TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢሠፓ

በደርግ ዘመነ መንግስት ገዢ ፓርቲ የነበረውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲን (ኢሠፓ) ዳግም ለማቋቋም የተሰባሰቡ ግለሰቦች፤ የምስረታ ሰነዶቻቸውን ለምርጫ ቦርድ አስገብተው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ለማግኘት እየተጠባበቁ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የፓርቲው የምስረታ ሰነዶች እንደደረሱት አረጋግጧል።

ኢሠፓን ከ30 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ለመመለስ የተሰባሰቡት ግለሰቦች፤ የምስረታ ሰነዶችን ለምርጫ ቦርድ ያስገቡት ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻ መሆኑን የፓርቲው አደራጆች ገልጸዋል።

ከአደራጆቹ መካከል የሆኑ እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር በሰጡት ቃል ፤ " የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተን [ለቦርዱ] አስገብተናል " ብለዋል።

" በአዲስ መልክ ተመልሶ ይመሰረታል " የተባለለትን ኢሠፓን በማደራጀት ላይ ከሚገኙት ውስጥ #የቀድሞው የፓርቲ አባላት ይገኙበታል ተብሏል።

ከእነዚህ የቀድሞ አባላት ውስጥ በኢሠፓ #በከፍተኛ_አመራርነት ያገለገሉ እንዳሉበት እኚሁ አደራጅ ቢገልጹም ማንነታቸውን ከመግለጽ ግን ተቆጥበዋል። 

" የቀድሞዎቹ የኢሠፓ አመራሮች በእስር ቤት ያለፉ ሰዎች ናቸው። ከስህተታቸው ብዙ ትምህርት ተምረዋል " የሚሉት አደራጁ፤ ግለሰቦቹ እንደገና በሚቋቋመው ፓርቲ የሚኖራቸው ሚና ከኋላ ሆነው ልምዳቸውን የማካፈል መሆኑን አስረድተዋል።

በአደራጆቹ ስብስብ ውስጥ ከቀድሞዎቹ የኢሠፓ አመራሮች እና አባላት በተጨማሪ #ወጣቶችም መካተታቸውን መግለፃቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#የትምህርት_እድል

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች አወዳድሮ ለማስተማር እንደሚፈልግ ገልጿል።

የምዝገባ መስፈርቶቹ ከታች የተዘረዘሩት ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተማሪዎች ተመዝግባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።

ሀ/ የውድድር መስፈርቶች

1ኛ. ክልላዊ የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት (average) (ጥሬ ማርክ) ለወንድ 78 እና ከዛ በላይ ለሴት 75 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገበ / ያስመዘገበች

2ኛ. ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ከፍተኛ ፍላጎት ያለው/ያላት 10ኛ ክፍል ካጠናቀቀ በኋላ በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልግ/የምትፈልግ

ለ. ዝርዝር መረጃ

• የምዝገባ ቀን ከ09/12/14 - 13/12/14
• የምዘገባ ቦታ-በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ፡ በቀድሞው ቀዳማዊ ምኒልክ የመጀመሪያ ት/ቤት፡፡ ከአራዳ ክ/ከተማ ፊት ለፊት
• የምዝገባ ሰዓት ከረፋዱ 3፡00 - ቀኑ 10:00

ሐ/ ተወዳዳሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ

• ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ውጤት የሚገልጽ ዋናውንና 1 ፎቶ ኮፒ
• የመመዝገቢያ ብር 400
• አንድ ክላሰር ይዛችሁ ተገኙ

መ. ተጨማሪ መረጃ

• የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/12/14 ከቀኑ 7፡30 - 10፡30
• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ በካምፓሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ተብሏል።

ት/ቤቱ ጎበዝ ተማሪዎች በማፍራት በሀገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎችም እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ያፈራ ት/ቤት ነው።

ለአብነት በ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና 78 ተማሪዎችን አስፈትኖ 42 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በኢትዮጵያ ትልቁ ውጤት የመጣውም 659 ከዚሁ ሲሆን በት/ቤቱ ዝቅተኛ ውጤት የነበረው 529 ነበር።

@tikvahethiopia
#ውብ_አረቢያን_መጅሊስ

ከአውሮፓና ከእስያ በሚመረቱ ጥሬ እቃ በብቁ ባለሞያ በዘመነ ማሽን ውብ አረቢያን መጅሊስ የሚያመርታቸውን ውብ እና ማራኪ የሆኑ መጅሊሶቻችን እና ሶፋዎችን እንካቹ ስንል 👉 በ9 ቅርጫፎቻችን ስንጠበቅዎ በታላቅ ደስታ ነው 0910222244 / 0954111133 / 0954111100
ተጨማሪ ፎቶ ለመምረጥ ሊንኩን የጫኑት https://t.iss.one/wubeare
የኬንያ አዲስ ፕሬዝዳንት ማን ይሆን ?

የጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዝዳንት ምርጫ ዛሬ ነሃሴ 3 እየተካሄደ ነው።

ኬንያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት አራት ዕጩዎች ቀርበዋል።

🇰🇪 ዴቪድ ሙዋሬ ፦

የኬንያ አጋኖ ፓርቲ፣ በሙያቸው ጠበቃ እንዲሁም ሰባኪ የሆኑት ዴቪድ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ያሰቡት በአውሮፓውያኑ 2013 ነበር። በኋላ ግን በውድድሩ ተሳታፊ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዘንድሮው ምርጫ አገሪቱን ለቀጣዩ አምስት ዓመት ለመምራት እየተፋለሙ ይገኛሉ።

🇰🇪 ራይላ ኦዲንጋ ፦

የአዚሚዮ ላ ኡሞጃ ጥምረት፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና አንጋፋው ፖለቲከኛ፣ አገሪቱን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ለአምስተኛ ጊዜ ሙከራቸውን እያደረጉ ነው።

🇰🇪 ዊሊያም ሩቶ ፦

የተባበሩት ዲሞክራቲክ አሊያንስ : አገሪቷን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ለሚመሩት ዊልያም ሩቶ ይህ የመጀመሪያ የፕሬዝዳንትነት ምርጫቸው ነው።

🇰🇪 ጆርጅ ዋጃኮያ ፦

የኬንያ ሩትስ ፓርቲ : ጠበቃውና ፕሮፌሰሩ ዋጃኮያ ለየት ባለ ሃሳባቸው ለፕሬዝዳንትነት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተወዳደሩ ነው።

ኬንያውያን ድምፃቸውን እየሰጡ ሲሆን የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን በአራት አካባቢዎች ላይ የሚደረጉ ምርጫዎችን አግዷል። እገዳ የተጣለው ከምርጫ ካርድ ህትመቶች ጋር በተፈጠረ ስህተት ነው ተብሏል።

ምርጫ የማይደረግባቸው አካባቢዎች ፦ ሞምባሳ እና ካካሜጋ የሚገኙባቸው ሲሆን፣ በእነዚህ ቦታዎች በቀጣይ እስኪገለጽ ድረስ ምርጫ ታግዷል።

ሌሎቹ ፖኮት ሳውዝ እና ካቺሊባ ግዛቶች ናቸው ምርጫ የማይደረግባቸው። የታቱሙት ካርዶች የያዟቸው ዕጩዎች ዝርዝርና ምስሎች የተሳሳቱ ናቸው ተብሏል።

Via BBC NEWS

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GurageZone የጉራጌ ዞን መንግስት የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ለብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት ፦ " ... የጉራጌ ዞን በክልልነት ለመዋቀር ለፌደሬሽን ም/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው። የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው። የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት…
#GurageZone

በደቡብ ክልል ያሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው በሁለት አዲስ ክልሎች ለመደራጀት በየም/ቤቶቻቸው ወስነው ውሳኔውን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ካቀረቡ ቀናት ተቆጥሯል።

በጋራ በአዲስ ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ውሳኔ አሳልፈው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄውን ካቀረቡት መካከል ግን የጉራጌ ዞን እንደሌለበት ይታወቃል።

ዞኑ ከአጎራባቾቹ ስልጤ ፣ ከምባታ ጠምባሮ ፣ ሀዲያ፣ ሀላባ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ ጋር ነበር በአንድ ክልል ይደራጃል ብሎ መንግስት አቅጣጫ አስቀምጦ የነበረው።

ነገር ግን የዞኑ ም/ቤት እስከ ዛሬ ድረስ በጉዳዩ ላይ አልተወያየም፤ አዲሱን አደረጃጀት አላፀደቀም ፤ ከዚህ በፊት ዞኑ እንደገለፀው የክልልነት ጥያቄን ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ ነው።

መንግስት በአሁን ሰዓት ዞኑን በክልል ለማደራጀት እንደሚቸገር በመግለፅ ከአጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳ ጋር ነው ክልል እንዲሆን ሀሳብ እያቅረበ መሆኑ ተሰምቷል።

የዞኑ ህዝብ ግን በክልል የመደራጀት ጥያቄው ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ መሆኑንና ለጠየቀው ህጋዊ የሆነ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው ፤ የ " ጉራጌ ክልል " አደረጃጀትም ተግባራዊ እንዲሆንለት በተለያየ መንገድ እየጠየቀ ይገኛል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ አንቂዎች ፤ የአካባቢ ነዋሪዎች መንግስት በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ እየተጠየቀ ላለው የክልልነት ጥያቄ ህጋዊ መልስ እንዲሠጥ ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ከክልል እንሁን ጥያቄ ጋር በተያያዘ በዞኑ መቀመጫ በ ' ወልቂጤ ' የስራ ማቆም አድማ መመታቱ ተሰምቷል።

በከተማይቱ ባንኮች ፣ የተለያዩ መ/ቤቶች፣ የንግድ እና የትራንስፖርት እንደቆመ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ፎቶ ፦ ጀማል ሞሀመድ

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በአሜሪካ ሚኒሶታ ፤ በ " ኢማም አል ሻቲቢ " በሚዘጋጀው የቁርዓን ንባብ ውድድር ከኢትዮጵያ ቤተሰቦች የተገኘችው ፋርቱን አብዱልቃድር ዋቆ አሸናፊ መሆኗ ተሰምቷል።

ውድድሩ 8ኛ አመታዊ ውድድር መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

ፋርቱን ፤ ውድድሩን ያሸነፈችው ሚኒሶታን ወክላ ሲሆን 20,000 ዶላር የገንዘብ ዋጋ እና 46,000 ዶላር የሚያወጣ 2022 ቶዮታ ሃይላንደር መኪና እና ዑምራ ማሸነፏን ከሀሩን ሚዲያ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

ፋርቱን አብዱልቃድር ፤ በትግል የሚታወቁት #የጄኔራል_ዋቆ_ጉቱ የልጅ ልጅ መሆኗ ታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ICRC #Tigray የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በተለያዩ ክልሎች በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል። ኮሚቴው #በትግራይ_ክልል በግጭት የተጎዱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ፦ 👉 በማዕከላዊ፣ 👉 በምስራቅ ፣ 👉 በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ዞኖች ለሚገኙ ለ20,000 አባውራዎች (120,000 ግለሰቦች) የአፈር ማዳበሪያ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ዛሬ አሳውቋል።…
#ICRC

ICRC ለተፈናቃይ አባወራዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት የተፈናቀሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች በሕይወት ለመቆየት በሰብአዊ እርዳታ ላይ ጥገኛ መሆናቸውን አመልክቷል።

በመጠለያ ካምፖች ውስጥ ያሉ ተፈናቃይ ሰዎች ደግሞ ምንም አይነት አስተማማኝ የኢኮኖሚ ምንጭ የላቸውም ሲል ገልጿል።

በዚህም ምክንያት በአማራ ክልል ፦ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ሃብሩ ወረዳ፣ ጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ 3,674 #ተፈናቃይ_አባወራዎች (22,044 ግለሰቦች) መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ደሴ

ከደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተዘርፈው ሊወጡ የነበሩ የህክምና ቁሳቁሶች ተያዙ።

ትላንት ነሀሴ 2 በግምት ከሌሊቱ 6 ሰአት ከደሴ ከተማ አጠቃላይ ስፔሻለይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ማሽን ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ።

ተሰርቆ ሊወጣ የነበረው ፦

- የላብራቶሪ ማሽን 4 ኦሎምፐስ (olomps) ማይክሮስኮፕ፣
- 1 ላቦመድ (labomed) ማይክሮስኮፕ፣
- 1 የኬሚስትሪ ማሽን(ዲያሚንሽን ማሽን ትንሿ ፕሪንተር፣
- 1 NEO-BIL የቢል ማሽን፣
- 5 አዲስ ዶግለር የበር ቁልፍና የተለያዩ የኤሌትሪክ ገመድና ቁሳቁስ ነው።

የህክምና ቁሳቁሶቹ ሰርቀው ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፍንጅ በጥበቃ ሰራተኞች የተያዙ ግለሰቦች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።

ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ አልተገለፀም።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ፤ ከአሁን በፊትም #በሆስፒታሉ_ሰራተኞች ከ6 መቶ ሺ ብር በላይ የሚገመቱ ለክሮኒክ በሽታ የሚታዘዙ መድሀኒትና ሌሎች መድሀኒቶች መዘረፉን ተነግረዋል።

ዘረፋ ያካሄዱ 3 ሰራተኞች ከስራ ተባረው በህግ እንዲጠየቁ ሲደረገ አንድ ባለሙያ ላይ ከደረጀ ዝቅ እንዲል መደረጉን ገልፀዋል።

ዶ/ር ሃይማኖት ፤ " የጥበቃ ስራውን አጠናክረን ስንቀሳቀስ የስርቆት ወንጀሉ ከውጭና ከውስጥ የተያያዘ ቁርኝት ያላቸው የሌብነት ሰንሰለት እንዳለ ተረድተናልና ህብረተሠቡ ሊያግዘንና ሊተባበረን ይገባል " ብለዋል።

መረጃውን ከደሴ ኮሚኒኬሽን ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#USAirstrike

የአሜሪካ አየር ጥቃት - በጎረቤት ሶማሊያ !

በጎረቤታችን ሶማሊያ ሂራን ክልል የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ኃይል የፀረ ሽብር ዘመቻ እያካሄደ ሲሆን ጦሩን ለመደገፍ #አሜሪካ የአየር ጥቃት መሰንዘር መጀመሯ ተገልጿል።

አሜሪካ የአየር ላይ ጥቃቱን እንድትሰነዝር የተጠየቀችው በሶማሊያ መንግስት መሆኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

በክስተቱ ንፁሀን ዜጎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም የተባለ ሲሆን አሜሪካ ለሶማሊያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

@tikvahethiopia