TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተሳፋሪ ዘመዶች በጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ‼️

ET302 ከጠዋቱ 4፡30 ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን የዘመድ ወዳጆቻቸውን መድረስ ሲጠባበቁ የነበሩ የመንገደኛ ዘመዶች በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ #ሃዘን ላይ ይገኛሉ።

የኬንያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አጋጣሚው እጅግ ከባድ ቢሆንም አደጋውን በሚመለከት በቀዳሚነት መረጃ መስጠት ያለበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመሆኑ እነዚህ ሰዎች #በትእግስት እንዲጠባበቁ አስታውቋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጄምስ ዋይናና የኬንያ መንግስት አደጋውን ተከትሎ ለሚመለከታቸው የኢትዮጵያ አካላት ድጋፍ እያደረገ እንደሆነና ለዚሁም ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ማእከል ማቋቋሙን ገልፀዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘመዶቻቸው የአውሮፕላኑ መንገደኛ ለነበሩ ሰዎች ቤተሰብና ወዳጅ መረጃ ይሰጡ ዘንድ የነፃ ስልክ መስመር (+254)733666066 አድርጓል።

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድም ተሳፋሪዎችን የሚመለከት መረጃ መስጠት የሚቻልባቸውን የስልክ መስመሮች ቀደም ብሎ ይፋ አድርጎ ነበር።

#BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia