TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ፎቶው ለምርጫ 2013 ያነሳሁት ነው" - አማኑኤል ስለሺ

ከሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ #የትግራይ_ተወላጆች ያለ ምንም አግባብ ለእንግልትና ማንነትን መሰረት ላደረገ እስር እየተዳረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ የሰጠውን ምላሽንም ሰምተናል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አንድሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጎ ነበር።

አምነስቲ በሪፖርቱ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የትግራይ ተወላጆችን ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ መልኩ አስሯል ብሏል።

የትግራይ ተወላጆች ለእስር የተዳረጉት የትግራይ ኃይሎች መቐለ ከገቡ በኋላ ነው ያለ ሲሆን እስሩም ማንነትን መሠረት ያደረገ ይመስላል ሲልም ይገልጻል።

የፌደራሉ መንግስት በሰብዓዊነት ላይ ያተኮረ የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች መታሰራቸውን ድርጅቱ በሪፖርቱ አምልክቷል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስርን እንዲያቆም እንዲሁም ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል።

አምነስቲ በዚህ ሪፖርቱ አንድ ፎቶ ያያዘ ሲሆን ፎቶው ግን ከሪፖርቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ለማረጋገጥ ችለናል።

የዚህ ፎቶ ባለቤት ፎቶግራፈር አማኑኤል ስለሺ ሲሆን ፤ የፎቶ ባለሞያው ለAFP ነው የሚሰራው ፤ አምነስቲ የተጠቀመው ፎቶግራፍ ለምርጫ 2013 የተነሳ እንጂ ከእስሩ ጋር የተያያዘ አይደለም።

አማኑኤል ስለሺ ፥ "አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተጠቀመው ፎቶ ለምርጫ ያነሳሁትን ነው፤ ድርጊቱ ስህተት ነው" ሲል የቲክቫህ ቤተሰቦች እወቁልኝ ብሏል። አምነስቲ በአስቸኳይ ፎቶውን እንዲያወርድም ጠይቋል።

@tikvahethiopia