TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ እንደሻው ጣሰው‼️

አቶ #እንደሻው_ጣሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። አቶ #ዘይኑ_ጀማል የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት።

አቶ እንደሻው ጣሰው ማናቸው??

ከ1983 ጀምሮ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከመምህርነት እስከ ክፍለ ጦር አመራርነት በትምህርቱ ዘርፍ እስከ 1992 ድረስ አገልግለዋል።

ከመከላከያ በኋላ በአዲስ አበባ የተለያዪ የሃላፊነት ቦታዎች ከወረዳ ጀምሮ እስከ ከተማ ድረስ በትጋት የህዝብንና የመንግስትን ሃላፊነት ሲወጡ የቆዪ ሲሆን አቶ እንደሻው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዴሞክራሲ ግንባታ
ማስተባበሪያ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባው የህዝብ ግንኙነት አማካሪ እና የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሰሩባቸው ቦታዎች ውጤታማ መሆናቸውን ያስመሰከሩ ሰው ናቸው።

አቶ እንደሻው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከሐገር ውጭ ተከታትለው በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ምንጭ፦ EPRDF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቢሾፍቱ🔝

የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላት በወቅታዊ ሃገራዊ የጸጥታና የለውጥ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት የጋራ ምክክር የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚልና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀነራል #እንደሻው_ጣሰው በተገኙበት ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ተጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...እንኳን በአገር ውስጥ ያለ ይቅርና በውጭ አገር #በወንጀል የተጠረጠረ ካለ ይዘን እናቀርባለን"~ጄነራል #እንደሻው_ጣሰው
.
.
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እስካሁን ድረስ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦች ቢዘገይም ነፃ እንደማይሆኑ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንደሻው_ጣሰው ሐሙስ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በኮሚሽኑ መሥሪያ ቤት በሰጡት መግለጫ፣ የእስር ትዕዛዝ ለወጣባቸው ግለሰቦች ትዕዛዙን ለማድረስ ሲኬድ ያጋጠሙ ችግሮች እንደነበሩ በመግለጽ፣ በእንደዚህ ዓይነት ወቅት መታኮስ አስፈላጊ ስላልነበር የተለያዩ አማራጮች ላይ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹አንዳንድ ጉዳዮች በመደበኛ የፖሊስ ሥራዎች ብቻ የሚፈቱ አይደሉም፡፡ የተለያዩ ቦታዎች ሔደው #የተደበቁ ሰዎች አሉ፡፡ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው በኋላም የእስር ማዘዣውን ቦታው ድረስ ሄዶ ለመስጠት ሲሞከር ያጋጠሙ #እንቅፋቶች አሉ፡፡ በዚህ ወቅት አትታኮስም፡፡ ሁኔታው አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ በጥሞና እንዲታይ ይደረጋል፡፡ ይኼ #ለሰላም_ሲባል ነው፡፡ ይኼ የሚደረገው አጠቃላይ ነገር እንዳይበላሽና እንዳይደፈርስ ሲባል ነው፡፡ ይኼ ማለት ግን ሄዶ ሄዶ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ሰዎች #ነፃ ይወጣሉ ማለት አይደለም፡፡ እንኳን በአገር ውስጥ ያለ ይቅርና በውጭ አገር በወንጀል የተጠረጠረ ካለ ይዘን እናቀርባለን፤›› ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ይኼንንም ለማስፈጸም ከተለያዩ ክልሎች ጋር አስተዳደራዊ ውይይቶች እንደተደረጉ በማስታወቅ፣ ‹‹ጉዳዮቹ ጊዜ ተሰጥቷቸው የክልል መንግሥታትም የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ይደረጋል፤›› ብለዋል፡፡

ይሁንና በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ይዘው የሚያስረክቡ ክልሎች እንዳሉም ያወሱት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፣ በተቃራኒው የሚደብቅ፣ የሚሸሽግና አካባቢዬ ላይ ተጠርጣሪው የለም ብሎ የሚያብር ሰው መልካም ተሞክሮ እንዳልሆነ፣ ብሎም የተጀመረውን ለውጥ የሚያናጋና የሚያበላሽ እንዲሁም የወንጀል መከላከል ሥራ ላይም ጥላ የሚያጠላ ጉዳይ ስለሆነ #በሚታረምበት መንገድ #ይታረማል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢትዮጵያ መንግስት #ግድያውን አጣርቶ ሊያሳውቀን ይገባል፤ለህዝብ ይፋ ያድርግ" --ኮነሬል ፅጌ አለማየሁ
.
.
የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሐይሎች ኢታማጆር ሹም ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች በጀነራሉ ግድያ ዙርያ የፍትህ ጉዳይ የዘገየ ሆንዋል ሲሉ ቅሬታቸው አሰሙ፡፡ የጀነራሉ ሚስት ኮነሬል ፅጌ አለማየሁ "የኢትዮጵያ መንግስት ግድያው አጣርቶ ሊያሳውቀን ይገባል፣ ለህዝብ ይፋ ያድርግ" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር #እንደሻው_ጣሰው በበኩላቸው ምርመራው ሂደት ላይ መሆኑ ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ/DW/ተናግረዋል፡፡ የጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ሰማንያኛ ቀን ዝክር ትላንት ሲካሄድ በተቀበሩበት ቦታ ለጀነራል ሰዓረ ሐወልት ቆሞላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጀማሪ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳም እንዲሁ የሰኔ 15ቱ ገድያ የምርመራ ሂደት ለህዝብ መገለፅ አለበት ብለዋል፡፡ 

Via DW/የጀርመን ራድዮ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia