TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Attention😷

በአንድ ቀን 2,097 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,171 የላብራቶሪ ምርመራ ነው 2,097 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓት የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ትላንት 1,336 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አጠቃላይ 196,621 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 2,769 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 152,508 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 769 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia😷

በአንድ ቀን 2,142 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 8,665 የላብራቶሪ ምርመራ ነው 2,142 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓት የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ትላንት 728 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አጠቃላይ 198,794 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 2,784 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 153,236 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 780 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Attention😷

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ200 ሺህ አለፉ።

ባለፉት 24 ሰዓታ ከተደረገው 7,250 የላብራቶሪ ምርመራ 1,769 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ወረርሽኙ ወደ ሀገራችን ከገባ ጊዜ አንስቶ ቫይረሱ የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎች 200,563 ደርሰዋል።

በ24 ሰዓት ውስጥ የ17 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 2,801 ደርሷል።

ትላንት 1,087 ሰዎች አገግመዋል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየው 805 ሰዎች በፀና ተመውብናል።

#Tikvah #Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,840 የላብራቶሪ ምርመራ 1,982 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 867 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 202,545 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,825 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 155,190 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 795 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

#Purpose #Tikvah

- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 341 የላብራቶሪ ምርመራ 39 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 56 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓት ከተደረገው 40 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 87 የላብራቶሪ ምርመራ 54 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 197 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 3 አገግመዋል።

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 105 የላብራቶሪ ምርመራ 40 ሰዎች ላይ ቫይረዱ ተገኝቷል ፤ 16 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 809 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 244 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

* ያልተካተቱ ሪፖርቶች ይፋ የሚደረጉ ከሆነ ዘግየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ።

@tikvahethiopia
የክልል የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

#Purpose #Tikvah

- በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 56 የላብራቶሪ ምርመራ 32 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 7 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓት ከተደረገው 58 የላብራቶሪ ምርመራ 18 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል፤ 18 ሰዎች አገግመዋል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 527 የላብራቶሪ ምርመራ 133 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 5 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 12 አገግመዋል።

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 44 የላብራቶሪ ምርመራ 12 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ፤ 17 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 539 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 138 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

- ሲደማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 264 የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ፤ 5 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 66 ሰዎች አገግመዋል።

* ያልተካተቱ ሪፖርቶች ይፋ የሚደረጉ ከሆነ ዘግየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ።

@tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

#Purpose #Tikvah

- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 732 የላብራቶሪ ምርመራ 63 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል ፤ 55 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓታት ከተደረገው 17 የላብራቶሪ ምርመራ 7 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 181 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 339 የላብራቶሪ ምርመራ 79 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል፤ 8 አገግመዋል።

- አፋር ክልል ከተደረገው 156 የላብራቶሪ ምርመራ መካከል 17 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጣል

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 130 የላብራቶሪ ምርመራ 23 ሰዎች ላይ ቫይረዱ ተገኝቷል ፤ 14 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 897 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 264 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 5 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- ሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 189 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 92 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 6 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 78 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል ፤ 103 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓታት ከተደረገው 31 የላብራቶሪ ምርመራ 18 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 168 የላብራቶሪ ምርመራ 95 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 1 ሰው አገግሟል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 246 የላብራቶሪ ምርመራ 83 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ከ83ቱ 68ቱ ከባህር ዳር ናቸው። በ24 ሰዓት 1 ሰው ህይወቱ አልፏል፤ 11 አገግመዋል።

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 170 የላብራቶሪ ምርመራ 52 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ፤ 23 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 805 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 166 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- ሃረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 80 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 37 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- ሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 160 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 63 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

* ያልተካተቱ ሪፖርቶች ይፋ የሚደረጉ ከሆነ ዘግየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ።

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦ - በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 78 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል ፤ 103 ሰዎች አገግመዋል። - በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓታት ከተደረገው 31 የላብራቶሪ ምርመራ 18 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። - በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 168 የላብራቶሪ ምርመራ…
የኮቪድ-19 የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ከ1 ሺህ አለፈ።

የዛሬ የኮቪድ-19 ዕለታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው አሁን ላይ 1,031 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት 33 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,878 የላብራቶሪ ምርመራ 2,149 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,288 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 236,554 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,285 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 175,879 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 22 ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ለ @tikvahuniversity እንዳሳወቀው በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠኛቸውን ተማሪዎቹን ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ/ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ 3ኛ ዲግሪ በመደበኛ እና የማታ መርሀ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አህመድ መሀመድ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ትምህርት በመጠናቀቁ ነባር ተማሪዎች (ከተመራቂዎች በስተቀር) ሰኔ 11 እና 12/2013 ዓ.ም እረፍት እንደሚወጡ ኃላፊው ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 25 እስከ 30/2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

#CARD #TIKVAH

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ! ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል። ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። አሁን ላይ 4ተኛ…
#UPDATE

ስቴም ፓወር ከቪዛ እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት 4ኛ ዙር በማጠናቀቅ 240 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስቴም ፓወር በቀጣይ አምስተኛ ዙር ሰልጣኞችን መዝገባ በማከናወን ሥልጠናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ የፊታችን ሰኞ ነሀሴ 16 ሥልጠናው መሰጠት ይጀምራል። በኦላይን ለመሰልጠን ለተመዘገቡም ስለጠናውን እየተሰጠ ይገኛል።

ከ4ኛው ዙር የተመረጡ ምርጥ 4 ፕሮጀክቶች፦

1. ግብርና እና ምግብ ዘርፍ፦

- ዮፍታሔ ሳሙኤል - Mushroom Agro-processing

- ​​ስጦታው አበራ - Punt Flour from Gipto

2. አገልግሎት ዘርፍ፦

- Wujo Digital Iqub

3. ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ:

- መኮንን አስማረ - Agricultural Chemical Spray & Aerial Mapping Drone

በልዩ ዘርፍ፦ ዶ/ር ትዝታ አለሙ - Biruh Hiwot Mental Health Consultancy

#STEMpower #VISA #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል።

እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

- በ2014 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ፦

• ወደ መንግሥት ተቋማት ተመድበው የሬሜዲያል ትምህርት ከተከታተሉት 105,00 ተማሪዎች 63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።

• በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው  ከተፈተኑት ውስጥ 44,500 ተማሪዎች 27,587 ተማሪዎች አልፈዋል።

በአጠቃላይ ወደ 145,000 ገደማ ተማሪዎች ሬሜዲያል ገብተው በዛው በተቋማቸው ከ30% እንዲሁም ከማዕከል 70% ተፈትነው ከ50% እና በላይ አምጥተው ያለፉት 90,620 ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች 27,267 ገደማ ናቸው። በቀጥታ ፌሽማን / አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በአጠቃላይ በ2014 ዓ/ም ተፈትነው ሬሜዲያል ያለፉና በ2015 ዓ/ም 50 በመቶ አምትጥተው በቀጥታ ያለፉትን ጨምሮ 117,887 ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። (90,620 ከሬሜዲያል፤ 27,267 ከ2015 ዓ/ም አላፊዎች)

- ዘንድሮ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡት 191, 509 ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች ናቸው፤ እነዚህ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል።

#MoE #TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል። እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - በ2014 ዓ/ም…
#MoE

" አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል "  - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፤ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በአግባቡ እንደሚሰራበት አመልክተዋል።

" በምንም አይነትና መስፈርት አግባብ የሌለውና አድሎ ላይ የተመሰረተ ምደባ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እያንዳንዱ ተማሪ በጠየቀው በችሎታው ፣ በሚገባው ቦታ እንዲመደብ እናደርጋል " ያሉት ሚኒስትሩ " አንድና ብቸኛው ከዛ የምንወጣበት አስቸኳይ የሆነና ቅርብ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የህክምና ጉዳይ ሲኖር ነው " ብለዋል።

" የህክምና ኬዞችንም ስንመለከት ከዶክተር ወረቀት ማምጣት ብቻ ሳይሆን በቦርድ ደረጃ ተነጋግረውበት ያ የህክምና ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመማር የማያስችል ነው፤ ለህይወቱ/ቷ አስቸጋሪ ነገር ያመጣል ከተባለ ብቻና ብቻ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፤ " ለአንድ የመንግሥት ባለስልጣን ፣ አንድ የምክር ቤት አባል፣ አንድ ዝም ብሎ ሃብታም ነኝ ብሎ ለሚያስብ ሰው ከሚገባው ውጭ ለልጁ የሚሰጥ ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

ከምደባ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ጥያቄዎች እየተጠየቁ መሆኑን ያልደበቁት ፕ/ር ብርሃኑ " ስልኮች ይደወላሉ ነገር ግን የምንሰጠው መልስ አንድ ነው ፤ ' ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው። በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው ከዛ ውጭ ባለ ሌላ መስፈርት ማንንም እድል አንሰጥም ' የሚል ነው " ብለዋል።

" ከዚህ ውጭ የተሰራና የሚሰራ ስራ ካለ አሳዩን፤ ንገሩን እናስተካክላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ለምደባ በሚል ጉዳይ እሳቸውም ጋር የሚመጡ እንዳሉ ገልጸው " ለሁሉም የምለው አትሞክሩ፣ ባትደውሉ ነው የሚሻለው embarrassing ይሆናል ፤ ትክክለኛ ጥያቄ አለን ካላችሁ በትክክለኛው ሂደት እለፉ ከዛ ውጭ ግን የሚመጣ የአቋራጭ መንገድ የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

#MoE #Tikvah_Ethiopia

@tikvahethiopia