TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል። ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ…
#Update

በህይወት ያለን ሰው ያቃጠሉት ግለሰቦች ምን ተደረጉ ?

• ካቃጠሉት ውስጥ እስካሁን አራት የሚደርሱ አልተያዙም።

• ወንጀሉን ከፈፀሙት ውስጥ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከድተው ጠፍተዋል፤ 2 የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ለህግ እንዲሰጡ ለክልሉ ፖሊስ አመራሮች ተጠይቋል።

• 3 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው (ሁለት የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት አንድ ሲቪል) ።

የፍትህ ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት በማድረግ ወንጀል እየፈፀሙ ያሉ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራው ነው ብሏል።

በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ፥ ውሳኔ ባገኙ ጉዳዮችና በምርመራ ላይ ስላሉ ጉዳዮች ለሚዲያ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሰውን ልጅ ከእነ ነፍሱ ሲያቃጥሉ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል እስካሁን ድረስ ያልተያዙ መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል።

የሰውን ልጅ ሲያቃጥሉ ከነበሩት መካከል የፀጥታ ኃይሎች እንደነበሩ የሚታወስ ነው ፤ ከነዚህ ውስጥ በወንጀሉ የተሳተፉ 3 ሰዎች (2 የደቡብ ልዩ ኃይል አባላት እና 1 ሲቪል) በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገልፀዋል።

አክለውም ፤ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማንነታቸው ቢለይም ወንጀሉን ከፈፀሙ በኃላ ከሰራዊቱ ከድተው በመጥፋታቸው እነሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፌዴራል ፖሊስ ሙከራ እያደረገ መሆኑን ፤ ሁለት የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በወንጀሉ ላይ ስለመሳተፋቸው በግልፅ በምስል ማስረጃ ተረጋግጦ ማንነታቸው ተለይቶ ለህግ አካላት እንዲሰጡ የክልሉ የፖሊስ አመራሮች ተጠይቀዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ - https://telegra.ph/ETH-06-24-2

@tikvahethiopia
" ህግ ይከበር ፤ ፍትህ ይሰጠን "

ለማስፋፊያ ስራ ተብሎ #ህግን_ባልተከተለ መልኩ ቤታችን ፈረሰብን ያሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

ያሉበት ቦታ ለማስፋፊያ ስራ ይፈለጋል የተባሉ ዜጎች ለማስፋፊያ አንደሚፈለግ ያወቁት ሰኔ 29/2013 ዓ/ም አንደሆነ ከዛ በፊት ስለጉዳዩ ምንም እንደማያቁ / እንዳልተነገራቸው ፤ ጉዳዩን የሚያውቁት ከወረዳው ጀምሮ እስከ መሬት ማናጅመት ድረስ ያሉ አካላቶች እንደነበሩ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ህግን ሳይከተል መኖሪያቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ክረምት ወቅት ዝናብ እየወረደባቸው ውጭ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ያንብቡ ⬇️
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-25
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ_አበባ_፤_ኮሪያ_ሆስፒታል_አካባቢ_ያሉ_ቤቶች_ማስረጃ.pdf
ቪድዮ ፦ በአዲስ አበባ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ " ህግን ባልተከተለ መልኩ ፤ ፍርድ ቤት ለእኛ ፈርዶልን ቤታችን ፈረሰብን " ያሉ ወገኖች ፍትህ ይሰጠን በማለት ሲጠይቁ።

የ80 ዓመት እድሜ ያለቸው አዛውንት ፦

" ... ለማን አቤት ይባላል ? ለማን አቤት ልበል ? 60 ዓመት የኖርኩበትን ቦታዬን ፣ ቤቴን መንግስት ፈርዶልኝ ፣ አርብ ተፈርዶልኝ ሰኞ ውሳኔ ልቀበል ቅዳሜ ለሊት መጥተው ቤቴን አፈረሱብኝ፣ ንብረቴን አወደሙብኝ።

ልጆቼም ተበተኑ ፣ ፀሃይ እና ዝናብ እየተፈራረቀብኝ ነው። ለማን አቤት ይባላል ? የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረድልኝ ፣ ዘመዶቼ ምን ልሁን ? እንዴት እንደምሆን እስኪ ፍረዱኝ፤ የምሆነው ነገር ግራ ገብቶኛል፤ ብቻዬን ነኝ "

🔻

ሌላ እናት የአካባቢው ነዋሪ ፦

" ... በደካሞች ላይ ቤት አፍርሶ ለሌላ መስጠት ለባለሃብት መስጠት ማለት ይከብዳል ያማል።

ለሌላ ትንኮላም አልሄድን ዓመት ሙሉ ስንሟገት አርብ ተወሰነልን ተብሎ ደስታችንን ሳንጨርስ የስራ ሰዓት አዘናግተው በእረፍት ሰዓት መጥተው ቁጭ ባልንበት ነው ያፈረሱብን። ዋና ዋና እቃዎችን እንኳን ማውጣት አልቻልንም ነበር።

... እኔ ልጄን ልያዝ እቃ ልጎትት ? እነሱም ደካማ ናቸው። አባታችንም እራሳቸውን መቆጣጠር አይችሉም ። ጎረቤት ባይደርስልን የተሻለ የምንለውን እቃ ማውጣት አንችልም ነበር።

መንግስትን በጣም ነበር የምንደግፈው ለውጥ አየን ብለን ግን አሁን ላይ በሰው የምናየው ስናዝን የነበረው ነገር በራሳችን ላይ ስለተፈፀመ እግዚአብሔር ፍትህ ይስጠን።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን ለፍትህ ነው የምቆመው ብሏል ፍትህ ይስጠን ፤ ልጅ ይዘን ነው እየኖርን ያለነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሙከጀላ በኤደን ገስላሴ.pdf
ኔሞ የሽናሻ_ታምሩ ዳኘው.pdf
305.2 KB
#4

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

''ኔሞ'' የሽናሻ ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት

አዘጋጅ: ታምሩ ዳኘው

" ኔሞ " ሽናሾች የሚመሩበት፣ የሚተዳደሩበት፣ እና ፍትህ የሚያገኙበት የህይወታቸው አንድ አካል ነው። የሺናሻ ብሄረሰብ በውስጡ ከ16 በላይ ንዑሳን ጎሳዎች ሲኖሩት እነዚህ ጎሳዎች ለኔሞ ስርዓት እንዲያመች ሆነው በሶስት ይከፈላሉ።

እነዚህም ጎሳዎች በብሄረሰቡ ባህል መሰረት “ሦስት ጉልቻ” ተብለው ይጠራሉ። ሦስቱ ጎሳዎች ዶዎ፣ ኢኖሮ፣ እና ኢንዲዎ ይባላሉ። ከእነዚህ ሶስቱ ጉልቻዎች አንዱ እንኳን ቢጎድል የኔሞ ስርዓትአይከወንም።

የቦሮ-ሽናሻ ብሄረሰብ ባህላዊ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቶች አራት ደረጃዎች አሉት። እነዚህም፦

#ቡራ፦ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ የሚሰጥበት “ቡራ”በመባል ይታወቃል:: ቡራ አንድ ሽማግሌ ብቻውን ሆኖ የሚፈርድበት የቤተሰብ ባህላዊ ችሎት ነው።

#ኔማ፦ ሁለተኛ ደረጃ ፍርድ የሚሰጥበት የዳኝነት ክፍል”ኔማ” ይሰኛል። በዚህኛው ደረጃ ሦስት ሽማግሌዎች ግራናቀኝ አይተው ፍርድ ወይም ፍትህ ይሰጣሉ ተብሎ ይታመናል።

#ፄራ፦ ሶስተኛው የዳኝነት ክፍል ወይም ችሎት “ፄራ” ይባላል::ይህ ባህላዊ ችሎት የሚመራው በአንድ ባህላዊ ሹም ዳኛ ነው። በዚህ ክፍል ኔማ ችሎት መፍታት ያልቻለው ጉዳይ በጥልቀት ይታያል።

#ፋላ፦ ይህ በሺናሻ የመጨረሻ ወይም ከፍተኛ የዳኝነት አካል ነው፡፡

የሽናሾች ባህላዊ የኔሞ ስርዓት ዘመናዊውን ዳኝነት እጅጉን የማገዝ አቅም አለው። በአመክንዮአዊነቱ (ምክንያታዊነቱ) ዘመናዊ አስተሳሰብንና ፍትህን በሚዛናዊነት አስተናግዶህብረተሰቡ በሰላም ተሳስቦ መኖር እንዲችል አስተዋፅኦውወደር የሌለው በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ባህላዊ እሴት ነው።

📁 ሙሉ ጹሑፉን ከላይ ተያይዟል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" አሁንም 10 ሰዎች ታግተዋል ፤ አጋቾቹ ብር ይፈልጋሉ " - አቶ ውብሸት አበራ

ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ከታገቱ ዜጎች መካከል እስካሁን 360ዎቹ የክልሉ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ስራ መለቀቃቸውን የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል ገለፁ።

አጋቾቹ በራሳቸው አንድ ወንድ እና አንድ ሴት መልቀቃቸውን ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

አሁንም 10 ሰዎች መታገታቸውን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው አጋቾቹ ብር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ትናንት በስፍራው ከታገቱት ዜጎች ውስጥ ሁለት የደራ ባለሀብቶች እንዳሉበት ተገልጿል። ዋና አስተዳዳሪው የታጋቾችን ብዛት እና ማንነት በተመለከተ መረጃው የተገኘው አምልጠው እና ተለቀው ከመጡ ሰዎች መካከል እንደሆነ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአዲስ አበባ ፍቼ ደራ መስመር የፌዴራል የጸጥታ ኃይል እንዲሰማራ ተጠይቋል።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መስመር ላለፉት ስምንት ወራት ተዘግቶ መቆየቱን አስታውሰዋል። የመኪና መንገዱ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ቢጀምርም ትናንት ሰዎች ግን መታገታቸውን ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ በአካባቢው እንዲሰማራ ጠይቀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው የፌዴራል ሰራዊት እንዲሰማራ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሰላም ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን እና ምላሽ እንዳላገኙ ገልፀዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማኅበር፣ ከግል ከፍተኛ ተቋማት የሚወጡ ምሩቃን በአንዳንድ የመንግሥትና የግል ቀጣሪዎች ተቀባይነት እንዳላገኙ አስታወቀ፡፡

ማኅበሩ ይህንን ያስታወቀው ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ውይይት ነው፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሞላ ፀጋዬ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ አንዳንድ የመንግሥትና የግል ቀጣሪዎች ከግል ከፍተኛ ተቋማት የሚወጡ ተማሪዎችን አይቀጥሩም ብለዋል፡፡

በተለያዩ የትምህርት መርሐ ግብሮች ተመርቀው በሥራ ላይ የሚገኙ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የወጡ ሠራተኞችም፣ ‹‹የደረጃ ዕድገት አንሰጥም›› እንደተባሉም አስረድተዋል፡፡

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን አንቀጥርም የሚሉ የመንግሥትና የግል ድርጅቶች መኖራቸውን፣ ከእነዚህም መካከል ባንኮችና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችም መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

ከመንግሥት ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ መሆኑን፣ ሌሎችም የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ምሩቃንን አንቀበልም (አንቀጥርም) መባላቸውን ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

በተለይ በአንዳንድ የክልል ከተሞች ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ተመርቀው በሥራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች፣ የደረጃ ዕድገት እንደማያገኙና የማይቀጥሩ ተቋማት እንዳምሉ ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎችን ከማይቀበሉና ለሠራተኞችም የደረጃ ዕድገት ከሚከለክሉ ክልሎች መካከል አማራና ደቡብ ይገኙበታል ብለዋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-06-26-2

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#ZH

ያገለገሉ እና አዲስ ካሜራ እና የካሜራ እቃዎችን እንገዛለን እንሸጣለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ያገኙ https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw

ይደውሉልን 0911284905

አድራሻ= ቦሌ ወሎ ሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ 205
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ / ቪድዮ ፦ በኦሮሚያ ክልል ፤ ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ፤ ቶሌ ቀበሌ ላይ ባለፈው ሰኔ 11 /2014 የተፈፀመውን የንፁሃን ግድያ በማውገዝ ሰልፍ የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፀጥታ ኃይሎች እንደበተኗቸው ለማወቅ ተችሏል። ተማሪዎቹ " ሞት ይብቃን፣ አትግደሉን...ያልሞትነው ተራችን ገና ስለሆነ ነው ፣ ዛፉ ከሰው ልጅ ያንሳል እንጂ አይበልጥም ፣ አባይን የምንገድበው ለሰው ፣ ለድሃ እንጂ…
#Update

በርካቶች በምዕራብ ወለጋ በንፁሃን በተለይ በህፃናት እና ሴቶች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ እያወገዙ ይገኛሉ።

በተለይ በአማራ ክልል በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ፍትህ እንዲሰፍን፣ መንግስት ንፁሃንን የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ሰልፍ በማድረግ ጭምር እየጠየቁ ይገኛሉ።

ዛሬ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተጠያቂነት እንዲሰፍን፣ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፀም ዘር ተኮር ግድያ እንዲቆም፣ ፍትህ እንዲሰፍን ጠይቀዋል።

(በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አመፅ እንደተቀሰቀሰ ፤ ተማሪዎች አመፅ እንዳስነሱ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውና ተማሪዎቹ በሰለጠነ መንገድ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን የወልዲያ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል)

ባለፈው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጎ ተማሪዎች ድምፃቸውን ማሰማታቸው አይዘነጋም ፤ ትላንትና ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድምፃቸውን ለማሰማት ቢወጡም በፀጥታ ኃይሎች ተደብደበው እንዲበተኑ ተደርጓል።

በሌላ በኩል ዛሬ እናት፣ መኢአድና ኢህአፓ ፓርቲዎች በምዕራብ ወለጋ የተፈፀመውን ገድያ በማውገዝ ሻማ በማብራት ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዜጎችም ድርጊቱን እያወገዙ የሀዘን ስነስርዓቶች እያደረጉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
" ... ለዩትዩብ (YouTube) ሽቀላ ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች መቆም መቻል አለባቸው " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ፦

" ...በዳይስፖራ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ሚዲያዎች ለዩትዩብ ሽቀላ ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች መቆም መቻል አለባቸው።

ተመልከቱ ሀገር ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር እነኚህ ጦርነቶች ካልቆሙ ሩዋንዳን የሚያስንቅ ፣ ሶሪያን የሚያስንቅ በጣም በጣም አስጠሊታ ዘግናኛ የሆነ እልቂት እየመጣ ነው።

nobody will win አማራ አያሸንፍም ፣ ኦሮሞ አያሸንፍም፣ ትግራይ አያሸንፍም it's a lose lose war ስለዚህ በሶሻል ሚዲያ እና በሚዲያው ላይ ያሉ ወንድሞቻችን የራሳቸው ብሄር መሞት እና መገደልን መኮነን አንድ ነገር ነው ከዛ አልፎ revenge የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ መቀስቀስ የራስን ብሄር የባሰ ማጋለጥ ነው።

ስለዚህ በተቻለ መጠን የምማፀነው ... እባካችሁ የውጭ ኃይሎች የእግር ኳስ ቡድን እንደምንመስል ያጨበጭቡልናል ዱላ ሲያልቅብን ያቀብሉናል። የኛው ደግሞ safe haven ውስጥ እየተቀመጠ እየነደደ ባለ እሳት ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋል።

Syria was one of the fastest growing country in the middle east ዛሬ በእኛ ከተሞች ጎዳና ላይ ይለምናሉ።

የstate መፍረስን ብዙ ትችት ያነሳብኛል ከኦሮሞዎቹ collapse of state በተለይም multinational , multiethnic, multireligious በሆነ ሀገር ውስጥ የማያልቅ የማያባራ micro conflict ይፈጥራል።

አሁን እየሄድንበትን ያለነው በፍጥነት ቀልብ ገዝተን እንዚህን ጦርነቶች አቁመን ወደ ውይይት ካልመጣን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ነው የምንገባው።

ስለዚህ ውጭ ሀገር ያላችሁ ለህዝባቹ መብት ታገሉ፣ የህዝባችሁን መብት ስትታገሉ ግን priority የአንዱን ቡድን አሞግሶ ሌላውን በማንኳሰስ በማሳነስ ሳይሆን የሰዎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ነው።

ልድገምላችሁ የአማራ ግድያ ቆሞ የኦሮሞ ግድያ ሊቀጥል አይችልም ፣ የኦሮሞ ግድያ ቆሞ የአማራ ግድያ ሊቀጥል አይችልም ገድያ ከቀጠለ ሁላችንም ነው የምንሞተው ሁላችንም ነው የምንገዳደለው እንዚህ ግዳያዎች ላይ ሁላችንም ተሳታፊዎች ነን ይሄን በመረዳት በተቻለ መጠን ሰላም ለሀገራችን እንዲመጣ፣ ሰላም ለህዝባችን እንዲመጣ ሁሉም የጋራ ስራ መስራት አለበት። "

ያንብቡ ⬇️

https://telegra.ph/Jawar-Mohammed-06-26-2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ_አይለያችሁ !

የ " FIAS 777 " ጉዳይ ከተነሳ በኃላ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ልክ እንደ " FIAS 777 " ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን እየጠቆሙ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት ያለብንን የኢኮኖሚ ችግር ተገን አድርገው " በአጭር መንገድ ትርፋማ የሚሆኑበት የማለፋ ስራ " እያሉ በርካታ ወጣቶችን እየቀሰቀሱ ገንዘባቸውን ላፍ እያደረጉ ናቸው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ተጠያቂ የምታደርጉት ሰው በሌለበት፣ ቢሮ ሆነ አድራሻ በሌላቸው ሰዎች ፣ ነገ ይቀጥል አይቀጥል የሚለውን በማታውቁት ሂደት በአሰቸጋሪ ሁኔታ ደክማችሁ ለፍታችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ፣ ተበድራችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ ፣ ተማሪዎችም ከቤተሰብ የተቀበላችሁትን ገንዘብ ለቀማኞች እንዳታውሉት አደራ እንላለን።

ብዙሃንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ በሚስጥር አይሰራምና ገንዘባችሁን ከሚያሳጣ ማንኛውም የአጭበርባሪዎች እንቅስቃሴ ራቁ።

ሌላው ደግሞ የስልክ ቀፎ፣ ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ... የመሳሳሉ እቃዎችን በርካሽ ከደቡብ አፍሪካ ፣ ከኬንያ በሞያሌ በኩፓ እናስመጣለን እያሉ ቅድመ ክፍያ እየተቀበሉ እብስ የሚሉ አሉና ተጠንቀቁ።

ሰዎችን ማታለያ መንገዶች አይነታቸውን እየቀያየሩ እየበዙ ነውና ህጋዊ ተጠያቂነት ያለባቸው ስራዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ።

ሁሌም ጥንቃቄ ማደረጋችሁን አትዘንጉ።

@tikvahethiopia
#DoubleA

የ “Double A QR Ethiopia” የሞባይል መተግበርያን በስልክዎ  በመጫን በትክክለኛው የ Double A  ወረቀት ካርቶን ላይ የሚገኘውን የ  QR ኮድ የሞባይል መተግበሪያውን ተጠቅመው ስካን በማድረግ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ይሸለሙ::

መተግበርያውን ለማውረድ:
Link: https://bit.ly/3KGYCxC  Or
https://da-cloud.advanceagro.net/index.php/s/WYovIsmE4u2Kz6y

ለተጨማሪ መረጃ: https://DoubleArewards.com/Ethiopia
#ጥንቃቄ | ዩኒቨርሲቲዎች፣ ተማሪዎችና አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ማህበረስብ አባላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላለፈ !

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

ግብረ ኃይሉ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህውሃት ቡድን ፋይናንስ ያደርጋቸዋል ያላቸው ሚዲያዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ ተማሪዎች በብሄርና በሀይማኖት በመከፋፈል ግጭት እንዲፈጠር ለማነሳሳት ሌት ተቀን እሰሩ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል።

እነዚሁ ሚዲያዎች ሰሞኑን «በአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ተማሪዎችን ለማጥቃት የተደራጀ የደህንነት ቡድን ወደ አማራ ክልል ተልኳል» የሚል በዩኒቨርሲቲዎች ግጭት ለማስነሳት መልዕክት አስተላልፈዋል ብሏል።

የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላም ለማናጋት እና ተማሪዎች በሰላም እንዳይማሩ የሚያደርጉ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ያሳሰበው ግብረኃይሉ ይህን ተላልፈው በሚገኙት ላይ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወድ አስጠንቅቋል።

ዩኒቨርሲቲዎች፣ ተማሪዎችና ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ሆን ተብሎ ግጭት ለማስነሳት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በመገንዘብ እራሳቸውን በመጠብቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።

(የግብረ ኃይሉ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia