TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ፅጌሬዳ_ግርማይ

ስለፅጌሬዳ ግርማይ ግድያ ጓደኞቿ ምን አሉ ?

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ከአባቷ ከአቶ ግርማይ ገ/መድን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ያበሻ ያዘዘው በወልቃይት አድ ረመጽ ከተማ በ1993 ዓ/ም ነው የተወለደችው።

የመሰናዶ ትምህርቷን በወልቃይት ጌታቸው አዘናው 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንደተከታተለች ፤ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመመደብ በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ እንደነበረች የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያሳያል።

ፅጌሬዳ ግርማይ ጥር 23 ቀን አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በምትማርበት ተቋም ተገድላለች።

ስለክስተቱ የቅርብ ጓደኞቿ ፅጌሬዳ ጥር 23 ምሽት ላይ ስልክ ተደውሎላት ከዶርም እንደወጣች ይገልፃሉ።

በስልክ ደውሎ የጠራት የገደላት ልጅ ሳይሆን የእሱም የእሷም ጓደኛ እንደሆነ እና እሱ ከጠራት በኃላ የገደላትን ልጅ እንዳገኘችው ያስረዳሉ።

በኃላም ብቻቸውን እንደነበሩ ፤ ብዙም ሳይቆ በስለት እንደወጋት ነው የታወቀው።

ወደ ነጭ ሳር ሆስፒታል ብትወሰድም ልትተርፍ አልቻለችም።

ፅጌሬዳ ግርማይ በቢለዋ አራት እና አምስት ቦታ መወጋቷን ጓደኞቿ አስረድተዋል። ፅጌሬዳና ገዳዩ የአንድ ክፍል ተማሪዎች እንደነበሩም አክለዋል።

ገዳዩ ፅጌሬዳን " እውድሻለሁ፤ አብረሽኝ ሁኚ " የሚል ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።

ልጁ በቁጥጥር ስር መዋሉ ፥ የፅጌሬዳም አስክሬን ወደ ቤተሰቦቿ መሸኘቱን ጓደኞቿ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፅጌሬዳ_ግርማይ ስለፅጌሬዳ ግርማይ ግድያ ጓደኞቿ ምን አሉ ? አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ከአባቷ ከአቶ ግርማይ ገ/መድን እና ከእናቷ ከወ/ሮ ያበሻ ያዘዘው በወልቃይት አድ ረመጽ ከተማ በ1993 ዓ/ም ነው የተወለደችው። የመሰናዶ ትምህርቷን በወልቃይት ጌታቸው አዘናው 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንደተከታተለች ፤ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመመደብ በሆቴልና…
#ፅጌሬዳ_ግርማይ

የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን ግድያ በተመለከተ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ መረጃ ሰጥቷል።

ሰኞ ዕለት ህይወቷ ያለፈው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተጠረጠረ ተማሪ ትላንት ከሰዓት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ምስክርነት የሰጡ የተጠርጣሪው #ሁለት_ጓደኞቹ የሚከተለውን ብለዋል :-

"ተማሪ ፅጌሬዳ ከተጠርጣሪ ወንጀለኛው ጋር ግንኙነት የነበራት ሲሆን በመሀል ውጪ የነበረ ጓደኛዋ ስለመጣ ግንኙነቱን ማቋረጥ እንደምትፈልግ ገልጻለታለች። በዚህም ተጠርጣሪው ደስተኛ እንዳልነበረና ዛቻና ማስፈራሪያ በጓደኞቿ በኩል ይልክላት ነበር።"

ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ከሁለቱ ጓደኞቹ በአንደኛው ስልክ በመደወል ወደ አስተዳደር ህንጻ አካባቢ እንድትመጣ አድርጓል።

በወቅቱ ስልክ ደዋዩና ሌላኛው ጓደኛው አብረውት ነበሩ። "ጉዳያችንን እኛ እንጨርሳለን እናንተ ሂዱ" ብሏቸው ብዙም ሳይቆይ በስለት እንደወጋት ጓደኞቹ ምስክርነት ሰጥተዋል።

ሟች ልቤን ብላ ስትጮህ በቅርብ ርቀት የነበሩ የግቢው ጥበቃ አባላት ደርሰው ለማምለጥ የሞከረውን ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውለውታል።

ተጠርጣሪው በሕግ ጥላ ስር ውሎ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ሲሆን ፍ/ቤት ቀጣይ ቀጠሮ እንደሰጠው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በድሩ ሂሪጎ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የሟቿ አስክሬን ትላንት ቤተሰቦቿ ወደሚገኙበት ወልቃይት ወረዳ አድ ረመጽ ከተማ መላኩንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በ20 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ተማሪ ፅጌሬዳ በዩኒቨርሲቲው የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፅጌሬዳ_ግርማይ

የአርባ ምርንጭ ዩኒቨርሲቲ እና የጋሞ ዞን ፖሊስ የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ህልፈትን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰቡ።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በድሩ ሂሪጎ " የአርባ ምንጭ አካባቢው በሰላም ግንባታ ለሀገራችን አርአያ፣ ምሳሌ የሚሆኑ አባቶች ያሉበት ከተማሪዎቻችን ጋርም በቅርበት የሚሰሩበት ነው " ብለዋል።

"አንዳንድ ግለሰቦች / እንደ ቡድን ሊገለፁ የሚችሉ አካላት የብሄር ተኮር ጥቃት እንደተፈፀመ ለማስመሰል የሚሞክሩ አሉ፤ ይሄ መታረም አለበት። " ሲሉ አስገንዝበዋል።

አቶ በድሩ ፥ " የተፈጠረው ድርጊት አሳዛኝና አሰቃቂ ነው ፤ ይሁን እንጂ ይሄ በልጁ በተፈጠረ ስሜታዊነትና ስሜቱ ባመጣበት ባልተገራ የአውሬነት ስሜት የተፈፀመ መሆኑን ማገንዘብ እንፈልጋለን " ብለዋል።

የወንጃ ድርጊቱን የፖለቲካ ይዘት ለመስጠት የሚሞክሩ እና የተደረገው ነገር ከብሄር ጋር ይገናኛል የሚሉ አካላት ተገቢ ያልሆነ መረጃ እያሰራጩ ስለሆነ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር አንተነህ አበበ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚፃፉ የሚለቀቁ ፅሁፎች ከተፈፀመው ድርጊት ጋር የሚገናኙ እንዳልሆነ በጥብቅ አስገንዝበዋል።

ኮማንደር አንተነህ ፥ " ድርጊቱን በሀገሪቱ ካለው የወቅቱ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ለማገናኘትና ግንኙነትም እንዳለው አድርገው ለማሰራጨት የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ " ያሉ ሲሆን " ይሄ ተገቢነት የሌለው ነው " ብለዋል።

" ትክክለኛው መረጃ እኛ አሁን የምንሰጠው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ያንን ልትቀበል ባለመቻሏ ተነሳስቶ ፤ አስቦ ፣ አቅዶ የፈፀመው ወንጀል ነው " ሲሉ አክለዋል።

ኮማንደር አንተነህ ያልተገባ መልዕክት የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲታቀቡ የጋሞ ዞን ፖሊስ ያሳስባል ብለዋል።

የ20 ዓመቷ ወጣት ፅጌሬዳ ግርማይ ጥር 26 ቀን 2014 ዓ/ም በዳንቫ ያተፈፀመ ሲሆን ከህልፈቷ ጋር በተገናኛ የቅርብ ጓደኛ ፣ የአርባ ምርጭ ዩኒቨርሲቲ እና የጋሞ ዞን ፖሊስ የሰጡትን መረጃ በዚህ ታገኛላችሁ 👇
https://telegra.ph/Tsegereda-Girmay-02-03