TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሩብል📉

የምዕራባውያን ማዕቀብ እጅጉን የበረታባት ሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሷል።

አሁን ላይ 1 የሩስያ ሩብል $0.0085 ከ1 የአሜሪካ ሳንቲም በታች ወይም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እየተመነዘረ ነው።

አንድ የአሜሪካ ዶላር በሩስያ ሩብል ሲመነዘር ፦

• ከአንድ ወር በፊት : 76.2 ሩብል
• ከአንድ ሳምንት በፊት : 81.4 ሩብል
• ከአንድ ቀን በፊት : 108.5 ሩብል
• አሁን : 117.18 ሩብል

ምዕራባውያን አንዳንድ የሩሲያ ባንኮች #ስዊፍት የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማዘዋወሪያ ስርዓትን እንዳይጠቀሙ አግደዋቸዋል።

እገዳውን ተከትሎ ነው የሩሲያው ሩብል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ደረጃ ዋጋው የወረደው።

ምዕራባውያን በሩስያ ባንኮች ላይ ጠንካራ የሆኑ ማዕቀቦችን ጥለዋል ፤ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክም 630 ቢሊዮን ዶላር ከማንቀሳቀስ ታግዷል።

አሁንም የምዕራባውያኑ ሀገራት በሩስያ ላይ እየጣሉት ያለው ጠንካራ ማዕቀብ የሩስያን ኢኮኖሚ እንደሚያሽመደምደው እና ከዓለም አቀፉ ስርዓት እንደሚገፋው ተንታኞች እየተናገሩ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩብል📉 የምዕራባውያን ማዕቀብ እጅጉን የበረታባት ሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሷል። አሁን ላይ 1 የሩስያ ሩብል $0.0085 ከ1 የአሜሪካ ሳንቲም በታች ወይም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እየተመነዘረ ነው። አንድ የአሜሪካ ዶላር በሩስያ ሩብል ሲመነዘር ፦ • ከአንድ ወር በፊት : 76.2 ሩብል • ከአንድ ሳምንት በፊት : 81.4…
#Rubel

ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በምዕራባውያን ብርቱ የሆነ ማዕቀብ ምክንያት የሩስያ የመገበያያ ገንዘቧ የሆነው #ሩብል ከአሜሪካ #ዶላር አንፃር በእጅጉ ቀንሶ እንደነበር ይታወሳል።

ከሳምንታት በፊት በተለዋወጥነው መረጃ 1 የአሜሪካ ዶላር በ117.18 የሩስያ ሩብል እስከመመንዘር ደርሶ ነበር።

ይህም ፥ የሩሲያው ሩብል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ደረጃ ዋጋው እንዲወርድ አድርጎት ነበር።

አሁን ላይ ግን በሩብል እና የአሜሪካ ዶላር ያለው ልዩነት በእጅጉ ጠቧል።

ከሳምንታት በፊት በ117.18 ሩብል ሲመነዘር የነበረው የአሜሪካ ዶላር ዛሬ በ80.25 ሩብል እየተመዘረ ይገኛል።

👉 የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ/ም - አንድ የአሜሪካ ዶላር 117.18 ሩብል

👉 ዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ/ም - አንድ የአሜሪካ ዶላር 80.25 ሩብል

የምዕራባውያን ጠንካራ ማዕቀቦችን ተከትሎ የኢኮኖሚ ተንታኞች የሩስያ ኢኮኖሚ በአጭር ጊዜ ሊሽመደመድ እንደሚችል እና የከፋ ችግር ላይ እንደምትወድቅ መግለፃቸው ፤ ሩስያ በበኩሏ እየተጣሉባት ያሉት ማዕቀቦች ይበልጥ ነፃና ጠንካራ ሀገር እንደሚያደርጋት መግለጿ ይታወሳል።

@tikvahethiopia