TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' ቤቲንግ ' ሊታገድ ነው ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ መሆኑን የሚገልፁ በትክክል ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ሲሰራጩ ተስተውሏል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን እየተሰራጩ ያሉት መልዕክቶች ፍፁም ስህተት ናቸው ብሏል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ።

" ' አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው ' በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት መሆኑን እንገልፃለን " ያለው አስተዳደሩ " የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ  ሎተሪን   በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ከ ' ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ / ' ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር #እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ  ፤ ከታዲጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ከሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች አንጻር ነው ዘርፉ #ሊታገድ ይገባል በሚል እየሰራ እንደሆነ አሳውቆ የነበረው።

የስፖርት ውርርድ ' ቁማር ነው ' ብሎ የሚያምነው ይኸው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ፤ በተለያየ ጊዜ ሰርቻቸዋለሁ ባላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ቤቲንግ ለወጣቱና ለታዳጊው ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ መሆኑን አመላካች መሆኑን ፤ ቁማር ታዳጊዎችን ይሁን አዋቂ ሰዎችን ወዳልተፈለገ መንገድ ሊወስድ የሚችል ማህበራዊ ቀውስ እንደሆነና ማንኛውም ሰው ሰርቶ የመለወጥ እሳቤውን የሚያቀጭጭ፣ ቤተሰብን ጭምር ወደ መበተን ሊያደርስ የሚችል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝቦ ነበር።

ወጣቶች እና ታዲጊዎች ለቤቲንግ ውርርድ ሲሉ ያላቸውን ነገር በሙሉ እስከማውጣት ይደርሳሉ ፤ ወጣቶች ስራን ከመስራት ይልቅ በአቋራጭ መክበር እንዲያስቡ በማድረግ ምርት እና ምርታማነትን የሚቀንስ ተግባር ነው የሚልው መ/ቤቱ ቤቲንግ እንዲታገድ ፍቃድ ለሚሰጡት የንግድ ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተቋማት አስፈላጊውን የግንዛቤ እና የማሳወቅ ስራ ቢሰራም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ባለማድረጋቸው ለውሳኔው መዘግየት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጾ ነበር።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤቲንግ እንዲታገድ ብርቱ እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩን ካሳወቀ ወራት ቢቆጠርም እስካሁን በጉዳዩ ላይ አዲስ ነገር የለም።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን በ ' ቤቲንግ ' ኮሚሽን (15%) በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያስገኛል (ለሀገር) ፣ በርካታ ሰው በተለይ ሴቶችን ቀጥሯል ፣ ለማህበራዊ ጉዳይ ከገቢው ያውላል ፣ ቤት ይከራያል ፣ ገንዘብ ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ያደርጋል ... ይህ ሁሉ ጥቅሞቹ ናቸው ብሎ ያምናል።

" ቤቲንግ " አትራፊ እንደሆነ የሚገልጸው አስተዳደሩ " ጨዋታ " እንጂ " ቁማር " አይደለም ብሎ ያምናል። በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎችን አውጥቶ እየሰራ እንደሆነና " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ፤ ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ባይ ነው።

ማህበራዊ ቀውስ ያመጣ እንደሆነ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት አጥንተው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል በሚል ከሚታገድ በህግ እንዲመራና የማይገባቸው ሰዎች እንዳይጫወቱ ክትትል  ቢደረግ የተሻለ መሆኑ ታምኖበት እየተሰራ እንደሆነ በከወራት በፊት ገልጿል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " ከጥር 3 ጀምሮ ቤቲንግ ይታገዳል " የሚሉ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ የነበረ ሲሆን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ ፍፁም የተሳሳተ ነው ፤ ማንኛውም ቤቲንግ / የስፖርት ውርርድ ነክ መረጃ የሚገኘው ከኔው ነው እንጂ ከሌላ አይደለም ሲል አስገንዝቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
" 3,241 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም መግለጫው በ " ህገ ወጥ  መንገድ " ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸእ 3 ሺህ 241 የስፖርት ቤቲንግ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

ወደ እርምጃ የተገባው የቤቲንግ ጨዋታ ፤ በከተማው አስተዳደር ላይ እንዲሁም ቀን በቀን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ እየፈጠረ ያለውን አሳሳቢ ችግር በመረዳት ነው ብሏል።
 
ቢሮው ለማሸግ ምክንያት ናቸው ያላቸው ዝርዝር ጉዳዮች ምንድናቸው ?

- ከስፖርት መጫወቻነቱ ባለፈ ሀገር  ተረካቢ ትውልድን እያጠፍ በመሆኑ፤
- ከፍተኛ የወንጀል ማስፍፊያ እየሆነ በመምጣቱ
-  የከተማውን ወጣት ግዜውን አላግባብ በስፍራው እያሳለፈ በመምጣቱ፤
- ከተፈቀደላቸው ፈቃድ ዉጪ እየሰሩ በመምጣታቸው
- የሰዉ ልጅ ህይወት አላግባብ እየጠፋ በመምጣቱ፤
- ተማሪዎችም ትምህርታቸውን ትተዉ በቦታው እየተገኙ በተገቢው መንገድም እንዳይማሩ በማድረጉ ፤
- የመማር ማስተማሩን ሂደት እያወከ በመምጣቱ የሚሉት ተነስተዋል።

ቢሮው በመግለጫው.  ከትምህርት ተቋም 200 ራዲየስ ርቀት ላይ መገኝት እንዱሁም እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በቦታው ላይ መገኝት እንደማይገባቸው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህግ እንደሚደነግግ አስገንዝቧል።

እርምጃው ፦
° የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣
° #የብሔራዊ_ሎተሪ_አስተዳደር
° የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን፣
° የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣናት በቤቶቹ ላይ የልየታ ምልከታ ካደረጉ በኃላ የተወሰደ ነው ተብሏል።

ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ምንም እንኳን በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ እየሰሩ ነው በተባሉ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ቢወሰድም በአጠቃላይ የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ኢትዮጵያ ውስጥ #አልታገደም

በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ ነው የሚሉ ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ከተሰራጩ በኃላ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ ፍፁም ስህተት እንደሆነና የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አሳውቆ ነበር።

ከዚህ ቀደም ከ " ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ " ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ #እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

መ/ቤቱ " ቤቲንግ " በወጣቱና ለታዳጊው ላይ ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ ' ቁማር ነው ' ብሎ የሚያምን ሲሆን  የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን " ቤቲንግ " አትራፊ እንደሆነ " ጨዋታ " እንጂ " ቁማር " ብሎ እንደማይወስደው ፣ በዚህ ዘርፍ በርካታ ሰው ተቀጥሮ እንደሚሰራ ከዚህ ቀደም ገልጿል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር " ቤቲንግ " በስርዓት እንዲመራ መመሪያዎች ወጥቶ እየተሰራበት እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ፤ ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ባይ ነው።

ማህበራዊ ቀውስ ያመጣ እንደሆነ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት አጥንተው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል በሚል ከሚታገድ በህግ እንዲመራና የማይገባቸው ሰዎች እንዳይጫወቱ ክትትል ቢደረግ የተሻለ መሆኑ ታምኖበት እየተሰራ እንደሆነ በከወራት በፊት ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ አስተያየት ካላችሁ በ @Birlikethiopia ገብታችሁ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

- " ችግሩ የተከሰተው አንድ ሂሳብ ማስታረቅ ቅልጥፍና እንዲያመጣ ታስቦ የተሰራ የሲስተም ማሻሻያ ሲተገበር ስህተት በመፈጠሩ ነው። የተፈጠረው ስህተት ለሌቦች ቀዳዳ ከፍቶ ነበር። "

- " የሲስተም ማሻሻያው የተተገበረው አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ነበር። ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ችግር እንዳለ ሊለይ ችሏል። ይህን ተከትሎም አንዳንድ የተጠረጠሩ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ይህም ሆኖ ሙሉ በሙሉ ችግሩ ስላልቆመ ሁሉም የዲጂታል ባንክ ስርዓቶች እንዲቋረጡ ተደርጎ ነበር። "

- " ባንኩ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተካሂዷን። ሌሊቱን ሙሉ ግብይት ሲፈጸምባቸው የነበረባቸው የባንክ ሂሳቦች በሙሉ እስኪጣራ ድረስ #እንዲታገድ ተደርጓል። "

- " በቀጣይ ከፍተኛ እና ያልተገባ ግብይት የፈጸሙ አካላትን እየለየን ለህግ የማቅረብ ስራ ይሰራል። "

- " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በወንጀሉ ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸው አሳዝኖናል። በየአካባቢው ያሉ የዲስትሪክት ኃፊዎች በየአካባው ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ #እንዲመልሱ እየተደረገ ነው። "

- " ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው። የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ እና ያስከተለውን ጉዳትም ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል። "

- " ባንኩ ላይ የደረሰው ጉዳት ባንኩ ካለው ሀበት እና አቅም አንጻር የጎላ ተጽእኖ የለውም፤ ከደንበኞች ሂሳብ ጋርም አይገናኝም። " #አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ " ፍርድ ቤት እንተያይ " ብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው " #ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ #እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

" ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ #እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል።

አሁን በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " ሙሉ በሙሉ የመታገዱ ነገር #እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ፣ እስራኤል እና ታይዋን የቀረበው የ95 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ጥቅል ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን…
#Update

የአሜሪካ ፕረዚደንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ሲባል የሀገሪቱን ፍልሰተኞች ሕግ አጥብቀዋል።

ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ ባለሥልጣናት በሜክሲኮ በኩል ድንበር አቋርጠው የገቡ ስደተኞችን / ጥገኝነት ጠያቂዎችን በቀጥታ በኃይል ወይም በግዳጅ  እንዲመልሷቸው ሥልጣን የሚሰጥ ነው።

ጉዳያቸው የሚመዘገቡ ሰዎች ዕለታዊ ኮታ ከተሟላ የተቀሩት ከአሜሪካ በኃይል እንዲወጡ ይደረጋሉ።

ከዚህ ባለፈ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውጪ ዜጋ ወደ አገር እንዳይገባ " #እንዲታገድ " የሚል ትዕዛዝ ፕሬዜዳንቱ አስተላልፈዋል።

#ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪቃውያን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ እንደሚሻገሩ ይታወቃል።

አሜሪካ የፍልሰተኞችን ፍሰት ለመግታት በሚል ከሜክሲኮ የሚያዋስናትን ድንበር ከማጠር ጀምሮ በርካታ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ይህ የአሁኑ የፕሬዜዳንት ባይደን ውሳኔ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ለሚመለከተው የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ቀርቦ ሳይታይ #በቀጥታ እንዲባረሩ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፤ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ግን ሕጉ የስደተኞችን መሰረታዊ መብት ይጥሳል ሲል ተቃውሟል።

መረጃው የጀርመን ዜና አገልግሎት፣ የዶቼ ቨለ እና ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia