TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DonaldTrump #DrAbiyAhemed

“ከኢትዮጵያው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ተወያይተናል ፤ ኢትዮጵያ #ቬንቲሌተሮች (የመተንፈሻ መሳሪያ) ያስፈልጓታል አሜሪካም ድጋፍ ለማድረግ በጥሩ አቋም ላይ ትገኛለች፤ ይህንንም እናደርጋለን!” - ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ
.
.
"ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የኢትዮ - አሜሪካንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ዙሪያ አበረታች የስልክ ውይይት አድርገናል፡፡ የCOVID-19 መከላከል እና ቅነሳ ጥረቶች እንዲሁም በበረሃ አንበጣ ቁጥጥር ላይ የሚደረገውን ድጋፍ ለማድነቅ እወዳለሁ፡፡" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DonaldTrump

በትላንትናው ዕለት ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንዲት ኤሲያዊ-አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የተነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ ንትርክ ምክንያት ሲሰጡት የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ በድንገት አቋርጠዋል፡፡

ትራምፕ ጋዜጠኛዋ ላነሳችው ጥያቄ “ቻይናን ጠይቂ “ የሚል መልስ ከሰጡ በኋላ ከሌላ የኋይት ሀውስ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ጥያቄ ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

የCBS ዜና የኋይት ሀውስ ዘጋቢ የሆነችው ጋዜጠኛ ዌይጃ ጂያንግ ከ80,000 በላይ አሜሪካውያን በሞቱበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን ለምን እንደ አለምአቀፍ ውድድር እንደሚያዩት ፕሬዘዳንቱን ጠይቃለች፡፡

ትራምፕ ቻይና ተወልዳ በ2 አመቷ ወደ አሜሪካ ለመጣችው ጋዜጠኛ “ያንን ጥያቄ ቻይናን ነው መጠየቅ ያለብሽ፣ ቻይናን ጠይቂ፤ እሽ”ብለዋታል፡፡

ትራምፕ ይህን ካሉ በኋላ ወደ ሌላ የኋይት ሀውስ ዘጋቢ ለማለፍ ሞክረው ነበር፤ነገርግን ጂያንግ በተከታይ ጥያቄ ትራምፕን አቋረጠቻቸው፡፡

“ጌታው፣ ያንን በተለየ ለምን እኔን አሉኝ” በማለት በትራምፕ የተገረመችው ጂያንግ ጠየቀች፡፡

“እየነገርኩሽ ነው” ትራምፕ ይመልሳሉ፡፡ “ ይህን በተለየ ለማንም አልናገርም፡፡ አስቀያሚ ጥያቄ ለሚጠይቅ ለማንም እመልሳለሁ” ብለዋል፡፡

“ይህ አስቀያሚ ጥያቄ አይደለም” ስትል ጂያንግ መልሳለች፡፡ “ምን ችግር አለው?” በዚህ ጊዜ ትራምፕ ከሌላ ጋዜጠኛ ጥያቄ ለመቀበል ሲሞክሩ ነበር፡፡

(በአል ዓይን የተዘጋጀ)

#AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump

"የኮቪድ-19 ክትባት ሰራም አልሰራም አሜሪካ ወደቀደመ እንቅስቃሴዋ ትመለሳለች" - ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ

(በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ በሽታውን በቁጥጥር ስር እናውለዋለን ሲሉ ተናግረዋል።

ፕረዝደንቱ ፤ የአሜሪካ ሳይንሲስቶች ይፋ ያደረጉትና በቅርቡ በሰዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለውን ክትባትም ፍጥነት አድንቀዋል፡፡

ምንም እንኳን በዝንጀሮ ላይ የተሞከረው ክትባት ተስፋ አሳይቷል ቢባልም ያም ሆነ ይህ ክትባቱ ተስፋ ሰጪም ሆነ አልሆነ አሜሪካዊያን ወደ መደበኛ እቅስቃሴያቸው ይመለሳሉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ኮሮና ቫይረስን (ኮቪድ-19) ይከላከላሉ የተባሉ ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DonaldTrump

"የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ቻይና በአፍሪካዊያን ላይ የፈጸመችውን ዘረኛ ድርጊት ችላ ብሏል" - ዶናልድ ትራምፕ

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይናዋ ደቡባዊ ከተማ ጉዋንዡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቀስቀሱን ተከትሎ በአፍሪካዊያን ላይ ሲፈጸም ለነበረው ዘረኛ ድርጊትና መድልዎ የዓለም ጤና ድርጅት ጠንካራ ምላሽ አልሰጠም ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ትራምፕ ለድርጅቱ ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጻፉት ደብዳቤ ላይ አፍሪካዊያን በግድ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ፣ ከመኖሪያቸው እንዲባረሩ ፣ እንዲሁም አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግን ጨምሮ ዘረኛ እና አድሎአዊ ድርጊት ደረሰብን ቢሉም፤ ድርጅቱ በቻይና #ዘረኛ ድርጊት ላይ አስተያየት አልሰጠም ሲሉ ከሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DonaldTrump

በኮቪድ-19 ተይዘው ሆስፒታል የገቡት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደህና መሆናቸውንና ቀጣዮቹ ቀናት ለጤንነታቸው ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት ጤንነታቸውን አስመልክቶ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎችን ተከትሎ ትላንት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ነው።

"እዚህ ስመጣ ደህና አልነበርኩም ፤ አሁን ላይ ግን እየተሻለኝ ነው" ብለዋል ትራምፕ። የሚቀጥሉት ቀናት ወሳኝ እንደሆኑ ገልፀው፤ " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ምን እንደሚፈጠር እናያለን" ብለዋል።

የፕሬዚደንቱ ሐኪም ትራምፕ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ሕክምናውን ከጀመሩ አንስቶ ለውጥ እያሳዩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሐኪማቸው ዶ/ር ኮንሊ በሰጡት መግለጫ ላይ ፕሬዚደንቱ ከተጋረጠባቸው አደጋ ሙሉ ለሙሉ ባይላቀቁም ፤ የሕክምና ቡድኑ ግን በሁኔታቸው ተስፋ እንዳለው ተናግረዋል - (BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው እንደተጭበረበረ ዳግም ተናግረዋል።

ከFOX ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጥቅምት 24 የተደረገው ምርጫ 'ሙሉ በሙሉ የተጭበረበረ ነው' ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ የትራምፕ ንግግር የምርጫ 'ውጤቱን እንደማይቀበሉ' አመላካች ነው ሲል ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE አሜሪካ የፋይዘር/ባዮንቴክ ሰራሹን የኮሮና ቫይረስ ክትባቶቹን "ወደ ሁሉም ግዛቶቿ" ማከፋፈለች መጀመሯን ተገልጿል። አሜሪካ ዜጎቿን ዛሬ መከተብ የምትጀምር ሲሆን እስከ መጋቢት ማገባደጃ ድርስ 100 ሚሊዮን ሰዎችን ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ክትባቱን ቅድሚያ የሚያገኙት ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ የሆኑት የጤና ባለሙያዎችና በእንክክብካቤ ማዕከላት የሚገኙ አረጋውያን ናቸው…
#DonaldTrump

የUS ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዮቹ ቀናት ለዋይት ሐውስ ባለሥልጣናት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመስጠት የተያዘውን እቅድ መቀየራቸውን አስታወቁ።

ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለሥልጣናት ክትባቱን ለመውሰድ ረዘም ያለ ጊዜ መጠበቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ፕሬዚደንቱ "በዋይት ሐውስ የሚሰሩ ሰዎች አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ነው ክትባቱን መውሰድ ያለባቸው" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ይህ እቅድ እንዲስተካከልም ጠይቄያለሁ ብለዋል።

ትራምፕ ክትባቱን ለመውሰድ ገና እንዳላቀዱ ገልፀው ፤ በተገቢው ጊዜ ይህንን ለማድረግ በጉጉት እንደሚጠባበቁ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@TIKVAHETHIOPIA
#DonaldTrump

- ፌስቡክ
- ኢንስታግራም
- ትዊተር
- ስናፕቻት እነዚህ ሶሻል ሚዲያዎች የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ትራምፕ ምንም አይነት መልዕክት እንዳያስተላልፉ ወይም ፖስት እንዳያደርጉ አግደዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ በረቷቸው ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙ አሳውቀዋል።

ጆ ባይደን ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመታቸው ቃለ መሐላ በመፈፀም 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከካፒቶል ነውጥ በኃላ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ይሁንና ዘግየት ብለው "የምትጠይቁኝ ካላችሁ በመጪው ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመት ላይ አልገኝም" ሲሉ አሳውቀዋል፡፡

Via Sheger FM 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump

የትራምፕ ደጋፊዎች ከፈጸሙት የአመጽ ድረጊት ጋር በተያያዘ ፣ የአሜሪካ ም/ቤት ፕሬዝዳንቱ በ25ኛው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሰረት ከስልጣን እንዲወርዱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ፣ ሀገሪቱን በአግባቡ መምራት ያልቻለ ፕሬዝዳንንት ከስልጣኑ ተነስቶ ምክትሉ መሪነቱን እንዲረከብ የሚደነግገውን 25ኛውን ማሻሻያ እንደማይተገብሩት ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንቱን በኢምፒችመንት ከስልጣን ለማውረድ ዝግጅት ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል ፕሬዝዳንቱን ለመክሰስ ዛሬ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ኢምፒችመንት የሚካሄድባቸው መሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ትራምፕ ከኋይት ሀውስ ለመውጣት የቀራቸው 1 ሳምንት ቢሆንም ፣ ፕሬዝዳንቱ በኢምፒችመንት እንዲነሱ ባለቀ ሰዓት ሩጫ መጀመሩ ፣ በዋነኛነት ከዚህ በኋላ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይቀርቡ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ (አል ዓይን)

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል። አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው…
#USA

በትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ወጥተዋል።

የግድያ ሙከራ ያደረገው ቶማስ ማቲው ክሮክስ የተባለው የ20 ዓመት ወጣት ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ከሚደረጉበት ስፍራ ውጭ ላይ ካለ አንድ ጣራ ላይ ተኝቶ ትራምፕን ለመግደል በተደጋጋሚ ሲተኩስ ታይቷል።

ብዙ ሳይቆይ በሴክሬት ሰርቪስ የስናይፐር ተኳሾች ተመቶ ተገድሏል።

የተለያዩ የአይን እማኞች ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሰጠቱ ቃል ፥ የግድያ ሙከራ ያደረገው ወጣት ጣራ ላይ ሲወጣና ከአንዱ ጣራ ወደሌላኛው ጣራ ሲሄድ በኋላም ተኝቶ ትራምፕ ላይ ሲተኩስ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ጣራ ላይ መሳሪያ የያዘ ሰው እንዳለ ለፖሊስ አባላት ጥቆማ ሰጥተው እንደነበር ጠቁመዋል።

የግድያ ሙከራው እስኪደረግ ድረስ ጥቆማቸው ለምን ችላ እንደተባለ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።

አንዳንድ የደህንነት ባለሞያዎች ሁሉም ጣራዎች ላይ ለምን የሴክሬት ሰርቪስ ሰዎች እንዳልነበሩ እና በሰዓቱ የነበረው የደህንነት ስራው ምርመራ እንዳሚፈልግ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ " ሴክሬት ሰርቪስ " ዋነኛ ስራው የአሁን እና ቀድሞ ፕሬዜዳንቶችን ደህንነት ማስጠበቅ ነው።

በሀገሪቱ በአሁን ወይም በቀድሞ ፕሬዜዳንቶች ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ የአሁኑ ከ43 ዓመታት በኋላ ነው።

ከ43 ዓመታት በፊት ሮናልድ ሬገን በተሞከረባቸው ግድያ ክፉኛ ተጎድተው ለጥቂት ነበር ከሞት ያመለጡት።

#USA
#DonaldTrump

@tikvahethiopia