TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጄነራሎቹ⁉️

የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዋና ሃላፊ ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው መያዛቸው ተነገረ። ሃላፊው ከትግራይ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው ጀነራሉ የተያዙት ትናንት ማምሻ ሁመራ ከተማ ውስጥ ነው።

#የትግራይ ልዩ ፖሊስ ጀነራሉን ከያዘ በኋላ ለፌደራል መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች #ማስረከቡን ምንጮች አስታውቀዋል። ከጀነራል ክንፈ ዳኘው በተጨማሪ የቀድሞ ኢንሳ በሚል ምህጻረ ቃል የሚጠራው የመረጃ ቴክኖሎጂ መስሪያ ቤት የቀድሞ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል #ተክለብርሃን_ወልደአረጋይም ከሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጋር #መያዛቸውን የተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበው ነበር።

ይሁን እና ጀነራል ተክለብርሃን የፍርድ ቤት #የማሰሪያ ትዕዛዝ አልተሰጠባቸውም በሚል እንዳልተያዙ ምንጮቼ ገልጸዋል ብሏል የጀርመን ድምፅ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት ክፍል።

ጉዳዩን #ለማጣራት የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እያነጋገረን ነው እንደደረሰን መረጃውን እናቀርባለን ብሏል የጀርመን ድምፅ።

ሁለቱን ጀነራሎች ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ከፍተኛ የጦርና የመረጃ (ስለላ) ባለሥልጣናት እሥረኞችን በማሰቃየት እና በሙስና ወንጀል እንደሚጠረጠሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትንንት አስታውቆ ነበር።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የመከላከያ ሰራዊቱን #ማገት የሚለው አስቸጋሪ ነው፡፡ #መከላከያን ማንም ሊያግተው አይችልም፡፡ አማርኛው ቢቀየር ጥሩ ነው። ሰራዊቱን #የትግራይ_ህዝብ አያገትም፡፡ ነገር ግን #ስጋት እየፈጠረ መኖር የለመደ አካል አለ፡፡ በጣም ጥቂት ነው፡፡ ህዝቡን ሽፋን አድርጎ ትርምስ ለመፍጠር የሚሞክር ኃይል አለ፡፡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ እርግጠኛ ነኝ #ይጋለጣሉ፡፡ የትግራይ ህዝብም #ቢዘገይም ይገባዋል፡፡ እንዲጋለጡና ህዝቡም እንዲያውቃቸው እናደርጋለን፡፡ ይህ እስኪሆን ግን ከህዝቡ ጋር #የሚያጣላ ነገር አናደርግም፡፡ ህዝብ ቅር ከሚለው እኛ ቅር ቢለን ይሻለናል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ነገር ከክልሉ እውቅና ውጭ ነው፡፡ ክልሉ ወስኖ የተደረገ ነገር አይደለም፡፡ የክልሉ ፍላጎትም አይደለም፡፡"-የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩት፤

@tsegabwolde @tikvqhethiopia
#የትግራይ_ህዝብ_ፍቅር_ነው!

"ወደ ትግራይ እንዳትሄድ ብለው አስጠንቅቀውኝ ነበር! የመጣነው ከአዳማ፣ ኦሮሚያ ነው። ልጆቻችን ለማስመረቅ ወደ መቐለ እንሄዳለን ብለን ስንናገር #ይቅርባችሁ ተብለናል። እንሄዳለን ብለን ስንወስንም በሉ አፋን ኦሮሞ እንዳትናገሩ ብለው መክረው ስለ ላኩን አሁን ግን የቴሌቪኑ የስርጭት ቋንቋ አማርኛ ቢሆንም ደስታዬ እና መልእክቴን በአፋን ኦሮሞ ነው ማስተላልፈው!" ብለው በኣፋን ኦሮሞ ደስታቸውን መልዕክታቸውን ተናገሩ። (ከትግራይ ህዝብ ጋር 'በ በሬ ወለደ ውሸታቸው ሊለያዩን የሚያስቡ ሰዎች ጤነኛ ናቸውን?) በማለት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በአፋን ኦሮሞ ሐሳባቸውን ገለፁ።

የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛም ጎበዝ ነበር እንደ እሳቸው በአፋን ኦሮሞ ጥያቄውን አስከተለ (አንድ ቋንቋ የሚናገር አንድ ሰው ነው:ሁለት የሚናገር ሁለት ሰው ነው ይባል የለ?) ጋዜጠኛው ብዙ ሰው ነበረ፡፡ እንግዳውም ቀጥለው... በአማርኛ ቋንቋ የትግራይ ህዝብ በሄዱበት መስጊድ፣ ምግብ ቤትና መኝታ ቤት በታላቅ ክብር እንዳስተናገዷቸው ገልፀው አመሰገኑ፡፡"

ፍቅር፤ ሰላም፤ አንድነት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያን ያስቆጣው የሀርቪስቶ አስተያየት :

ከ3 ቀን በፊት የፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ለአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ነበር።

በዚህ ሪፖርታቸው ላይ ስለ #ትግራይ ጉዳይ የተናገሩ ሲሆን በይበልጥ ግን የብዙሃን መነገሪያ የሆነው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በነበረኝ ቆይታ፥ "የኢትዮጵያ ባለስልጣናት #የትግራይ_ተወላጆችን_ለማጥፋት እንደሚፈልጉ /ታጋሩዎችን ለ100 ዓመታት ማጥፋት እንደሚፈልጉ ነግረውኛል" ብለው የተናገሩት ነው።

የትኛው የኢትዮጵያ ባለስልጣን ይህን እንዳለ / ሲናገር እንደሰሙት ግን በስም ገልፀው ሲናገሩ አልታዩም።

ሀርቪስቶ የአውሮፓ ህብረትን በመወከል ለጥቂት ቀን በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገው እንደነበር አይረሳም።

ፔካ ሀርቪስቶ ከቀናት በፊት ያቀረቡት አጠቃላይ ሪፖርት ኢትዮጵያን ክፉኛ አስቆጥቷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ሀርቪስቶ ያቀረቡት ሪፖርት ኃላፊነት የጎደለው፣ መሰረት የሌለው፣ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶችን ያልተከተለና ከቅኝ ገዢነት የመነጨ ነው ብሎታል።

ሚኒስቴሩ “ፔካ ሃቪስቶ መንግስት እያከናወነ ያለውን ስራ የሚያጣጥል እና በሐሰተኛ መረጃዎች የተመሰረቱ ሪፖርቶችን፣ ውሸቶችን በማቅረብ ተገቢ ያልሆኑ ጣልቃ ገብነቶች እንዲኖሩ አድርጓል” ብሏል።

በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ ፔካ ሃቪስቶ ከጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ፣ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ ከም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አውስቶ፤ የቀረበው ሪፖርት ግን ሃሰተኛና የተካሄዱ ሰፋፊ ውይይቶችን ያላካተተ መሆኑን ተገልጿል።

* የፔካ ሀርቪስቶ ሪፖርት ፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
"ፎቶው ለምርጫ 2013 ያነሳሁት ነው" - አማኑኤል ስለሺ

ከሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ #የትግራይ_ተወላጆች ያለ ምንም አግባብ ለእንግልትና ማንነትን መሰረት ላደረገ እስር እየተዳረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ የሰጠውን ምላሽንም ሰምተናል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አንድሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጎ ነበር።

አምነስቲ በሪፖርቱ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የትግራይ ተወላጆችን ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ መልኩ አስሯል ብሏል።

የትግራይ ተወላጆች ለእስር የተዳረጉት የትግራይ ኃይሎች መቐለ ከገቡ በኋላ ነው ያለ ሲሆን እስሩም ማንነትን መሠረት ያደረገ ይመስላል ሲልም ይገልጻል።

የፌደራሉ መንግስት በሰብዓዊነት ላይ ያተኮረ የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች መታሰራቸውን ድርጅቱ በሪፖርቱ አምልክቷል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስርን እንዲያቆም እንዲሁም ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል።

አምነስቲ በዚህ ሪፖርቱ አንድ ፎቶ ያያዘ ሲሆን ፎቶው ግን ከሪፖርቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ለማረጋገጥ ችለናል።

የዚህ ፎቶ ባለቤት ፎቶግራፈር አማኑኤል ስለሺ ሲሆን ፤ የፎቶ ባለሞያው ለAFP ነው የሚሰራው ፤ አምነስቲ የተጠቀመው ፎቶግራፍ ለምርጫ 2013 የተነሳ እንጂ ከእስሩ ጋር የተያያዘ አይደለም።

አማኑኤል ስለሺ ፥ "አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተጠቀመው ፎቶ ለምርጫ ያነሳሁትን ነው፤ ድርጊቱ ስህተት ነው" ሲል የቲክቫህ ቤተሰቦች እወቁልኝ ብሏል። አምነስቲ በአስቸኳይ ፎቶውን እንዲያወርድም ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን  መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ኤስያ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ። 

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?

- የፖለቲካ ፍላጎትን መሠረት አድርጎ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ኢትዮጵያ አትቀበልም ብለዋል። የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው አካላት ገፋፊነት እና አስተባባሪነት የተላለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ምድር ተፈፃሚ እንደማይሆን አስረግጠው ተናግረዋል።

- የህወሓት አሸባሪ ሀይል በደረሰበት ምት ይዟቸው የነበሩ አብዛኛው የአፋር እና የአማራ አካባቢዎችን በማስለቀቅ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልፀዋል። ይህም ቡድኑ ለሰላም ሲል በወረራ ከያዝኳቸው አካባቢዎች ለቅቂያለሁ ማለቱ ከተጨባጩ እውነታ ጋር የሚቃረን ነው ብለዋል።

- መንግስት ቡድኑ (ህወሓት) በሚሸሽባቸው እያንዳንዱ #የትግራይ_መንደሮች እግር በእግር በመከተታል የመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል፤ ነገር ግን ቡድኑ መቸውም ቢሆን መልሶ ጥቃት የማድረስ አቅሙ የተዳከመ መሆኑ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

- የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትን ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ መጠን፣ ትግራይን ጨምሮ #በማንኛውም_ሀገሪቱ_አካባቢዎች ሰራዊቱን የማስፈር መብት እንዳለው ተናግረዋል።

- በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ ሁሉን አካታች ዉይይት እንዲኖር ማንኛዉም በአገሪቱ ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አካል የሚሳተፍበ የህገ መንግስት ማሻሻያን ጨምሮ በሀገሪቱ ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ለውይይት ክፍት እንደሚደረጉ ገልጸዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Minstry-of-Foreign-Affairs-of-Ethiopia-12-21

@tikvahethiopia
#PressBriefing

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር ፤ በመግለጫቸው ያነሷቸው ነጥቦች እና ተጠይቀው ከመለሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ጥቂቶቹ ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ተመድ [UN] ሊያደርገው ያቀደው ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በኢሰማኮ እና በተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋራ ሪፖርት ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል። ነገር ግን በተመድ በኩል ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የሚደረገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

- ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ አገራዊ ምክክሩ በሂደት ላይ መሆኑ እና ሰላምን የማስፈን ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።

- ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻዋን እንዳጣች በሚመለከት ይፋ የሆነውን መረጃ በተመለከተ መንግስት መረጃውን እያጣራ ይገኛል ብለዋል።

- መንግስት ሱዳን የያዘችው የኢትዮጰያ መሬት በሌሎች የኢትዮጰያን መረጋጋት በማይፈልጉ አገራት ግፊት የወሰነችው ውሳኔ አድርጎ እንደሚወስደው ገልፀዋል። አሁንም ቢሆን መንግስት ሱዳን ከያዘችው የኢትዮጵያ ግዛት ያለ ግጭት ለቃ እንደምትወጣ ተስፋ አለው ብለዋል።

- ከሰሞኑ ገንዘብ ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም በጀትን ለክልሎች ሲደለድል #የትግራይ_ክልልንም አካቷል ፤ የበጀት ድልድሉ #ድርድር ስለመጀመሩ አመላካች ነው ወይ ? ተብሎ ለተነሳ ጥያቄ አምባዳደር ዲና ሙፍቲ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Credit ፦ #ኤፍቢሲ #አሀዱሬድዮ #ኢትዮኤፍኤም

@tikvahethiopia
" #የአማራ እና #የትግራይ ህዝቦች ዝም ብሎ ጆግራፊ አይደለም ያስተሳሰራቸው ፤ የጋራ ታሪክ አላቸው ፈለግንም አልፈለግንም አብሮ መኖራቸው አይቀርም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ከብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ቃለ ምልልሳቸው ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲሱ አመት 2016 ዓ/ም አስተዳደራቸው ፦

- የሰላም ጅምሩ እንዲጠናከር እንደሚሰራ ፤
- ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንደሚሰራ፤
- ከምንም በላይ በዜጎች አእምሮ ላይ የተፈጠረውን ስብራት ለመጠገን እንደሚሰራ፣
- የተቋረጡ የማህበራዊ አገልግሎቶች ለአብነት ትምህርት ፣ጤና አገልግሎቶች ከጦርነት በፊት ወደነበሩበት ለመመለስ ተስፋ ሠጪ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንደሚሰራ፤
- ምርጫ ተድርጎ የሚመረጠው አስተዳደር በተሟላ መልኩ ትግራይን የሚያስተዳድረበት በፌዴሬሽኑ ውስጥ ትግራይ ያላትን ተሳትፎ የሚያረጋግጥ መንግሥት እንዲሆን የፖለቲካ ስራዎችን ለመስራት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ምርጫ መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ጌታቸው " ዋናው መሬት ላይ ያለው እውነታ ነው። ምርጫ ብቻችንን አይደለም የምናደርገው ፤ የፌዴራል መንግሥቱ ፣ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉዳይ ውስጥ መካከት አለባቸው ፤ የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ምርጫ መሆን አለበት " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ምርጫ ስለሚደረግበት ቀን ቁርጥ ያለ ጊዜ አልተናግሩም።

የአማራና የትግራይ ህዝቦችን ግንኙነት በተመለከተ በአዲሱ አመት ስለታቀዱ እቅዶች ተጠየቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ የሚጠየቅበትን ሁኔታ መመቻቸት አለበት ፤ ለዚህ ችግር የለብንም ብለን ብዙ ሰው በእኛ አካባቢ የችኮላ ነው የሚለውን እርምጃ ባህር ዳር ሄደን ያለንን የሰላም ፍላጎት ገልጸናል። ከዛ አንስተን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ ተፈናቃዮችን መመለስ ጀምረን ልዩነቶቻችንን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችል ነገር ውስጥ እንገባለን ብለን መንቀሳቀስ ጀምረን ነበር " ብለዋል።

ይህ እንቅስቃሴ በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም ያለቱ ፕሬዜዳንቱ " በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም ማለት አይሄድም ማለት አይደለም። እንዲሄድ መስራት አለብን ምክንያቱም የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች ዝም ብሎ ጆግራፊ አይደለም ያስተሳሰራቸው ፤ የጋራ ታሪክ አላቸው ፈለግንም አልፈለግንም አብሮ መኖራቸው አይቀርም ፤ ቢረፍድ ይሻላል ፈፅሞ ከሚቀር እንደዚህ አይነት ነገር ስለዚህ እሱን (የተጀመረውን ግንኙነት) በአዲሱ አመት አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

አዲሱን ዓመት በማስመልከተም አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና በውጭ ላለው ዳያስፖራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቀው የሚገባው ፤ ግጭት አንድ አካባቢ ስላለ cheer ማድረግ ይቁም። አንድ አካባቢ ያለ ግጭት የሁላችንም ግጭት መሆኑን እንረዳ፤ አንድ አካባቢ ያለ ጥፋት የሁሉም ጥፋት ነው ብለን እንቀበል ፤ መንግሥት ወደልማት ጎኑ ለመሄድ የሚያደርገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ነገር ካለ ልማት ነው የሚያዋጣን የሚለው ድምፅ ጎልቶ እንዲወጣ ለማድረግ የሚያስችል እገዛ ይደረግ " ብለዋል።

" ዳያስፖራ ማጋጋል ፣ ማጋጋል ፣ ማጋጋል መሆን የለበትም ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግጭትን ከማጋጋል ስለሰላም መስበክ የሁሉም ድምፅ መሆን መቻል አለበት፤ እነ እገሌን ካላንበረከክን እነ እገሌን ካላሸነፍን ሞተን እንገኛለን የሚል አስተሳሰብ ሁላችንንም ወደ ጥፋት የሚወስድ እንጂ አንዱን የሚጠቅም አይደለም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
" የምንበላው አጥተናል ፤ የምንሄድበትም ጠፍቶን ጨልሞብናል። "

በባለፉት የክረምት ወራት ባጋጠመ የዝናብ እጥረት በተለያዩ #የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ጉዳት እየደረሰ ነው።

በተለይ አበርገለ ጭላ ወረዳ የበረታ ድርቅ በመከሰቱ የሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት እንደሆነ በርካቶችም ከቄያቸው ወጥተው ወደልመና እንዲገቡ እንዳደረገ ተነግሯል።

አንዲት እናት ፦

" በየአካባቢያችን ድርቅ ስላጋጠመን ወደጭላና ሌሎች ቦታዎች ሄደን እየለመንን ነው።

በየአካባቢያችን ምንም እህል የለም። የተወስኑ አካባቢዎች ብቻ ነው የተወሰነ ዝናብ የዘነበው እንጂ አብዛኛው አካባቢ እህል የሚያበቅል በቂ ዝናብ አልዘነበም።

አብዛኛው ሰው ወደ ልመና ተሰማርቶ ነው ያለው።

እርዳታ እንኳን ከተቀበልን 1 ዓመት ሆኖናል ከዛ በኃላ ተሰጥቶን አያውቅም። አጠቃላይ የዚህ አካባቢ ማህበረሰብ ተጎድቷል። ሁሉም እየተቸገረ ስለሆነ አንዳንዴ ለምነንም አናገኝም። በርካታ ሰዎችም በረሃብ እየሞቱ ነው። መንግሥት እርዳታ ያድርግልን ልጆቻችንም ትምህርታቸውን ይቀጥሉ። "

ሌላ አንዲት እናት ደግሞ ፦

" ከልጆቼ ጋር በጣም ስለተራብኩ ነው ወደ ጭላ ከተማ የመጣሁት። እዚህም ምንም የለም። ልጆቼን ይዤ በጣም ተቸግሪያለሁ።

አምስት ልጆች አሉኝ ሲጨንቀኝ ጊዜ 3ቱን ልጆች ሰው ቤት አስጠግቼያቸዋለሁ። ሁለቱ ከእኔ ጋር ናቸው ግን የማበላቸው የለኝም። ከዚህም ከዚያም እየለመንን እየዋልን እያደርን ያለነው።

በጣም ከፍቶናል፤ እርዳታ ካቆመ ቆይቷል። አንዳንዴ ሲጨንቀኝ የቀን ስራ እየሰራሁ የልጆቼን እራት አገኝ ነበር አሁን ግን የቀን ስራም የለም የምንሄድበት ጠፍቶን ጨልሞብናል። "

አንዲት ልጅ ደግሞ ፦ በመራቧ ምክንያት ትምህርት ማቋረጧንና ወደ ጭላ የሚበላ ፍለጋ መምጣቷን ገልጻ ፤ በየቀኑ እየለመንን ነው የምንበላው ብላለች። እርዳታ ይሰጠን ስትል ተማፅናለች።

የድርቁ ተጎጂዎች አስከፊው ድርቅ እንዳለ ሆነ ለነፍስ ማቆያ የሚሆነው እርዳታ ተቋርጦ በመቆየቱ ህይወት ጨልሞብናል ፤ መንግሥት ህይወታችንን ይታደግ ብለዋል።

የወረዳው አስተዳደር ምን ይላል ?

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሃጎስ ሃደራ ፦

" ህብረተሰቡ በችግር ላይ ችግር ወድቆ አደጋ ላይ ነው ያለው። የክረምት ወቅቱ በጣም የዝናብ እጥረት ነበረበት ፣ተባይም እንዲሁ የማዳበሪያ አቅርቦቶም ችግር ነበር ሌሎችም ምክንያቶች ነበሩ እነዚህ ሁሉ ተደማምረው ህዝቡ ላይ የደረሰው አደጋ አስከፊ ነው።

ከ7 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። እስከ 5000 ሺህ የሚያህል ተማሪ ተበቷል። ተመዝግቦ ነበር አሁን የለም።

አስከፊ ረሃብ አለ፣ ሞትም አለ፤ እስካሁን ከ210 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ ከመድሃኒት እጥረት፣ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ነው።

ችግሩን ለመፍታት የፌዴራል መንግሥት በማስተባበር ተግባራዊ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል። የተፈናቀሉ ሰዎችም ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለበት፤ እስኪመለሱ ደግሞ እርዳታ መምጣት አለበት። ህዝቡ አደጋ ላይ ነው ያለው ህዝቡ ሳያልቅ መድረስ አለበት። "

መረጃው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ለድምፂወያነ ቴሌቪዥን ከሰጡት ቃለመጠየቅ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለአስቸኳይ ህይወት አድን የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ አስታወቀ።

ካቢኔው ህዳር 16/2016 ከሰዓት በኃላ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በከባድ የድርቅ አደጋ ለተጎዱ መርጃ የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ ያስረዳል። 

ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ፤ በተለይ በሦስት ዞኖች ፣ 12 ወረዳዎችና 47 ቀበሌዎች ከባድ የድርቅ አደጋ ማጋጠሙ ተከትሎ በርካታ ስዎችና እንስሳት ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል። 

የተመደበው ገንዘብ በቂ እንዳልሆነ የጠቆመው መግለጫው ፤ የክልሉ ተወላጅ ባለሃብቶች ፣ ዳያስፓራዎችና የትግራይ ህዝብ ወዳጆች የሚቻላቸው ድጋፍ በማድረግ የወገንና የእንስሳት ህይወት እንዲታደጉ አደራ ብሏል።

በድርቅ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጠው ህዝብ ለማዳን የውጭ እርዳታ ከመጠበቅ የውስጥ አቅም አማጦ መጠቀም ወሳኝ ነው ያለው የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤቱ መግለጫ ይህንን ለመተግባር ጊዚያዊ አስተዳደሩ አቅጣጫ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በባለፉት የክረምት ወራት ባጋጠመ የዝናብ እጥረት በተለያዩ #የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ጉዳት እየደረሰ ነው።

በተለይ አበርገለ ጭላ ወረዳ የበረታ ድርቅ በመከሰቱ የሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት እንደሆነ በርካቶችም ከቄያቸው ወጥተው ወደልመና እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ተነግሯል።

መረጃውን ያደረሰን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
የሙስሊም ሊቃውንት/ #ዓሊሞች ጉባዔ ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ  እየተካሄደ ይገኛል።

ለሶስት ቀን ይቆያል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት ሁለተኛው ዓመታዊ የዓሊሞች (የሙስለም ሊቃውንት) ጉባዔ ላይ ፦
- #የትግራይ
- የሶማሊ
- የአፋር
- የአማራ
- የኦሮሚያ
- የጋምቤላ
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ
- የደቡብ ኢትዮጵያ
- የሐረሪ
- የሲዳማ
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ የዑላማ ምክር ቤቶች እተካፈሉ ይገኛሉ።
                          
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ትላንት ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ፤ " ጦርነት በፈጠረው የሰላም እጦት ችግር ሳቢያ ተለያይተን ከነበርነው የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር ግንኙነታችን ቀጥሎ ዛሬ በአንድ ጉባዔ ላይ መታደማችን የሚያስደስትና የሠላምን ዋጋ ከፍ የሚያደርግ ነው " ብለዋል።

ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፤ " የሀገራችን ሙስሊም ሊቃውንት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው ዲኑን ለትውልዶች ለማሻገር እና ማኀበራዊ ትስስር እንዲፈጠር ትልቅ ልፋት የሚያደርጉ ታላቅ የሕዝብ ባለውለታና የዲን መሪ ናቸው " ብለዋል።

የሀገር አቀፉ የዑለማ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀይላን ኸድር በበኩላቸው፣ " የዑለማው በዚህ ዓይነት ትስስር መፍጠር ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነት ትልቅ ፋይዳ አለው " ብለዋል።

የዑለማው ጉባዔ የሙስሊሙ ችግሮች እና የሚገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚገለጹበት በመኾኑ፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲዎቾ፣ የየክልሉ የዑለማ ም/ ቤት እና የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ኃላፊዎች በዚህ መድረክ ላይ ተገናኝተው መምከራቸው መድረኩን ታሪካዊ ያደርገዋል ተብሏን።

የጉባዔው ተሳታፊ የሆኑት ክልሎች የየክልላቸውን ተጨባጭ ሁኔታ አስመልክተው ለጉባዔው ሪፖርት ማቅረባቸውን ለማቀው ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ሊቃውንት ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ እልምና ጉዳዮች ጠቅላት ምክር ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

​NB. የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር የነበረውን አለመግባባት በይቅርታ ፈቶ ወደ ቀደመው ግኝኑነት መመለሱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia