆነ እየሰራበት ነው። 


የስርቆት ሙከራው የተካሄደበት ቦታ ሓሚዳይ የተባለ የኢንዱስትሪ መንደር ፡ ቀን ሰውና ተሽከርካሪ የሚበዛበት ፤ ጨለማ ሲሆን ደግሞ በሰው እጦት ፀጥታ የሚሰፍንበት ነው።

የስርቆት ሙከራው ሲፈፀም በመቐለ በንፋስ ምክንያት በበርካታ አከባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ ስለነበረ ለስርቆቱ አመቺ ሁኔታ ሳይፈጥርላቸው አልቀረም ተብሏል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ገለሰብ ፤ የስርቆት ሙከራው ተራ ስርቆት ሳይሆን በኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች የታገዘ የባለሙያ ስርቆት ነው የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የትራንስፎርመር ስርቆት ሙከራው ምን ያለመ ነበር ?

የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስርቆቱ ለምን አላማ እንደተፈፀመ ለአንድ የኤሌክትሪክ ሃይል የቴክኒክ ባለሞያ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ባለሞያው ፦

- ይህ መሰል ሰርቆት በተለይ በጦርነቱ ጊዜ እጅግ የተባባሰ እንደነበረ ፤ ሰርቆቱ በትራንስፎርመሩ ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ ዘይትና ኬብል ለመውሰድ ያለመ መሆኑን፤

- ከትራንስፎርመሩ የሚቀዳ ዘይት ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ጥቅም ላይ እንደሚውል ፣ ኬብሉ ደግሞ ቀልጦ ከወርቅ ተደባልቆ እንደሚሰራና በተጨማሪ ለብየዳ ስራ እንደሚውል ፤

- አሁን ስርቆቱ በተፈፀመበት ቦታ በጦርነቱ ጊዜ 800 ኪሎ ቮልት ያለው በአከባቢው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎች የሚጠቀሙበት ትልቅ ትራስፎርመር በመፍታት በወስጡ ያለው ዘይት በመዘረፉ ምክንያት ተቃጥሎ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መደረሱን ገልጸዋል።

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ ባለፈው የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት በትግራይ መቐለ ከተማ ዓይደር ከፍለ ከተማ በተለምዶ " ሓሚዳይ የኢንዱስትሪ መንደር " ተብሎ በሚጠራ ቦታ በቡድን የተደራጁ ዘራፊዎች የተጠና ስርቆት ሊፈፅሙ ሲሉ ተደርሶባቸው አምልጠዋል። በወቅቱ ይህ መረጃ የደረሰው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ቦታው ድረስ በመሄድ ጉዳዩን ተከታትሏል። ድርጊቱ እንዴት ተፈፀመ ? የካቲት 14/2016…
" ... ተራ የዝርፍያ ሙከራ ሳይሆን #በባለሙያ የተደገፈና የተጠና ነው " - አቶ አዳነ ሓጎስ

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት 8:00 ሰዓት በተደራጁ የዘራፊ ቡድኖች በመቐለ " ሓሚዳይ የኢንዱስትሪ መንደር " የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ስርቆት ሙከራ ተደርጓል።

የመቐለው የቲክቫህ አባል ፤ ለጎርፍ መከላከያና የተለያዩ አጥሮች የሚውሉ የብረት ምርቶች የሚያመርተውን " ምድሓን ጋብዮን ፋብሪካ " የተባለ ደርጅት ባለቤት የሆኑት ባለሃብት አቶ አዳነ ሓጎስ ስለጉዳዩ እንዲያብራሩለት በስልክ ጠይቆዋቸዋል።

ትራንስፎርመሩ ለፋብሪካቸው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እንዲውል የገዙትና ዋጋው 3 ሚሊዮን ብር መሆኑን ፤ የትራንስፎርመር ስርቆቱ በአከባቢው ተደጋግሞ የተፈፀመና ተራ ዝርፍያ ሳይሆን #በባለሙያ የተደገፈና የተጠና መሆኑን ገልጻዋል።

ይህ እየታወቀ ግን መንግስትና ፓሊስ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ባለማስቆማቸው ማዘናቸውን አስረድተዋል።

" የስርቆት ሙከራው እጅግ የተጠና ባለሃብቱን ተስፋ ከማስቆረጥ አልፎ አገር አስጥሎ የሚያሰድድ ነው " ብለዋል።  

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ?

ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱና የክልሉ አስተዳደራዊ ወሰን እንዲከበር ጠይቀዋል።

በጥቅሉ ያነሷቸው ጥያቄዎች  ምንድናቸው ?

- የመከላከያ አባላት የነበሩት ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤
- የትግራይ ነጋዴዎች ከጦርነቱ በፊት የወሰዱት የብድር ወለድና ቅጣት ይነሳ፤
- የመንግስት ሰራተኞችና የጡረተኞች ውዙፍ ደመወዝና አበል ይከፈል፤
- ከትግራይ ሰራዊት (TDF) ለተሰናበቱ ታጣቃዊች ማቋቋምያ ይከፈል፤
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር፤
- ከረሃብ ጋር በተያያዘ እርዳታ ይደረግ ፤
- የህወሓት የህጋዊነት ጥያቄ ለምን ዘገየ ?
የሚሉና ሌሎች ይገኙባቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምን መለሱ ?

ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ ብዙ ስኬቶች እንዳሉ አሁንም ግን የሚቀር ብዙ እንዳለ ገልጸዋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በጥይት ሰው እንዳልሞተ ተናግረዋል። በትግራይ መረጋጋት ፤ መንግሥት መመስረት ፣ ህወሓት (TPLF) ከሽብርተኝነት መፋቅ የስምምነቱ ውጤት ነው ብለዋል።

ከስምምነቱ በኃላ በርካታ ቢሊዮን ብሮች በካሽም በቁሳቁስም ወደ ትግራይ ክልል መላኩን ገልጸዋል።

እስረኞችን መፍታት በተመለከተ ፦

" ስብሃትን ፈትቼው የለም እንዴ ? ፣ አልፈልግም እንዲታሰሩ።

የመከላከያን በተመለከተ እራሱ ይነግራችኋል (ዶ/ር አብርሃምን ማለታቸው ነው) አላውቅም በእኔ እውቀት #አንድም_የታሰረ_ሰው_የለም።  ከስራ ያቆምናቸው ታጋዮች ነበሩ እርቁ ሲፈፀም መፍታት እኮ አይደለም ወደቦታቸው ነው የመለስናቸው። አሃዱ አለቃ ናቸው ሁሉም በየቦታው በየደረጃው ኃላፊዎች ናቸው መከላከያ ውስጥ ...

እስረኛ በሌብነት ምክንያት ካለ አላውቅም ፤ እስረኛ ሰው ገድሎ የታሰረ ወንጀለኛ ካለ አላውቅም። ከግጭቱ ጋር የሚያያዝ ግን በመከላከያ ወጥተው የነበሩት ተመልሰው መከላከያ ውስጥ ገብተዋል።

እኛ እንደዚህ አይነት ፍላጎት የለንም። የምናውቀውም የለም። እኛ እስረኛ ፈተን ስራ አስፈፃሚ ፈተን ጌታቸው ጋር የቀሩ እስረኞች ነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያልፈታቸው ። "

ትግራዋይ ተፈናቃዮችን በሚመለከት ፤ ተፈናቃዮች በስምምነቱ መሰረት ቤታቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የአማራ ክልሉ አቶ አረጋ ፣ ዶ/ር አብርሃም ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰሞኑን ንግግር ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ የተፈናቀሉ ሰዎች በሙሉ ቤታቸው እንዲመለሱ ነው ያሉ ሲሆን " በማንኛውም ሰዓት ነገ ሁመራ ያለው ቤቴ መመለስ እፈልጋለሁ የሚል ካለ እኛ ለመመለስ ዝግጁ ነን " ብለዋል።

#መከላከያ በአካባቢው የትግራይም ይሁን የአማራ ፀጥታ ኃይል እንዳይኖር ኃላፊነት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ሁሉም ሰዎች ወደ ቤታቸው #ከተመለሱ_በኃላ እራሱ ህዝቡ አስተዳዳሪውን እንዲመርጥ እንደሚደረግና ከተረጋጋ በኃላ ህዝቡ ሪፈረንደም በማድረግ " እኔ አማራ ነኝ ፤ እኔ ትግራይ ነኝ " የሚለውን እንደሚወስን ተናግረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ተፈናቃዮች መቐለ ፣ ሽረ መቀመጥ እንደማያስፈልጋቸውና ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ረገድ ፌዴራል መንግሥት የሚጠበቅበትን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በነበረው ሁኔታ ውጭ ሀገር የሄደ ባለሃብት ካለ መመለስ ይችላል ፣ ከባላሃብቶች ጋር በተያያዘ ችግር ካለም ይፈታል ብለዋል።

#ረሃብን በተመለከተ ጉዳዩን ፖለቲካዊ ማድረግ እንደማይገባና ትግራይ ተርባ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በልቶ ጠግቦ እንደማያድርግ ገልጸዋል። " ጌታቸውንም ወቅሼዋለሁ ረሃብ ካለ መደወል ነው እኔ ጋር ያለ አምጡ አግዙ ማለት ነው ቀላል ነው በትዊተር ከሆነ ግን እኛ በትዊተር አንነጋገርም ብሄዋለሁ ለሌሎች ነው የነገርከው እንጂ እኔ አልሰማሁም " ሲሉ ገልጸዋል። " ረሃብ ረሃብ ችግር ችግር አለ የሚል ፖለቲካ " ማድረግ ተገቢ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሚቴ ተቋቁሟል ሄዶ ጥናት አድርጎ መደረግ ያለበት ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/TPLF እውቅናን በተመለከተ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድ ቢሆንም " በእኛ በኩል መሰጠት አለበት ብለን እናምናል ፤ በቅርብም #አነጋግረናቸዋል የሚፈታ ይመስለኛል ፤ ብዙም ከባድ አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#ከባንክ ጋር በተያየዝ ጉዳዩ ውስብስብ መሆኑን በማስረዳት መናገር ያልፈለጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቢሯቸው አማካሪዎች እና ጉዳዩን በቀጥታ የሚያዩ የሚመለከታቸው አካላት ተነጋገረው የሚቻል ነገር ካመጡ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ከባንክ ብድር ጋር በተያያዘ " ብድር ተከለከልን " የሚሉ ባላሃብቶች ካሉ ከዶ/ር አብርሃም እና ከሌሎች የሚመደቡ ሰዎች ጋር እንዲነጋገሩ አቅጣጫ ሰጥተው አልፈዋል። በመንግሥት ፖሊሲ ሊፈታ የሚችል ካለ ግን እንደሚታይ ገልጸዋል።

በኤርታራ መንግሥት (በሻዕብያ ኃይል) ስለተያዙ መሬቶች በተመለከተ ፤  የፌዴራል እና ከትግራይ የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙን በዚህም የሀገር መከላከያ ከትግራይ ጓዶች ጋር በመሆን ቦታዎችን እንዲያዩ እንደሚደረግ ገልጸዋል። " #ከአልጀርስ_ስምምነት ውጭ የሆነ ካለ ሪፖርቱ ሲመጣ እናያለን ፤ ማንም የማንንም ቦታ በኃይል ይዞ ለዘላለም መኖር አይችልም እንዳንዋጋ፣ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር ትርፍ ነገር የተካሄደ ካለ አይተን ቦታውን ለይተን ኦፊሻሊ እነዚህ ነገሮች ይስተካከሉ ብለን በንግግር መልክ ልናበጅ እንችላለልን " ብለዋል። ውጤቱ ታይቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተግረዋል።

➡️ የጡረተኞችን ውዝፍ ክፍያን በተመለከተ ምንም ሳይሉ አልፈው በአቶ ጌታቸው በኩል ያለውን ነገር እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ሌሎችም አንዳንድ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ በቀጥታ አስተያየት ባይሰጡም በጥቅሉ በክልሉ ካሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በውይይት በምክክር እንደሚፈቱ ቃል ገብተዋል።

#TikvahFamilyMekelle
#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#መቐለ

በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ፥ ዘስላሴ ቀበሌ ቀጠና 14 በሚገኘ " እየሩሳሌም " በተባለ ሆቴል እፍሬም ፍትዊ ገ/ክርስቶስ የተባሉ ግለሰብ በመኝታ ክፍል ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን የክ/ከተማው ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ መጋቢት 20/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ነው በያዙት የመኝታ ክፍል ውስጥ ሞተው የተገኙት።

የአሟሟታቸው ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችል የአስክሬን ምርምራ በዓይደር ሆስፒታል በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የሟች ቤተሰቦች እስከ መጋቢት 22 /2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ ወደ ፖሊስ ሪፓርት ካላደረጉ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ከአስከሬን ምርመራ በኃላ የቀብር ስነ-ሰርአት ለመፈፀም እንደሚገደድ ፖሊስ አመልክቷል። (104.4 የመቐለ ኤፍኤም ሬድዮ)

#TikvahFamilyMekelle
        
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው።  "አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ?  የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል። ታጋቹ…
#Update

ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል።

ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?

የማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦች ፦

" ታዳጊ ልጃችን ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ከ 11:00 ሰዓት በኃላ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በመሄድ ሳለች በትግራይ ዓድዋ ከተማ ዓዲ ማሕለኻ ተብሎ ከሚጠራ ልዩ ቦታ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና ተወስዳለች።

አጋቾቹ በወሰዱዋት ቀን በራስዋ ሞባይል ስልክ ወደኛ በመወደወል ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንድንከፍላቸው ጠይቀውናል።  ከዛ በኃላ ግን በደውሉበት የልጃችን የሞባይል ቁጥር ብንደውልም አናገኛቸውም፤ በሌላ የሞባይል ቁጥር ደውለውም ያሉን ነገር የለም።

ስለሆነም እኛ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ወላጆች በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንገኛለን። ስለዚህ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና የፀጥታ አካላት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ እናቀርባለን። "

ማህሌት ተኽላይ የሚመለከት ማንኛውም አይነት መረጃ ለመስጠት ፦
+251938819844 ሙሴ ተኽላይ
+251992733943 ደጀን ተኽላይ 
+251935036100/
+251962529287 ሚልዮን ተኽላይ
በሚሉ የሞባይል ቁጥሮች እንድትጠቀሙ በትህትና እንጠይቃለን። "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ቤተሰቦችን ጠይቆ ፥ " የዓድዋ ፓሊስ እኛን መልሶ ምን አዲስ ነገር አለ ብሎ ይጠይቀናል ? " ሲሉ መልሰዋል።

የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ #ዓድዋ እና #አክሱም ያደረገው ጉዞ በፓሊስ አመራሮች ስብሰባ ምክንያት አልተሳካም።

#TikvahFamilyMekelle
                                            
@tikvahethiopia            
#Mekelle

በመቐለ የሚገኘው " ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል " በእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ወድመት አጋጥሞታል። 

አደጋው ያጋጠመው ሚያዝያ 7/ 2016 ዓ.ም ሲሆን ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ የእርዳታ ጥሪ ተማጽኖ አቅርቧል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱን የተለያዩ በጎ አድራጊዎች ሲረዱት ቆይተዋል።

የሚያዘያ 7ቱ የእሳት አደጋ ከአጋዦቹ አንዱ የሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሚሊዮን ብሮች በመስጠት ባሰራው አዳራሽ ነው የደረሰው።

በተነሳው ቃጠሎም አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በተረጂዎች ማደሪያ ፣ መመገብያና ፣ መስሪያ ክፍሎች ወድመት ደርሷል።

በከፍተኛ ውጪ የተሰራው አዳራሽ ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. የተመረቀ ሲሆን በነጋታው  ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነው በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመው።

የአደጋው መንስኤ በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ በተነሳ ቃጠሎ ነው ተብሏል።

ያጋጠመው ቃጠሎ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በህዝብና በመቐለ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ የተቀናጀ ርብርብ በማእከሉ በሚገኙ አቅመ ደካሞች የህይወት ማጣት አደጋ  አልደረሰም።

ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት የመኝታ፣ መመግብያ ክፍሎቻቸው የተቃጠለባቸው የሚንከባከባችው አቅሞ ደካሞች ሜዳ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ በመጠቆም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰብአውያን ሁሉ እንዲረዱት ጥሪ አቅርበዋል።    

መርዳት የሚፈልጉ ወገኖች ፍሬምናጦስ  የአረጋውያን የእአምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000622132404 ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia