TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#StateofEmergency

ባልተረጋገጡ ወሬዎች እንዳትረበሹ!

የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ ማሳሰቢያ፦

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀዉን የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በዛሬው ዕለት አጽድቋል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 4 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 መሰረት የሚጣሉ የመብት እገዳዎች፣ እርምጃዎች እንዲሁም ግዴታዎችን በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ መግለጫ ይሰጣል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰባችን ከአሰቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ ያልተረጋገጡ ወሬዎችን እና መረጃዎችን ከመሰማት እንዲቆጠብ እናሳስባለን።

በአዋጁ መሰረት ከሚዉጡ ህጎች ጋር በተያያዘ ማብራሪያ የመሰጠት ኃላፊነት በተሰጠዉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል እስከሚሰጥ ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን። ዝርዝር መግለጫው የሚሰጥበትን ሠዓት ነገ አሰቀድመን የምናሳወቅ ይሆናል ፡፡

ሚያዚያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StateofEmergency

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

ክልከላን በሚመለከት፦

- ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

-አራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን አለበት።

- ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር ይኖራል።

- ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች አይፈቀደም።

- በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ ነው።

- በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

- የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስወጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

- ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም ተከልክሏል።

- ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

MORE @TIKVAHETHMAGAZINE

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StateofEmergency

የተጣሉ ግዴታዎች!

- ማንኛውም በስራ ላይ ያለ ፣ ጡረታ የወጣ ወይም በትምህርት ላይ ያለ የጤና ወይም የሌላ ሙያ ባለቤት ወይም ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በመንግስት ጥሪ ሲደረግለት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

- ማንኛውም የቤት፣ የሆቴል፣ የአፓርታማ፣ የተሽከርካሪ፣ የአዳራሽ ወይም የማንኛውም ንብረት ባለቤት መንግስት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል ፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ ንብረቱን ለዚህ አላማ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል ሲወሰንና ሲጠየቅ ንብረቱን ለእለት ከእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ካልሆነ በሰተቀር ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት።

ተጨማሪ የተጣሉ ግዴታዎችን ይህን ተጭነው ያንብቡ : https://telegra.ph/DrAbiyAhemed-04-11

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StateOfEmergency

የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች ፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች እና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ #ግዴታ አለበት።

የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#StateofEmergency

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከዚህ በፊት ባወጣው መመሪያ መሠረት የጦር መሣሪያዎች የምዝገባ ሁኔታን ገምግሟል።

ዕዙ ፥ በግምገማው መሠረት ብዙ መሣሪያዎች በየክልሉ የተመዘገቡ መሆኑን በመመልከት ኅብረተሰቡ እና የጸጥታ ኃይሎች ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርቧል።

የኅብረተሰቡን የተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ከዚህ በፊት የወጣው ትእዛዝ የገጠር አካባቢዎችን ባለማካተቱ የተነሣ፣ የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም እንደሚያስፈልግ ዕዙ አምኗል።

በመሆኑም በሁሉም የሀገሪቱ የገጠርና የከተማ አካባቢዎች ከኅዳር 30/2014 ዓም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጦር መሣሪያ ምዝገባው እንዲቀጥል ተወስኗል።

በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ጽ/ቤቶችም ይሄንን መመሪያ እንዲያስፈጽሙ ታዝዟል።

ይህ መመሪያ በጦር ግንባር የዘመቱ እና የሚታወቅ የጸጥታ ኃይል እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን እንደማይመለከት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#StateofEmergency

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል።

በዚህም ስብሰባው በዋነኝነት በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱም በመላው ሀገሪቱ እንዲፈፀም ለ6 ወራት ታውጆ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

የምክር ቤት አባላት ዛሬ ከመሸ ለነገው ልዩ ስብሰባ " አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማረዘም " የሚለውን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎች እንደተላከላቸው ተነግሯል።

የተወካዮች ምክር ቤት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያጸደቀው ነሐሴ 8/2015 ነበር።

ለ6 ወራት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት በመጠናቀቁ ነገ ም/ቤቱ በ " ልዩ ስብሰባ " አዋጁን ያራዝመዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህን መረጃ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የምክር ቤት አባላትን ዋቢ በማድረግ ነው ያሰራጨው።

@tikvahethiopia
#StateofEmergency #EHRC

" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።

በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።

ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።

በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።

#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency

@tikvahethiopia