TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደባርቅ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ችሎ ሊቀ ጳጳስ ተሰይሞለታል፤ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ትላንት ደባርቅ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናን፣ የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ መኮንኖች ናቸው ለሊቀ ጳጳሱ አቀባበል ያደረጉላቸው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahehiopia
የዛሬ የህዳር 10/2012 ዓ/ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልት እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰባሰበ መረጃ👇
https://telegra.ph/ETH-11-20-4

(TIKVAH-ETHIOPIA)

#ድሬዳዋ #ሀረማያ #ወልዲያ #መቱ #ASTU
#መደወላቡ #ባህርዳር #ደባርቅ #ደብረታቦር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደባርቅ

° “ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ተበራክተዋል ” - የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች

° “ ከጥር ወዲህ ወደ 13 ሰዎች ራሳቸውን #መርዘው ሞተዋል ” - ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል

በአማራ ክልል ባደባርቅ ከተማ ፣ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች እየተበራከቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ በሰጡት ቃል፣ “ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ተበራክተዋል። የሟቾች ቁጥር በተለይ ከፋሲካ በዓል ወዲህ እየጨመረ ነው ” ብለዋል።

አንድ ሁነቱን በቅርበት የሚከታተሉ ታማኝ ምንጭ ፤ በቤተክርስቲያን አንድ የሃይማኖት አባት “ የሟች ቁጥር 63 መድረሱን ” ሲገልጹ መስማታቸውን ተናግረዋል።

እውነትም ሰዎች ራሳቸውን እያጠፉ ነው ወይ ? ተብሎ የተጠየቀው የከተማው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት፣ “ ራስን የማጥፋት አደጋዎች አሉ ፤ በተደጋጋሚ እየታዬ ያሉ። ኬዙ ግን ወደ ሆስፒታል ነው እየሄደ ያለው ” ብሏል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የከተማው አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አለአምላክ ተስፋ በበኩላቸው፣ “ አዎ ችግሩ አለ። በጣም ብዙ ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩ አሉ ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ ከ13 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን መርዘው እኛ ማገዝ በማንችለው ስለመጡ የሞቱ አሉ ” ብለው፣ ሟቾቹም ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ በማድረጋቸው ምክር ሲሰጣቸው ከነበሩ 59 ሰዎች መካከል መሆናቸውን አስረድተዋል።

“ ከጥር ወዲህ ወደ 13 ሰዎች ራሳቸውን መርዘው ሞተዋል ” ያሉት ኃላፊው፣ ሰዎቹ ለድርጊቱ የሚገፋቸው  የኢኮኖሚ መቃወስ ፣ ቤተሰብ #እንደሞተባቸው ሲሰሙ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዋናነት ግን ምክንያቱ #በጥናት መረጋገጥ አለበት ብለዋል።

ይህን መጥፎ ውሳኔ እየፈጸሙ ያሉት በተለይ ወጣቶች እንደሆኑ አስረድተው፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia