TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትክክለኛ ፍትህ እንፈልጋለን " ህይወታቸውን ሙሉ ደክመው ያፈሩት ንብረታቸው በአንድ ቀን ሙሉ በሙሉ ዶግ አመድ ሆኖባቸው የሰው እጅ ለማየት የተገደዱ ወገኖቻችን " ፍትህ እንፈልጋለን " እያሉ ነው። ሰሞኑን በደቡብ ክልል፤ ደቡብ ኦሞ ዞን ፤ ደቡብ አሪ ወረዳ ከዞን የመዋቅር ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሳው የፀጥታ ችግር በርካቶች ንብረታቸው ወድሞ ከገዛ ቤታቸው ተፈናቅለው በየትምህርት ቤቱ እና መንግስት…
#ደቡብ_ኦሞ

🗣 " መልሶ ማቋቋም የተባለው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እንጂ ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም አቤት የምንልበት አጥተናል " - ተፈናቃዮች

🗣 " 72 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ እየተሰራ ሲሆን እስከ ሰኔ ድረስ የወደሙ ቤቶች ለመገንባትና ነዋሪዎችን ወደቀያቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው " - አቶ ባንቄ ኩሜ

በፀጥታ ችግር ሳቢያ በደቡብ ኦሞ ዞን " አሪ ወረዳ " የተፈናቀሉ ዜጎች ችግር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አንድ ተፈናቅለው በመጠላያ ጣቢያ የሚገኙ የቶልታ ነዋሪ ፥ " ያለንበት ችግሩ ተዘርዝሮ አያልቅም " ብለዋል ። መንግስት ነገሮችን የማለሳለስ ስራ ነው የሰራው አንድም የተሰራ ስራ የለም፤ ህዝቡ ያለው ሜዳ ላይ ነው እስካሁን ድረስ ፣ ዝናብ እና ፀሃይ ይፈራረቅበታል፣ ተጨናንቆ ነው ያለው አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ በአንድ ክፍል እስከ 50 እና 60 ሰው ነው ያለው ፤ ይህ ለጤናም አስጊ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

እኚሁ ተፈናቃይ የጠየቀን አካል የለም መልሶ ማቋቋም የተባለውም ፖለቲካዊ ይዘት እንጂ የተፈናቃዮችን ችግር የሚፈታ አይደለም ፤ አቤት የምንልበትንም አጥተናል ሲሉ ገልፀዋል።

ተፈናቃዩ ፥ " ሰላሙን በትክክል አስጠብቆ ፣ ህዝቡን ወደቦታው መልሶ ማቋቋም አለበት ብለን ነው እኛ እየጮህን ያለነው። ነገር ግን የተደረገ ነገር የለም። ከወር በላይ ሆኖናል አሁን ዝም ብሎ ቦታውን በዶዘር እንደለድላለን ብሎ የአንድ ሰው ነው የሁለት ሰው ቤት እንደደለደለ ይኸው ሰላም ወርዷል በሚል የተለያየ ነገር በሚዲያ የማሰራጨት ስራ ነው እየተሰራ ያለው ይሄ የፖለቲካ ስራ ነው እየተሰራብን ያለው " ብለዋል።

አንድ ሌላ የቶልታ ተፈናቃይ መምህር ደግሞ ለስምንት አመታት ባስተማሩበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል።

ሌላ ጥቃትም ይደርስብናል ብለን ስጋት ላይ ነን ሲሉም አስረድተዋል።

"ያየን ሰው የለም" የሚሉት እኚሁ መምህር የተደረገም ድጋፍ እንደሌለ አንስተዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት መምሪያ ኃላፊ አቶ ባንቄ ኩሜ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል። ምግብ ነክ እንም ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እየቀረበ ነው ሲሉም ተፈናቃዮች የሚያነሱትን ቅሬታ ውድቅ አድርገዋል።

የተሠጠው ድጋፍ ለ1 ወር ከ15 የሚበቃ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

መልሶ ለማቋቋም ፤ 72,000,000 ብር ለማሰባሰብ እየተሰራ መሆኑን እና እስከ ሰኔ ድረስ የወደሙ ቤቶች ተመልሰው ተገንብተው ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እና ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ በበኩላቸው የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ የነበረባቸው ወረዳዎች ወደ ቀደመው ሰላማቸው ተመልሰዋል ብለዋል።

በወንጀል የተጠረጠሩ ከ1400 በላይ ሰዎች በወቅቱ ታስረው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን እና ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸውን እና መሪ ሚና የተጫወቱት ላይ ክስ ለመመስረት በሂድት ላይ ነው ብለዋል።

ለአሁን ላይ ተፈናቃዮች የማያቀርቡትን የደህንነት ስጋት በተመለከተ ፥ " አሁን ባለው ሁኔታ ጥቃት የሚያደርስ አካል አለ ወይ ብለን ስንገመግም ብዙም የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

Credit : ቪኦኤ / ጋዜጠኛ ዮናታን ዘብዲዮስ

@tikvahethiopia