TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰኔ_15 #ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ለተፈጠረውን ችግር የፀጥታ ተቋማት መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት አለመስጠታቸው እንደሆነ አመለከተ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በጋራ የተስማማባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አቅርቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተፈጠረውን ችግር የተመለከተ ጉዳይ አቅርቧል፡፡ የጥፋት መንስኤው የፀጥታ ተቋማት አመራሮች መደማመጥ አለመቻል እና ወጥ የሆነ የአመራር ሂደት ባለመኖሩ መሆኑን ለምክር ቤት አባላቱ ግልጽ አድርጓል፡፡

በክልሉ መንግሥት የሠላም እና ደኅንነት ተቋም ላይ ችግሮች ከመከስቱ በፊት የፖለቲካ አመራሩ አስቀድሞ ዋነኛ መንስኤዎችን እየለዬ መፍታት ባለመቻሉ የተከሰተ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ሰኔ 15/2011ዓ.ም የተፈፀመው ድርጊት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት በመቆጣጠር በወቅቱ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከፍተኛ መሪዎችን በመክበብ ግድያ መፈጸሙ፤ በቡድን መሳሪያ ጭምር በመጠቀም ስልጣን ለመያዝ የተፈፀመ መሆኑን ነው ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው፡፡ የክልሉ ሕዝብ፣ የክልሉ እና የፌዴራል ፀጥታ አካላት ችግሩን ለመፍታት ባስተዋይነት ለወሰዱት ፈጣን እርምጃ እና መሰዋዕትነት ለከፈሉት ወዳጅ ዘመዶቻቸው የክልሉ ምክር ቤት መፅናናትን እየተመኘ በማንኛውም ወቅት ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጧል፡፡

አሁንም ቢሆን በወቅቱ የተፈጸመውን ድርጊት ለመሸፋፈን መሞከር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል፡፡

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/AM-07-23

@tikvahethiopia