TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትኩረት በሲዳማ ዞን ለሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች!

📣ትኩረት #ይርጋለም #አለታ_ወንዶ #ጩኮ #ለኩ #ሀገረ_ሰላም በሚባሉ ከተሞች የሚገኙ ዜጎች አሁንም ያለው ሁኔታና አለመረጋጋት እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። በአንዳንድ ከተሞች ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ጠፍቷል። ዝርፊያ ተፈፅሟል፤ ሰዎች ህይወታቸውን ሙሉ ለፍተው ያፈሩት ንብረት ወድሞባቸዋል። መልዕክታቸውን ለTIKVAH-ETH በስልክ #ደውለው የተናገሩት የየከተሞቹ ነዋሪዎች የሚመለከተው አካል በሙሉ ከዚህ የከፋ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ሁኔታዎችን ተቆጣጥሮ #እንዲያረጋጋ ተማፅነዋል። ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ አስፈሪ ነው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሀገር ሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል። የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን...ሌሎችም ለሀገር እና ወገን ተቆርቋሪዎች ወጣቱን በመምከር፣ በማረጋጋት ከጥፋት በመመለስ በኩል ሀገራዊ #ሃላፊነታቸው ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል...

ሀዋሳ ከተማ #የጦርነት_አውድማ እንደሆነች ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። በዚህ ፈታኝ ወቅት ሀገሪቱን ወደማያባራ ግጭት ውስጥ እድትገባ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው የፌስቡክ አርበኞች በመኖራቸው የምንሰማቸውን መረጃዎች #በደንብ ልናጣራ እና ልንመረምራቸው ይገባል።


🚫📱💻በሲዳማ ዞን እና ዙሪያው በሚገኙ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው። ከየከተሞቹ ነዋሪዎች በስልክ የሚደርሱኝን የተጣሩ መረጃዎች ወደናተ የማደርስ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia